የህወሃት ሴራና በአገው -በቅማንት – ዋግ ላይ የተደቀነው አደጋ

የህወሃት ሴራና በአገው -በቅማንት – ዋግ ላይ የተደቀነው አደጋ

የህወሃት ሴራ እና የአገው – ቅማንት – ዋግ ክልላዊ መንግስት ፅንሰት

የማይሳካው ግን ቀጣዩ የህወሃት የከፋፋይነት መርዝ የሙከራ እርሻ – አዊ ጎጃም
ከፌስ ቡክ የተገኘ………………………………(Ghion Sisay)

ለሀገር አንድነት፣ ለህዝቦች ሰላም እና ነገ የተሻለ ይሆናል በሚል ዕምነት በተለያየ መንገድ የምናውቃቸውን ሃቆች የጥቂት ሰዎች ምኞት እና ቅዠት ነው በሚል ከመግለጥ ተቆጥበን ቆይተናል፡፡ አሁን ግን ማፍረጥረጡ ተገቢ እና ወቅታዊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

ወቅቱ በኢትዮጵያ የቀን አቆጣጠር 2002 ዓ.ም. ክረምት ነው፡፡ እኔ እና አንድ ወዳጄ ስለሃገር፣ ስለ ስርዓቱ ተንኮል፣ ስለ ወቅታዊ ሁኔታዎች ወዘተ እንደ ሁሌው ስንወያይ አንድ አጥንት ድረስ ሰርስሮ የሚገባ ሃሳብ ጣል አደረገ፡፡ ጉዳዩ የተነሳው የዋግ ኸምራ እና የአዊ ህዝብ ትውውቅ በሚል በተከናወነ የባህል ኤግዚቢሽን ዝግጅት ጋር ተያይዞ ስንወያይ ነው፡፡ እኔ እና ወዳጄ ሁለታችንም የአዊ ቤተሰቦች ተወላጆች ነን ልዩነታችን የቦታ እና አስተዳደግ ብቻ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በወሬችን መሃል ‹‹በነገራችን ላይ ብአዴን ውስጥ ያሉ የአዊ ተወካዮች በኢህአዴግ ስር የሚሆን በአገው ስም የሚጠራ ፓርቲ ሁሉ ያስባሉ›› አለኝ፡፡

ብአዴንም ሆነ ኢህአዴግ ሁለቱም ለእኔ የህዝብ እና ሀገር ጠላቶች ስለሆኑ ከቁብ አልቆጠርኩትም ነበር፡፡ ‹‹ተዋቸው ይሄ ዙሮ ዙሮ የአማራን ህዝብ አንድና ጠንካራ አያደርገውም፣ ከግለሰቦች ጥቅም ባለፈ ፋይዳ የለውም አልኩት››፡፡ ቀጠልኩናም ‹‹በነገራችን ላይ ይህ የምናየው የአገው ህዝቦችን ማቀራረብ ምናምን የሚል ሃሳብ ከበስተጀርባ የተለዬ ዓላማ እንዳለው ውስጤ ይጠረጥራል አልኩት››፡፡ ወዳጄም‹‹ ምነው? ምን ችግር አለው?›› እኔም ‹‹የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ መልካም ነው፡፡

የአገውኛ ተናጋሪውን ብቻ ሳይሆን ጎጃምን ከወሎ ያስተሳስራል፡፡ ጠንካራ ህዝባዊ አንድነት ይፈጥራል፡፡ ነገር ግን ከህወሃት መሰሪ ባህሪ አንፃር የህዝብ አንድነት እና የአማራ ሃገር ህዝብ አንድነትን አይፈቅድም›› አልኩት፡፡ ‹‹እሽ ምን ጠረጠርክ?›› ሲለኝ ‹‹የበለጠ ያልተለመደ መከፋፈልና አለመግባባት ለመፍጠር ይመስለኛል፡፡ ምናልባትም በብአዴን ውስጥ በሰፊው በስልጣን ላይ ያሉ የዋግ ሰዎች የአዊን ድጋፍ ማሰባሰቢያና ስልጣን ላይ መቆያ ዘዴ ይሆናል፡፡›› አልኩት፡፡ ይህን ያልኩበት ምክንያት በወቅቱ የአማራ ክልል ስልጣን በብዛት በዋግ ተወላጆች የተያዘ ነው የሚል ሃሜትም እውነትም ስለነበረ ነው፡፡

