በለገሰ ወልደሃና
የመላው የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ ) ፕሬዝደንት አቶ ማሙሸት አማረ ነሐሴ 22/2007 ዓም አራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በነጻ ቢለቀውም እስካሁን ድረስ በእስር ላይ ይገኛል ከአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጳፈውን ማስፈቻ የቅሊንጦ እስር ቤት ሀላፊዎች ሌላ ያልተዘጋ ፋይል አለ በሚል ሰንካላ ምክንያት አንለቅም መለታቸው ይታወቃል ዛሬ ነሐሴ 25/2007 ዓም ከጠዋት ጀምሮ እስካሁን ማለትም እስከ 11:00 ሰአት ድረስ ሌላ ያልተዘጋ ፋይል ያሉትን ለማጣራትና መፈቻውን ለማፃፍ ብዙ ተደገክሞ ነበር ግን ባለው ብሮክራሲ አልተጠናቀቀም
ቤተሰቡና የትግል አጋሮቹ አራዳ ሰበር ሰሚ ችሎት ( ሰባራ ባቡር ) ማሙሸት አማረ ውክልና ካልሰጣችሁ የሱን ክስ በተመለከተ እናንተን ማስተናገድ አንችልም ብለው ነበር አሁን ደግሞ ቅሊንጦ ማረሚያ ቤት የሚፈልገውን ይጻፋላችሁ ከዛ በዛ መሠረት ትስተናገዳላችሁ ብለዋል
የማሙሸትን መፈቻ ለማውጣት ውክልና ያስፈልጋል እያሉ ይቀልዳሉ በእስር ላይ ያለን ለዛውም ፍርድ ቤት ነጳ ያለውን ሠው ለማስፈታት የታሣሪ ውክልና የሚጠየቅባትና ይህንን የመሰለ የፍትህ ስርአት ያለባት ሀገር ኢትዮጵያ ነች::