ወልቃይትን መሬቱን እንጂ …

ወልቃይትን መሬቱን እንጂ 
———————————-
(የቀለም ቀንድ ቅጽ 3 ቁጥር 24 ታህሳስ 26 ቀን2008)

ከአንድ ሳምንት በፊት የወልቃይት አማሮችየማንነት ጥያቄ አስተባባሪዎቹ ሊያገኙኝእንደሚፈልጉ ገልጸውልኝ በቀጠሯችን መሠረትተገናኘን። ለኢፌዴሪ የፌደሬሽን ምክር ቤትያስገቡትን የማንነት ጥያቄ ማመልከቻእንዲሁም 116 የት እንደደረሱ የማይታወቁወገኖቻቸውን ስም ዝርዝር የያዘ ሰነድ ፎቶ ኮፒሰጡኝ። ሰነዱ በራሱ ገላጭ ቢሆንምየአካባቢውን ተወላጆች መሠረታዊ ጥያቄበሚገባ ለመረዳት በዕድሜና በተመክሮ በሳልየሆኑ ሰዎችን ማነጋገሩ የተሻለ

መስሎ ስለተሰማኝ ሐሳቤን ገለጽኩላቸው።እነሱም ጥያቄየን ተቀብለው ከአንድ የ70 ዓመትአዛውንት ጋር አገናኙኝ።

ያገኘዋኋቸው አባት ታሪክን ጠንቅቀውየሚያውቁ የቤተ ክህነት ሊቅ ናቸው። እኚህአዛውንት ስለወልቃት ጠገዴ ብቻ ሳይሆንበኢትዮጵና ሱዳን ጉዳይ ላይ ያላቸው ዕውቀትከፍተኛ ነው። ይህ ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውየዕድሜ ባለጸጋው የወልቃይት ተወላጅ የነገሩንነው። የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ወንዱምሴቱም ጅግና ነው። በጣሊያን ወረራ ዘመንእናቶቻችን ልጆቻቸውንና ባሎቻቸውን አልጋሥር ጠመንጃ አቀባብለው እንዲደበቁያደርጋሉ። እነርሱ ደግሞ በርበሬ (ሚጥሚጣ)ድቁሱን በውኃ በጥብጠው ያስቀምጣሉ።ከዚያም የጠላት ወታደር በውበታቸው ማርከውወደ ቤት ያስገቡታል። የወልቃይቷን ሴት ውበትዓይቶ በስስት የሚገባው ፈረንጅ ፊትና ዓይን ላይያን የተበጠበጠ በርበሬ ይደፉበታል። ያ ወታደርሲደናበር አልጋ ሥር የተደበቀው ባለነፍጥአናቱን ብሎ እየሸለለ የጠላትን ትጥቅ ቀምቶጫካ ይገባል።

ኢሕአፓና ሕወሓት ታኅሣሥ 21 ቀን 1972 ዓ.ም.በወልቃይት ደጀና ከተባለ ቦታ ላይ ጦርነትገጠሙ። ‹‹ግንብ›› የተባለ ጎድጓዳ ቦታ አለ።ግንብ ውስጥ ሰው ቢጮህ ማንምአይደርስለትም። ጥይት ቢተኮስም ርቀት ቦታአይሰማም። ደጀና ላይ ሲዋጉ የነበሩ የኢሕአፓወታደሮች ሁሉ ግንብ ውስጥ ዶግ አመድ ሆኑ።አስከሬን ቀባሪ አጥቶ ለአሞራ ቀለብ ሆነ።የሰው ልጅ ለካ ያን ያክል ስብ ይሸከማል? ስቡቀልጦ የሚፈሰው መሬቱን ሁሉ አጥቁሮትነበር። የጥይት ድምጽ አፍኖ የሚይዘው ግንብአስከሬኖቹ የሚተፉትን መጥፎ ጠረን ግን አፍኖመያዝ ተሳነው። ድፍን ወልቃይትን በመጥፎጠረን አሰከረው።

