የዓማራ ህዝብ አቅጣጫ ፩: ራእይ

የዓማራ ህዝብ አቅጣጫ ፩: ራእይ

አማራው መደራጀቱን መቀጠል አለበት። የአማራው መደራጀትና መጠንከር ነው ለራሱ ለአማራዉም ሆነ ለሌሎች ነገዶች ወይም ጎሶች ዋስትና የሚሰጣቸው። የዚህ ሃሳብ አስኩዋል የአማራ መደራጀት ለአማራው ብቻ ሳይሆን ለሌሎቹም ደህንነት ሰላምና እድገት አስፈላጊ መሆኑን መግለጽ ሲሆን ሁለተኛ የኣስኩዋሉ ክፍል ከእንግዲህ ሌሎቹ ንገዶች ወይም ጎሶች ባይከተሉም አማራው መደራጀቱንና የራሱን ደህንነት ሰላምና እድገት በአተማማኝ ሁኔታ ላይ መሰረቱን ለማቆም የሚያደርገውን ትጋት የማያቆመው መሆኑን አጉልቶ ማሳየት ነው።

ወደ ዝርዝሩ (Details) ስንገባ የአማራው የወደፊት አቅጣጫና አካሄድ እንደ ኢትዮጵያ ሁኔታና እንደሌሎቹ ነገዶች ወይም ጎሶች አካሄድና ባህርይ እየታየ የሚቀየስ ይሆናል። አማራው ሌሎቹን ኢትዮጵያውያን ወንድሞቹን በምንም አይነት ለመጋፋት አይሞክርም። እንዲያዉም ከዚህ በፊት በረጅሙ ታሪኩ እንዳደረገው ከጠነከረ በችግር ጊዜ አጋዥ ይሆናቸዋል። አማራው ከማንኛዉ ነገድ ወይም ጎሳ በበለጠ ከሌሎች ነገዶች ወይም ጎሶች ጋር የተቀላቀሉ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦች አካሉ እንድሆኑ ስለሚያዉቅ በነሱም ደህንነት ላይ አይደራደርም።

ኢትዮጵያ ዉስጥ ከእንግዲህ የአማራዉን ደህንነትና ጥቅም የማያስከብር እንደ ወያኔ አይነት ጸረ አማራ ስርአት በምንም አይነት ሁኔታ በስልጣን ኮርቻ ላይ እንዳይንጠለጠል ማንናዉንም አስፈላጊ ነገር ከማድረግ ወደሁዋላ አይልም። ስሙን ነጥቀው ሊነግዱበት በሚቅበዘበዙ አስመሳዮች ወጥመድ ውስጥ እንዳይገባ ማእከሉን በቤተ ዓምሃራ ኢትዮጵያ ጥላ ስር አድርጎአል።

ማእከሉ ከሌሎች የታወቁና የታመኑ የአማር ድርጅቶች (ለምሳሌ ከሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት) ጋር ይመክራል አብሮም ይሰራል።ከአብራኩ የወጡ እዉነተኛ ልጆቹ መሪ ደረጃን በማይዙበትና በማይሳተፉበት መድረክ ወይም ከማንኛዉም አይነት ጸር ሰብአዊ ፍጡር ጸር አማራና ጸረ ኢትዮጵያ ከሆነ ሃይል ጋር አይተባበርም።

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.