በነገራችን ላይ ራሳቸውን የወግ ተወካይ አድርገው ክልሉን ይመሩ የነበ ሰዎች በአብዛኛው ወላጆቻቸው ትግሬዎች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ካሳ ተክለብርሃን፤ ከበደ ጫኔ፤ ታደሰ ጥንቅሹን መጥቀስ ይቻላል)፡፡ ጓደኛየም ቀበል አደረገና ‹‹ኧረ እንደውም አንድ ክልል የመመስረት ዕቅድ አለ፡፡›› አለኝ፡፡ ያኔ ውይይታችን ወደ ክረክር ከፍ አለ፡፡ ‹‹እንዴት ሆኖ ነው አዊ እና ዋግ አንድ ክልል የሚሆኑት በየት አልፈው ተዋስነው አልኩት፡፡ ደግሞስ ለምን አልኩት፡፡ አንተም ይሄን ዓይነቱን ነገር ትደግፋለህ? ገና ለገና አንድ ክልል ሲፈጠር ስልጣን አገኛለሁ ብዬ እኔ ይሄን አልደግፍም፡፡….›› በንዴት ብዙ ተናገርኩት፡፡ ‹‹እርሱም እንዲህ ዓይነት ውይይት አለ፡፡ መንግስትም [ህወሃት መሆኑ ነው] የሚደግፈው እንቅስቃሴ ነው፡፡ …ክልሉንም ለመመስረት የጎጃም አገውን ከጎንደር ቅማንት እና ዋግ ጋር በማገናኜት [የአገው-ቅማነት-ዋግ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት] ነው ›› ብሎኝ እርፍ አለ፡ ….በወቅቱ ከረጅም ጊዜ ጓደኛዬ ጋር ተደባበርን፡፡ አንድ ሁነን ሳለ በህወሃት ፖለቲካ ልንለያይ እንደምንችል ሳስብ ተበሳጨሁ፡፡ እኔ አገው ነኝ፡፡ ከአገው ቤተሰብ ተወልጃለሁና፡፡ እኔ አማራ ነኝ፡፡ አማራ ሁኜ አድጊያለሁና፡፡ በነገራችን ላይ በአገው ህዝብ ታሪክና ባህል ላይ ጥናት የማካሄድ ዕድሉን አገኝቻለሁ፣ ባህሉን ታች ወርጄ አቀዋለሁ፣ ሰርቻለሁ … እኔ የማቀው የአዊ ህዝብ ለእንደዚህ ዓይነቱ የህወሃት ሴራ ፈፅሞ እጅ የማይሰጥ መሆኑን ስለማቅ፤ ከላይ የማይሳካው ግን ቀጣዩ የህወሃት ህዝብን የመከፋፈል ዘመቻ ጎጃም አገው ምድር ነው ያልኩት፡፡ ምን አለ በሉኝ ይህ መከሰቱ አይቀርም፡፡

ህወሃት ሃሳቡ አገውን፣ ቅማንትን እና ዋግን ህዝቦች ከሌላው የአማራ ወገናቸው የተለዩ እንደሆኑ በቅጥረኞቻቸው እና የስልጣን ጥማተኖች ወሬ በማሰራጨት፣ ራሱን የቻለ ክልል ቢፈጥሩ ህገ መንግስታዊ መብታቸው እንደሆነ እና ለማንኛውም ችግር መንግስት [ህወሃት] ከጎናቸው እነደሚቆም በማሳመን ይህን አገር እና ህዝብ በታኝ ስራ ይፈፅማል፡፡ ይህንም በቅማንት ጀምሮታል፡፡ ቀጣዩ መርዝ ጎጃም አገው ምድር የሚረጭ ሲሆን በዋነኝነት ሰበብ የሚሆነው ብአዴን የሚለው ስያሜ ወካይ ስላልሆነ የራሳችንን የኢህአዴግ አጋር ፓርቲ እንመሰርታለን የክልሉም ሆነ የሃገሪቱ መንግስት በሚፈቅድልን መሰረት ራሳችንን በራሳችን ለማስተዳደር ክልላዊ መንግስት እንመሰርታለን በሚል ይሆናል፡፡ ይህን ሁሉ ከፈፀመ በኋለ በሚፈጠር ብጥብጥና ችግር ህወሃት አስታራቂ ዳኛ ሆኖ በመቅረብ የአገው-ቅማንት-ዋግ ሰርፅ ፈጥሮ ቀስ በቀስ የታላቋ ትግራይ ሳተላይት ግዛት ማድረግ ነው፡፡ ለህወሃት ከባዱ ፈተና የጎጃም አገው ኩሩ፣ ጠንካራ ስነ ልቦና ያለው ሲፎክር እንኳ ‹‹የአገዊቷ ልጅ›› የሚል፣ የህወሃትን ግፍ እና ተንኮል አብጠርጥሮ የሚያውቅ ከምንም በላይ በአገው ሚቶሎጅ ውስጥ አማራ እና አገው የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ሁነው መቅረባቸው ነው፡፡ ይህም ቀጣዩ የህወሃት መርዝ ጎጃም አገው ምድር ቢሆንም መርዙ ግን በጎጃም ላይ ሟርት፣ በአዊ ላይ አስማት ፈጽሞ አይሰራምና ገና ከወዲሁ ረክሷል፡፡ ፃ ርኩስ መንፈስ – ህወሃት – ውጣ ከታላቁ የግዮን ምድር፤ ቤተ አማራ፡፡

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.