እጅግ ጥልቅ የሆነ የኢትዮጵያውያን የስነ ህዋ እውቀት

እንደ ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አስተምህሮ መሰረት ፀሐይ: ከእሳት እና ከነፋስ ውህደት ጨረቃ: ከነፋስ እና ከውሃ ውህደት ከዋክብት ደግሞ ከነፋስና ከውሃ ውህደት ተፈጥረዋል።

ይሄ ተረት ተረት አይደለም። ይሄ እጅግ ጥልቅ የሆነ የኢትዮጵያውያን የስነ ህዋ እውቀት አልያም አገራዊ ሳይንስ ነው። ይህን ለመቀበል አልያም በዚህ ፍልስፍና ላይ ሰፊ ተግባራዊ ጥናቶችን ለማድረግ የነጮችን ይሁንታ መጠበቅ የለብንም። ከላይ የተጠቀሰውን እና ተያያዥ ኢትዮጵያዊ የስነ ህዋ እውቀቶች ላይ ዘመኑ በሚፈልገው መስፈርት ተግባራዊ ጥናቶችን በማድረግ አገራዊ እውቀቶችን ግራ ለተጋቡት የአለም ምሁራን ማስተማር የኛ ሀላፊነት ነው። በተለይ ወጣት ሙያተኞችና ተማሪዎች የጥንቱን አገራዊ እውቀት ወደአሁን እና ወደፊት ለማምጣት ትኩረት ማድረግ አለብን። ትኩረት ማድረግ አለብን! !!!!

ከላይ የተጠቀስኩት የስነህዋ እውቀት በሚከተሉት መፅሀፍት ላይ ተተንትኗል።
፩, የስነ ፍጥረት አንድምታ
፪, መፅሐፈ አክሲማሮስ

ተያያዥ መፃህፍት
√ መፅሐፈ ሔኖክ
√ አቡሻህር

እነኚህ መፃህፍት ለመግዛት ከሆነ በመንፈሳዊ መፃህፍት መደበር ለማንበብ ከሆነ ፒያሳ በሚገኘው የገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ/ክ ሰንበት ት/ቤት ቤተመፃህፍት ውስጥ ይገኛል።
ገዝታችሁ አልያም ቤተመፅሀፍት ገብታችሁ በማንበብ ለአበው እውቀት ዋጋ እንደምትሰጡ ተስፋ አደርጋለሁ።

‪#‎ራፋቶኤል‬

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.