ስለእናት ግጥም

emyeinateyeimahoyatselakutsedale

 

 

 

 

 

 

ያገር ካስማ

የትዉልድ  ቋጠሮ ዉል ቀመሩ ፣

የቀጣይነት ማግ ድዉሩ፣

እናት አይደለች የክር እትብቱ፣

የትዉልድ ህላዌ ማህቶቱ።

በደሟ ስር በእትብቷ ፣

አንዳች ሳይቀር ስታካፍል ለትዉልዷ – አቤት አቤት  ደግነቷ፣

አይሰፈር አይለካ ሚስጥረ ኩን ዉበቷ።

አፏ ደርቆ አፍ አብሳ ፣

እሷን እርቧት ልጇ እንዲጠግብ ምድር አስሳ፣

ለትዉልዷ ክብር  ምድር ልሳ፣

ደስ ይላታል ልጇ ሲልቅ እሷ አንሳ።

እናትማ ፣ የትዉልድ የእትብት ቋጠሮ፣

የትዉልድ የህላዌ ማሰሮ፣

የትዉልድ ዥረት ፍሰት አምባ- የርህራሄ ባላ፣

እያጠባች ታነባለች ልጄ ራበዉ ብላ።

የሀገር እሴት  እንዳወጀዉ ፍልስምና  ፣

“ወላድ በድባብ  ትሂድ”  የትዉልድ ምንጭ ነችና።

እናትማ ያገር ማማ ፣

ያገር ካስማ የትዉልደ ሸማ፣

ትወደስ ንሳ- ስሟ ሳይቀር ፍቅረ መዓዛማ፡፡

ሸንቁጥ አየለ

መታሰቢያነት፤ ለሁሉም እናቶች

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.