የአማርኛ የወራት ስያሜና የግእዝ ስረወ ቃሉ
የአማርኛ የወራት ስያሜና የግእዝ ስረወ ቃሉ:- ከመስከረም እስከ ጳጉሜ የተሰየሙት ወሮቻችን
ስያሜያቸውን ከየት እንዳገኙ ያውቃሉ? እስኪ የሚከተለውን ይመልከቱ፡፡
የአማርኛ የወራት ስያሜ | የግእዝ ስረወ ቃሉ | ትርጉም |
መስከረም | መስ እና ከረም | ትርጉም መስ-አለፈ፤ ከረም-ክረምት፤ ክረምት አለፈ |
ጥቅምት | ጠቀመ | ሠራ፤ ጠቃሚ ጊዜ |
ኅዳር | ኀደረ | አደረ-ሰው በወርኃ አዝመራ ማሳ ውስጥ ለጥበቃ ማደሩን ይገልፃል |
ታኅሳስ | ኀሠሠ | መረመረ- በመኸር ወቅት የሰብል ምርመራን ያመለክታል |
ጥር | ነጠረ | ጠረረ- ብልጭ አለ፤ ነጻ፤ የፀሐይን ግለት ወቅት ያሳያል |
የካቲት | ከቲት | ትርጉም መክተቻ (እህልን) |
መጋቢት | መገበ | በቁሙ የሚመግብ (በጎተራ የተከተተው የሚበላበት) |
ሚያዝያ | መሐዘ | ጎለመሰ ጎበዘ ሚስት ፈለገ (ወርኀ ሰርግ መሆኑን ሲያጠይቅ) |
ግንቦት | ገነበ | ገነባ፤ ሠራ፤ ቆፈረ፤ ሰረሰረ (ለእርሻ የመሬቱን መዘጋጀት ያሳያል) |
ሰኔ | ሰነየ | አማረ (አዝርዕቱ) |
ሐምሌ | ሐመለ | ለቀመ (ለጎመን) |
ነሐሴ | አናሕስየ | የወሩ ስም አቀለለ፤ ተወ (የክረምቱን እያደር መቅለል ያሳያል) |
ጳጉሜ | ኤጳጉሚኖስ (ግሪክ) | ተጨማሪ ማለት ነው |
ምንጭ:- ግእዝ ይማሩ
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር (መቅድመ ባህረ ሓሳብ)
የባህረ ሓሳብ የቃሉ ትርጉም ፡፡
ባህረ ሓሳብ ከሁለት ጥምር የግዕዝ ቃላት የተወሰደ ሲሆን እነዚህም ” ባህር” እና “ሀሳብ” ናቸዉ ፡፡ ባህር ዘመን ማለት ሲሆን ሓሳብ ማለት ደግሞ ቁጥር ማለት ነው ፡፡ ኃጢአቱ ያልቆጠረበት ሰዉ ምስጉን መዝ፤ 31፡1
1.2 ባህረ-ሓሳብን ማንደረሰው ቢሉ ድሜጥሮስ የተባለ ሊከቅ ነዉ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መጀመሪያ የተነሳበት ቀን መጋቢት 29 እሁድ ነዉ ፡፡ ድሜጥሮስ ጌታችን ባረገ 207 ዓ.ም ተነስቶ ይኽንን ባህረ ሓሳብ ደርሶታል ፡፡ ድሜጥጥሮስ ከመነሳቱ በፊት የጥንት አባቶች ቁጥር እየተደበላለቀባቸዉ ትንሣኤን ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ሐሙስ ዓርብ ያዉሉት ነበር ፡፡
ይህን የተመለከተዉ ድሜጥሮስ ፆመ ነነዌ፣ አብይ ጾም ፣ ፆመ ሐዋርያት ከሰኞ በአለ ትንሣኤ ፣ ደብረዘይት ፣ በዓለ ሆሣዕና ፣ በዓለ ጰራቅሊጦስ ከእሁድ ፆመ ድኅነት እና ርክበ ካህናት ከረቡዕ ፣ በዓለ እርገት ከሐሙስ ፣ በዓለ ስቅለት ከአርብ ባይወጡ እያለ ይመኝ ነበር ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ነገር በመኞት ይፈጸማልን ከሌሊቱ 23 ከቀኑ 7 ሱባኤ ገብተህ እየዉ ብሎ አዘዘዉ፡፡አንድሱባኤ7 ቀንነዉ ፡፡
