ፉከራ
ስለ ፉከራ እና ሽለላ መንደርደሪያ
ኢትዮጵያዉያን አማሮች የታሪክ የባህል እና የስነጽሁፍ ባለጸጋዎች ናቸው። የተቀደሰዉን የግእዝ ቁንቁአቸዉን ለጸሎትና እግዚአብሄርን ለማመስገን ሲጠቀሙበት ዓማርኛን ደግም ለአስተዳደር ለአለማዊ ንግግሮች ጽሁፎች ለወታደራዊ ስርአት ልቦናቸዉን ለማነቃቃትና ለመራቀቅ ይጠቀሙበታል። ሽለላ ፉከራ እና እንጉርጉሮ ከጥንት ጀምሮ ለሸላዩና ለፎካሪዉ ብቻ ሳይሆን ለሚያዳምጠውና ለሚያየው ሰው ከፍተኛ የሆነ መነቃቃትን ድፍረትንና አስተዋይነትንም ጭምር የሚፈጥር ነው።
ከአድዋ ጦርነት በፊትም ሆነ በሁዋላ ፉከራ እና ሽለላ ተዋጊዉን በማበረታታት በማስተማርና በማጽናናት የኢትዮጵያ ህዝብ በነጻነት እንዲኖር የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ ያደረጉ የኢትዮጵያ ህዝብ ባለዉለታ ናቸው። ኢትዮጵያዉያን በሙሉ ይህንን ጠቃሚ ባህላችንን በወጉ መጠበቅና ማሳደግ ይኖርብናል። የጸረ ኢትዮጵያዉያን አላማ የአማራን ብቻ ሳይሆን የጠቅላላ የጥቁር አፍሪካዉያንንም ታሪክ ማጥፋት ስለሆነ ሸለላን እና ፉከራንም ክብራቸዉን ለመንካት ሲዉተረተሩ ቀንዳቸዉን በማለት ማሳፈሩ ተገቢ ነው። መልካም የንባብ ግዜ ይሁንላችሁ::
እርሳሱ ጥቁር አለንጋው መንታ፤
ቆላ ተኩሶ ደጋ የሚመታ፡፡
በቦንብ ገዳይ በሽንትርትሩ
በሽጉጥ ገዳይ ባጭር ስንዝሩ
ልበ ተራራ አሞተ ኩሩ
አካለ ቀጭን እግረ በባዶ፤
ያብረከርካል በስል ጎራርዶ፡፡
በላዩ ወጥቶ በዚያው ተራምዶ፤
ኣደራራቢ የሬሳ ነዶ፡፡
ዱብ ዱብ ባይ እንደበረዶ
አካለ ቀጭን እግረ በባዶ
በልጅነቱ በርሃ ለምዶ
እምቢ
ይምጡ ባይ ዪሰብሰቡ ባይ
ሲሰበሰቡ እንበላቸው ባይ
እምቢ
ቢብለጨለጩ እንደቅቤ ቅል
መተኮስና መምታት ለየቅል
ቢብለጨለጩ በልብስ በጫማ
ሊፈረጥጡ ድምጼ ሲሰማ
እምቢ!!!
በለው በለውና አሳጣው መድረሻ
ማእረግ አያውቅም ወንበዴና ዉሻ
ያመጣል መንገድ ይወስዳል መንገድ
አንድ የሚጠላ አንድ የሚወደድ
ሀገር አስነካሽ ልጅ አይወለድ
Leave a Reply
You must be logged in to post a comment.