ቅማንት፣ ሻንቅላ እና ወይጦ
የካም ነገዶች ከእስያ ወደ ኢትዮጵያ ከክርስቶስ ልደት በፊት 2713 ዓመት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ። በምድራችን ኢትዮጵያ ላይ ለ78 ዓመታት ከቆዩ በኃላ ወደ እስያ ሄደው ሶሪያን ለመያዝ ዘመቱ። ቢሆንም ግን በሴም ልጆች የሽንፈትን ፅዋ ተጎንጭተው ተመለሱ። ይህ ቢሆንም የካም ልጆች ወንዳማቸውን ኩግን አንግሰው እስከ ልጅ ልጆቻቸው 25 ነገስታት ኢትዮጵያን ለ743 ዓመታት አስተዳድረዋል። ታዲያ በነገደ ካም የአስተዳደር ዘመን ሶስት ነገዶች ወደኢትዮጵያ ገብተዋል።
እነዚህ ነገዶች ስማቸው ቅማንት፣ ሻንቅላ እና ወይጦ ይሰኛሉ። እነዚህ ሶስት ነገድ መነሻ ከነዓን ሲሆን አባቶቻቸው አርዋዲና፣ ሳኒ እና ሳምሪ ናቸው። አራተኛው የነዚህ ነገዶች ወንድም ሐማቲ ነው። ሳኒ የሻንቅሎች፣ አርዋዲ የቅማንቶች፣ ሳምሪ የወይጦዎች ሐማቲ የሽናሾች አባቶች ናቸው።
የቅማንት፣ የወይጦ ነገዶች ከመካከለኛው ምስራቅ ወደኢትዮጵያ ፈልሰው የገቡ ነገዶች ናቸው።
ለበለጠ መረጃ: ኢትዮጲስ የተሰኘውን የግርማ ዘውዴ መፅሐፍ ያንብቡ።
#ራፋቶኤል — with Amanye Paramera.