አዋጅ ፡-ማንኛዉምቁጥር ከ30ከበለጠ በ30አዉደ ወርኅ አካፍለን ቀሪዉን እኒዛለን ፡፡ የሌሊቱ ሱባኤ 23×7=161 ከዚያም 161÷30 =5 ቀሪ 11 ይህ ቀሪዉ ቁጥር 11 ጥንተ አበቅቴ ይባላል ፡፡ የቀኑ ሱባኤ 7×7=49 ÷30=1 ቀሪ 19 ይህ ቀሪው ቁጥር ጥንተ መጥቅዕ ይባላል ፡፡
1.3 ባህረ ሓሳብን ማን ይማረዋል ቢሉ ክርስቲያን ሁሉ ሊማረዉ ሊያስተምረዉ ይገባል ፡፡ በተለይም ካህናት ሊማሩት ሊያስተምሩት ይገባል ፡፡ባህረ -ሐሳብን መማር በዓላትን እና አፅዋማትን ለማወቅ ይጠቅማል፡፡
የኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር (የዘመን ቀመር)
ጥንት ከሚለዉ ይጀምራል ፡፡ ጥንትነቱም ከፍጥረተ ዓለም ፣ ከፍጥረተ ፀሐይ ፣ ከፍጥረተ ጨረቃ እና ከዋክብት ይጀምራል ፡፡ እግዚአብሔር ዓለምን የፈጠረዉ መጋቢት 29 በእለተ እሁድ በዘመነ የሐንስ ነዉ ፡፡ በዘመነ ዮሐንስ መሆኑ እንዴት ይታወቃል ? ቢሉ በዘመነ ብሉይ የወንጌለዉያን ስም የሚታወቅ ሆኖ ሳይሆን የሐድስ ኪዳን ሊቃዉንት ዘመናትን አስልተው ያገኙት ነዉ ፡፡
ለምሣሌ፡ አሁን ያለንበት 2008 ዓ.ም ዘመኑን ለማወቅ የሚከተለዉን ስሌት እንጠቀማለን ፡፡ 1ኛ 5500 ዓመተ ፍዳ + 2009 ዓ.ም =7509 ዓመተ ዓለም፡፡
2ኛ 7509÷4 (አራቱ ወንጌላውያን)=1877 =ቀሪ 1 በቀሪዉ ምክንያት ዘመኑ ዘመነ ማቴዎስ
አዋጅ፡– ቀሪዉ 1 ሲሆን ዘመነ ማቴዎስ ይሆናል ፡
2…….. ………..ማርቆስ
3………………… ሉቃስ
0………………..ዮሐንስ ይሆናል ፡፡
አዕዋዳት(መዘዋወሪያ)
ዓመተ ዓለም የሚሰፈርበት 7 አዕዋዳት አሉ ፡፡ እርሱም ፡- ሆነ እንላለን ፡፡
፩ኛ) አዉደ እለት ከሰኞ – እስከ እሁድ ያሉት 7ቱ ቀናት ሲሆኑ ሁልጊዜ በ7 በ7 ሲመላለሱ ይኖራሉ ፡፡ ጥቅማቸዉም ወራትን ማስገኘት ነው ፡፡
፪ኛ) አዉደ ወርህ፡- በፀሐይ ሙሉ 30 ቀናት በጨረቃ ግን አንድ ጊዜ 30 ሌላ ጊዜ 29 ይሆናል፡፡
፫ኛ) አዉድ ዓመት ፡- በፀሐይ 3651⁄4 ቀናት 365 ቀናት ከ15 ኬክሮስ ሲሆን በጨረቃ 354 ቀናት ከ22 ኬክሮስ ይሆናል ፡፡
፬ኛ) አዉደ አበቅቴ (ንኡስ ቀመር 19)፡- በ19 ዓመት ዜሮ (ወንበር ዜሮ) ስለሚሆን በ19 ዓመት አንድ ጊዜ አልቦ መጥቅ ወአልቦ አበቅቴ ይሆናል ፡፡ ምክንያቱም ወንበር ዜር መሆኑ ነዉ ፡፡
፭ኛ) አዉደ ፀሐይ (28 ዓመት)፡- ፀሐይ የተፈጠረችዉ በዕለተ ረቡዕ ፡፡ በየ28 ዓመቱ እለቱ እና ወንጌላዊው ይገናኙበታል ፡፡ ፀሐይ የተፈጠረችበት ቀን ረቡዕ ወንጌላዊው ማቴዎስ የሚገናኝበት ነው ፡፡
፮ኛ) አዉደ ማሕተም (ማዕከላዊ ቀመር 76ዓመት)፡- በ76 ዓመት አንድ ጊዜ አበቅቴው 18 መጥቅዑ 12 ይሆናል ፡፡ ቀጥሎ ባለው ዓመት ጨረቃ በምትወለድበት ጊዜ በ19 ዓመት አመት ለ4ቱ ወንጌላዉያን በማዳረስ መስፈሪያ ነው ፣ 19×4=76 ዓመት ፡፡
፯ኛ) አውደ ዓቢይ ቀመር (532 ዓመት ነው)፡- በዚህ ጊዜ 3 ነገሮች በአንድ ጊዜ ይገናኙበታል ፡፡ እነርሱም እነርሱም ፣ እለት ፣ ንዑስ ቀመር እና ወንጌላዊ ናቸዉ ፣ 7×4×19 =532 ፡፡
