ስለ ጅሩ
ስለ ጅሩ የተገጠመ ግጥም
ሀገሬ ጅሩ ነዉ
የስንዴዉ ዘለላ፡ዉል ዉል የሚለዉ
የነጩ ጤፍ ዛላ፡ የሚዘናፈለዉ፤
ተጨንቆ ተጠቦ፡ እግዜር የፈጠረዉ፤
የገነት አምሳያዉ፡ ሀገሬ ጅሩ ነዉ ፡፡
የጅሁርን ሜዳ ፡ ላየዉ ሰዉ ማማሩ፤
የወይራ አምባን ሜዳ፡ ላየዉ ሰዉ ማማሩ፤
የቦሎዉን ሜዳ፡ ላየዉ ሰዉ ማማሩ፤
የኩሳየን ሜዳ፡ ላየዉ ሰዉ ማማሩ፤
የእነዋሪን ሜዳ፡ ላየዉ ሰዉ ማማሩ፤
የማንጉዶን ሜዳ፡ ላየዉ ሰዉ ማማሩ፤
ሽዉ ሽዉ እያለ ጋያ እየዋለለ፡ ወፎች ሲዘምሩ፤
ቀልብን ያሸፍታል፡ የሰብሉ መአዛ ነፋሻዉ አየሩ፡፡ (2)
የሰንጋ ሲኒማ፡ ማየት ላማራችሁ፤
ከምእራብ ከምስራቅ፡ በርቀት ላላችሁ፤
ከደቡብ ከሰሜን፡ ወሬ ለሰማችሁ፤
በጌታ ትንሳኤ በፋሲካ በአል፡ ወረዳ ከተማዉ እነዋሪ ሜዳ ታገኙናላችሁ፡፡ (2)
ታዲያ ይሄ ሁላ፡ ሀብት ንብርት ሞልቶ፤
ምንድን ነዉ ሚስጥሩ ፡ ርቀት ያልሄድነዉ ያላደግነዉ ከቶ፤
መንገድ ያልቀየርን ፡ የምናፈራርቅ ሎንችና ና ቸንቶ፤
በሉ ስራ በሉት፡ ካድሬ ና ሚኒሻ አይዋል ተጎልቶ፤
ማየት እንሻለን ልማታችን ለምቶ፡ መንገዱም ተሰርቶ፡፡ (2)
08/12/ 2007
ቬነስያ ከለሊቱ 4፡20
Leave a Reply
You must be logged in to post a comment.