አማራው ባለፈው የታሪክ ፈለጉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ታማኝነቱን አሳይቶአል
አማራው ባለፈው የታሪክ ፈለጉ ለኢትዮጵያ ህዝብ ታማኝነቱን አሳይቶአል ነገር ግን በአቶ ተክሌ የሻው የሚመራው ሞረሽ ከተመሰረተ ጀምሮ ኢትዮጵያዉያን ድርጅቶችንና ግለሰቦችን ብቻ ሳይሆን የዉጭዉንም ተለጣፊ አካላት ማሳሰቡን በተለያዩ አጋጣሚዎች በሚናገሩትና በሚያሳዩት ባህሪ ስንታዘብ ቆይተናል። የኢትዮጵያን ህዝብ ከአንድነት ጋር የተቆራኘ ጥቅምና ደህንነት የተገለጸልን ሰዎች የሞረሽን መመስረት ከላይ የተጠቀሱት አካላት ጠቃሚ መሆኑን እንዲረዱት በተለያየ መንገድ ለማስረዳት ሞክረናል።
አማራው በኢትዮጵያ ህዝብና ባለፈው የታሪክ ፈለጉ ለኢትዮጵያም ህዝብ ታማኝነቱን አሳይቶአል። በቅጥረኞችና በከሃዲዎች ቢካድም። ከዚህ በተጨማሪ ፩) ከማንኛዉም ነገድ በበለጠ ከሌሎች ነገዶች ወይም ጎሶች ጋር በመዋሃዱ ፪) አስተሳሰቡና ስነ ልቦናው ኢትዮጵያዊ ስለሆነ ፫) ከሌሎች ነገዶች ጋር የተዋሃደው ህዝብ ብዛት ከማንኛዉም ነገድ በላይ በመሆኑና ፬) ከዚያም አልፎ አማራው እንደ አንድ ወጥ ነገድ ከሁሉም ነገዶች በቁጥር የሚበልጥ በመሆኑ የሚያደርገው የፖለቲካ እንቅስቃሴና ሚዛን አንሺ ተሳትፎው ሊከበር ይገባል።
ከዚህ ዉጭ በወያኔና በሽእቢያ የታጀበ ያረጀና ያፈጀ ተንኮልንና ፕሮፓጋንዳን በመጠቀም አማራውን በቀጣይነት ለማግለል ወይም ለማስጠቃት አለዚያም ሆን ብሎ የኢትዮጵያን ህዝብ በታትኖ አዉራ የለሽ ለማድረግና ለማኮላሸት የሚደረግ ፈተላ ሁሉ የሰብአዊ መብት መደፈርንና አጠቃላይ ዜጎችን ከማሰቃየት ዉጭ ሌላ ጥቅም የለው።
አማራው ከእንግዲህ ገብቶአቸዉም ሆነ ሳይገባቸው ወደዚያ አቅጣጫ ከሚነጉዱ ግለሶቦችም ሆነ ድርጅቶች ወም ቡድኖች ጋር በምንም አይነት ማህበር አይጠጣም። ኤርትራዉያን ወንድሞቻችን መሆናቸዉን አማራው ከማንም በላይ ያዉቃል። በሰላም ለመኖርም ችግር የለበትም። ነገር ግን ታላቁን የአማራን ህዝብ ከዚያም አልፎ የኢትዮጵያን ህዝብ ነጻ ያወጣሉ ብሎ እራሱን አያታልልም። በምንም አይነት እንኩዋን የማትታመነው ትንሹዋ ኤርትራ ሌላም ህይል ማለት ከራሱና ከእግዚአብሄር ድጋፍ በስተቀር ይረዳኛል ብሎ የሚያስበው ነገር የለም።
ይህንን ማለት መጣላት አይደልም። ሌሎች ነጻ ታወጣናለች የሚሉ ካሉ ግን መብታቸው ነው። እዚያ ዉስጡ አንገባም ነው፦ ዉጤቱንም ወደፊት እናየዋለን። አማራው ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር አብሮ ቢሰራ ደስ ይለዋል!! ካልሆነ ግን ከእንግዲህ አማራው የራሱንም ሆነ የሌሎቹን ኢትዮጵያዉያንን ደህንነትና ጥቅም ለመጠበቅ እንደአባቶቹ በራሱ በመተማመን መደራጀቱንና በቀየሰው የራሱ መንገድ ላይ ያለ ማሰለስ ይጉዋዛል እንጂ እንደ አናሳ ከሌሎች ጉያ ለመግባት ግዙፍነቱ አይፈቅድለትም።
ባጭሩ የአማራው አላማ እራሱን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ወንድሞቹንም (በረጅም ጊዜ እቅዱ ምስራቅ አፍሪካንም) ጭማር ነጻ ለማዉጣት ነው። ካሁን በሁዋላ የአማራውና የሌሎች አናሳ ብሄረሰቦች ደህንነት ሳይጠበቅ ማንነታቸው የማይታወቅና በጠላት ተኮትኩተው ያደጉ ግለሰቦች ስልጣን ኮርቻ ላይ እንዲፈናጠጡበት አይፈቅድም። ስለዚህ ግዜው ለኢትዮጵያዉያን ምንም ያህል እልህ አስጨራሽ መስሎ የፈለገዉን ያህል አስቸጋሪ ቢሆንም የራሳቸውን ስራ መስራት አለባቸው። ኤርትራዉያን ወንድሞቻችንም ሌላ ችግር የሚፈጥር ነገር ዉስጥ ባይገቡና የራሳቸው ችግር ላይ ቢያተኩሩ ሁኔታዎች ሲረጋጉ አብሮ ለመኖር ይረዳናል። እንደረዱንም ይቆጠራል።