ኢትዮጵያዊነትን ምንም ያህል ቢታገሉት ታግለዉ አይጥሉትም
ኢትዮጵያዊነት በጥልቀት የገባቸዉ ጸሀፍት በብዛት ስለኢትዮጵያዊ ህዝባቸዉ ቢጽፉ ኖሮ እንደ ተስፋዬ አይነት አጭበርባሪዎች በኛ ላይ ብዕራቸዉን ለመምዘዝ ባልደፈሩ ነበር:: ኢትዮጵያዉያኖቹም ወገን ከሚጽፍላቸዉ ወርቃማ ጽሁፍ ይልቅ የባዕዳን ጸሀፍትን ጭራ እየተከተሉ ባዕዳን ለሚዘሩት መርዝ መማለላቸዉን መቼ እንደሚያቆሙ አይታወቅም::
ምናልባትም ወርቃማ ኢትዮጵያዉያን ጸሀፍት ስለ ታላቂቱ ሀገራቸዉ ኢትዮጵያ ለመጻፍ የማይበረታቱት ህዝቡ ወርቃማ ባለ አዕምሮዎችን ከማበረታታትና ለራሱ እንቁ ዋጋ ከመስጠት ይልቅ የባዕድ ጸሀፍትን ተከትሎ መኮብለል ስለሚወድ ይሆን?
ኢትዮጵያዉያኖቹ ስለራሳቸዉ ህዝብ ስለማይጽፉም የኢትዮጵያዉያን ጠላቶች ገብተዉ ስለኢትዮጵያዊዉ ህዝብ ይፈተፍታሉ:: ቢሆንም ከቀኝም ከግራም የቆመ ጠላት አንድ ነገር እርግጠኛ ይሁን:: ኢትዮጵያዊነትን ምንም ያህል ቢታገሉት ታግለዉ አይጥሉትም:: ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት ሚስጥራዊ ቃል ነዉ:: የምን ቃል የሚል ካለም:: የእግዚአብሄር ሚስጥራዊ ቃል::
ሸንቁጥ አየለ (shenkutayele@yahoo.com)
Leave a Reply
You must be logged in to post a comment.