የአድዋ ጦርንነትና የኢትዮጵያዉያን ድል
የአድዋ ጦርንነትና የኢትዮጵያዉያን ድል :- የካቲት 23 ቀን የቅዱስ ጊዮርጊስ ለት በ1888ዓ.ም (እደ ኤሮፓ አቆጣጠር ማርች 1 ቀን 1896 ዓ.ም) የዓለምን የፖለቲካ አቅጣጭ እና በዘርላይ የተመሰረተዉን ኢሰብአዊ ግንኙንትን የለወጠ የፍትህና የመከላከል ጦርነት ኢትዮጵያዉስጥ ኣድዋ በሚባለው ቦታ ላይ ተካሄደ። ጦርነቱ የተካሄደው በእብሪት ከኤሮጳ ባሀርኣቁአርጦ በመጣው የኢጣሊያ ጦርና ዓለም ከተፈጠረች ጀምሮ ሀግሩ በሚኖረውየኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ነበር።
ኢትዮጵያዉያን በጀግናና በብልህ ንጉሳቸው በዳግማዊ ምኒልክ ስር ተሰባስበው ዘመናዊ መሳሪያ ታጥቆ የመጣዉን ወራሪ ጦር ቅስሙን በመስበር የሃገራችውን ነጻነትአስከብረው ለመላው በባእድ አገዛዝ ስር ለሚማቅቀው የአለም ህዝብ ተስፋ እንዲኖረው አድርገዋል:: በዳግማዊ ምኒልክ ኢትዮጵያ እንድታድግና ዜጎች እንዲጠቀሙ አስደናቂ የልማት ስራወችን በማከናወን ህዝቡ በሰላምናበስርአት እንዲኖር ኣድርገዋል።
በሌላ በኩል በጠላትና በደጋፊዎቹ ጸረ ሰላም እና ጸረ እኩልነት ሃይሎች ጎራ ከፍተኛ ድንቃጤን ከመፍጠሩምበላይ አንዳንዶቹም ቂም ከመያዝ አልፈው በረቀቀ መንገድ ሀዝቡን በመከፋፈል ለመጉዳት ከፍተኛ ተንኮልሸረቡ:: የሁለተኛዉን የዓለም ጦርነት ኣጋጣሚ በመጠቀም በድጋሚ ወረራ አካሂደው አሰቃቂ የሆነ ኢሰብአዊድርጊት ፈጸሙ።
ከዚያ ወዲህ ያለው ትዉልድ ታሪኩን ኢንዳያዉቅና እንዳይጠነቀቅ የዉሸት ጽሁፎችን በሀገርዉስጥና በዉጭ ሃገር ሰዎች በማጻፍና በመበተን እልሀቸዉን በረቀቀ ስልት መወጣት እንድሚፈልጉ አሁንያለዉን የኢትዮጵያ ሁኔታ በጽሞና ለሚከታትል ስዉር ሊሆንበት አይችልም። እነዚህ ሁለት የእብሪት ዎረራወችታሪክ እራሱን ይደግማል የሚለዉን እንዳንረሳ ማስጠንቀቂያ ናቸዉ። ለዚህ ነው ታሪክን መማርና ማውቅያለብን በተገኘው ድል ለመኩራራትና ለመጠቀም ብቻ ሳይሆን ታሪክ እራሱን መድገሙ ስለማይቀርለመዘጋጀትም ጭምር ነው::
ይህ በብዙ ሺህ የኢትዮጵያዉያን መሰዋእትነት የተገኘው ድል ኢትዮጵያ አለኝታና ተስፋ ከመሆን አልፋ ለአፍሪካናለሌሎች በባርነት ቀንበር ለሚማቅቁ ህዝቦች የበኩሉዋን ድርሻ አበርክታለች። በዚህ የተንሳ ብዙ ሃገሮች ነጻሲወጡ የሰንደቅ አላማዋን ህብረ ቀለም ይወስዳሉ:: ጣሊያኖች በድጋሜ ኢትዮጵያን በወረሩበት ወቅትየኢትዮጵያኖችን ስነልቦናና ክብር ለመንካት ሰንደቅ አላማዋችንን ከተሰቀለበት ቦታ እያወረዱ ይረግጡትእንደነበረ በታሪክ ይታወቃል።
ምንም እንኩአን የኢትዮጵያ ህዝብ ባይቀበላቸዉም ዛሬ የባንዳ ልጆች (ወያኔች)ፋሽስቶች ካደረጉት ለወጥ አድርገው አባቶቻችን ተሰዉተው ያስረከቡንን ህጋዊና ታሪካዊ ሰንደቅ አላማችንን ባእድ አካል እመሃል ላይ በመለጠፍ የኢትዮጵያ ህዝ እዉቅና ያልሰጠዉን ባንዲራ በመስቀል ተደብቆ የቆየዉንጸረ ኢትዮጵያ ድርጊታቸዉን በዉስጥ አርበኝነት በመፈጸም የህዝቡን ስነ ልቦና ከመጉዳትም አልፈው የዲሞክራሲያዊ መብቱን በመንፈግና ነፍሰገዳዮችን በማሰማራት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣን በማካሀድ ላይ ናቸዉ።
በዚህ የተነሳ መልካቸዉን ቀይረዉ በመጡት የዉስጥ ከሃዲወችና በነጻነት ወዳዱ ሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ መካከል በአሁኑ ሰአት የከረረ ትግል በመካሄድ ላይ ነው።
የአድዋን ድል ኢትዮጵያዉያን ይደግሙታል:: ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!! አመሰግናለሁ!!