መደብና ወንበር ፡- መደብ ማለት ዓመተ ዓለም ለዓቢይ ቀመር እንደየድረሻቸዉ ከተካፈሉ በኋላ መጨረሻ የሚቀረዉ ተረፈ ዘመን ማለት ነዉ ፡፡ መደብ = ዓመተ ዓለም÷19 ቀሪዉ ምንጊዜም ከ19 በታች ይሆናል ፡
ወንበር =መደብ-1
የነበር ጥቅሙ አበቅቴና መጥቅዕን ለማግኘት የምንጠቀምበት የሒሣብ ሥሌት ነዉ ፡፡ ወንበር ለማግኘት ብዙ መንገዶችን መጠቀም እንችላለን ፡፡ የአባቶችን ስሌት ከ20ዉ አንድ በማለት ወይንም ዘመነ ብሉይ +ዘመነ ሀድስ በማለት ማግኘት ይቻላል ፡፡ ለምሣሌ ፡- የ2009 ዓ.ምን ወንበር ለማግኘት 5500 (ዘመነ ብሉይ)+2009(ዘመነ ሀድስ)÷19=395 ቀሪ 4 የህ 4 ቁጥር መደብ ተብሎ ይጠራል ፡፡ ስለዚህ ወንበር 4-1=3 ይሆናል ማለት ነዉ ነገር ግን በአጋጣሚ መደብ 1 ቢሆን ወንበር ዜሮ ይሆናል ምክንያቱም 1-1=0 ስለሆነ ነው እንድሁም ወንበር ዜሮ ሆነ ማለት መጥቅዕና አበቅቴ አልቦ ይሆናሉ ማለት ነው (አልቦ ማለት ምንም ነገር የለም ማለት ነው) በዚህ ጊዜ መስከረም 30 የዋለበትን እለት ተውሳክ ተጠቀም ፡፡
ልዩ ደንብ፡- በቀመር ስሌት መሰረት መደብ አንድ ሆነ ማለት ወንበር የለም ማለት፡፡ ምክንያቱም ከአንድ አንድ ሲቀነስ ዉጡቱ ዜሮ ስለሚሆን ፡፡
አበቅቴ እና መጥቅዕ
አበቅቴ የሚለዉ ቃል አበክቴ ከሚለዉ የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ተረፈ ዘመን ፣ ሰፍረ ዘመን ፣ ቁጥረ ሌሊት አምደ ሌሊት የሌሊት ሰፍር ቁጥር የሚገኝበት ማለት ነዉ ፡፡ አኃዛዊ አመጣጡም የፀሐይና የጨረቃ ዓመታዊ ልዩነት ማለት ነዉ ሥሌቱም 365-354,=11 ፡፡11 አበቅቴን እስከ 19ዓመት ድረስ በየዓመቱ ትርፍ የሚመጣ የስሌቱ ዉጤት ነዉ ፡፡
አበቅቴን በወንበር
የዬ ዘመኑን አበቅቴ ለማገኘት ያገኘነውን ወነበር በጥንተ አበቅቴ በማባዛት እና በማካፈል ማገኘት እንችላለን ፡፡ የሚከተለዉን ምሣሌ ተመልከት ፡- አበቅቴ=ወንበር × ጥንተ አበቅቴ(11)÷30
ምሣል፡- የ2009ዓ.ም ወንበር 4 ይሆናል ፡፡አበቅቴ= 4×11=44÷1 ቀሪ 14 ይህ ቀሪው 14 የ2009 ዓ.ም አበቅቴ ይሆናል ፡፡
የአበቅቴ ጥቅም
አበቅቴ ከእለታትና ህፀፅ ጋር ተደምሮ ሌሊትን የሰገኛል ፡፡ ህፀፅ ማለት ሀፀ ጎደለ ካለዉ የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ጉድለት ማለት ነው ፡፡ ይህ ጉደለት በፀሐይና በጨረቃ መካከል ያለዉ ልዩነት ማለት ነው ፡፡ ፀሐይ በየወሩ ሙሉ 30 ቀናት ስትዞር ጨረቃቃዘ ግን አነድ ጊዜ 29 አንድ ጊዜ 30 ትዞራለች ፡፡ በዚህ ምክንያት ከሁለቱ ወር አነድ ቀን በመጉደል ከፀሐይ ወደፊት ትቀድማለች በዚህ የተነሳ ህፀፅ አወራሀ እንደሚከተለዉ ይሆናል ፡፡
የመሰከረመና የጥቅምት ህፀፅ……1ነዉ
የህዳርና ታህሳስ ……………………..2 ነው
የጥር እና የካቲት……………………..3 ነው
የመጋቢትና ሚያዚያ …………………4 ነው
የግንቦት ናሰኔ …………………………5 ነው
የሐምሌና ነሐሴ……………………….6 ነው
አጠቃቀሙም አንደሚከተለው ነው ፡፡ ዕለት+አበቅቴ+እፀፅ
ለምሣሌ፡-የ2009 ዓ.ም የካቲት 23 ቀን የሚያድረው ሌሊት