ከሞት ያመለጡት የኢሕአፓ ሠራዊት አባላትወደ ሱዳን ተሰደዱ። የወልቃይት ጠገዴ ጣዕርከዚህ ጊዜ ይጀምራል። ሕወሓቶች ወልቃይትጠገዴን ዙረው ሲመለከቱ በመሬቱ ለምነትጎመዡ። በዚህ ምክንያት መሬቱን ለመውሰድሕዝቡን በልዩ ልዩ መንገድ ማሰቃየትናከአካባቢው ማፈናቀልን ሥራዬ ብለውተያያዙት። በዚህ መንገድ ሕወሓት ‹‹ኢሕአፓንአስጠልላችኋል›› በማለት በወልቃይት ሕዝብላይ መከራውን አንድ ብሎ ጀመረ። ያኔየተጀመረው መከራ አሁንም ይበልጥ ተጠናክሮቀጠለ እንጂ አልቆመም። ኢሕአፓንአስጠግተዋል ያላቸውን አማሮችን ቤትናንብረት ማቃጠል የጀመረው ሕወሓት ከዚያንጊዜ ጀምሮ የወልቃይት ወጣቶችን ሰበብእየፈለገ መግደል ሥራው ሆነ፤ የግፍ አገዛዝበሕዝቡ ላይ ተጫነ። ለዚህ ደግሞ የሱዳንመንግሥት ታላቅ ሚና ተጫውቷል።

አሁንም ቢሆን የሱዳን መንግሥት የጥፋትእጆች አልተሰበሰቡም። የወልቃይት ጠገዴአማሮች የተከፈተባቸው ጥቃት ሁለንተናዊናከብዙ አቅጣጫ ነው። የኢኮኖሚ፣የማኅበራዊና የሥነ ልቦናዊ ጦርነት ሰላባናቸው። በመንግሥት መሥሪያ ቤት ቅድሚያየሚሰጥ ከመሐል አገር ለሚመጣ የትግራይተወላጅ ነው። የወልቃይት ልጆች ትምህርትበአማርኛ መማር አይችሉም፤ ትምህርት ቤትውስጥ በአማርኛ ቋንቋ ማውራትምአይችሉም። ክልክል ነው። ሕወሓት በዚያአካባቢ መንቀሳቀስ ከጀመረበት ጊዜ አንሰቶከሰላሳ በላይ ለሚሆኑ ዓመታት የኢትዮጵያም ሆነየዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያላወቅ ብዙ በደልደርሷል። አያሌ የወልቃይት ተወላጆችተገድለዋል፤ ተሰደዋል። ቁጥራቸውንየማናውቀው ልጆቻችን የት እንደወደቁሳይታወቅ ደብዛቸው ጠፍቷል። የሕወሓቶችግፍ ወልቃይት ጠገዴ አማሮች የተፈጥሮስሜታቸውን እንኳ በወዱ እንዳይገልጹ ነውየሚያስገድዷቸው። የዳንሻ ከተማ ከንቲቫሕዝቡን ሰብስቦ ‹‹ልጆቻችሁ ስለምን አማርኛያወራሉ!›› በማለት በአደባባይ ሕዝቡንማስፈራራቱ የአደባባይ ሚስጥር ነው። አማርኛቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ‹‹የኢሕአፓ ቅሪቶች››በመባል ይታወቃሉ።

አማርኛ የሚናገሩ ሰዎች ምንም ዓይነት መብትየላቸውም። የሕግ አካላት የአማራ ተወላጆችንአያስተናግዱም። የወልቃይት ተወላጆችከትግራይ ብሔረሰብ አባላት ጋር ተጋጭተውወይም ሌላ በደል ደርሶባቸው ለሚመለከተውየፍትሕ አካል ቢያመለክቱ የፍትሕ አካሉለትግራዩ እንደሚያዳላ ማንም ያውቃል።የተለመደ ነው። ትግርኛ በአግባቡባለመናገራቸው በደል የሚደርስባቸውየወልቃይት አማሮች ብዙ ናቸው። ለናሙና አንድእናንሳ። የአካባቢው ሕዝብ ባህሉም ሥነልቦናውም ምርጫው አማራነት ነው። ሕዝቡለትግራይና ኤርትራ ቅርብ በመሆኑ እንደሌሎችበአዋሳኝ አካባቢዎች እንደሚኖሩ ሕዝቦችየተለያየ ቋንቋ ይናገራል። የዚህ ዓይነት ሁኔታበየትም አካባቢ ያለና ተፈጥሯዊ ነገር ነው።የድሬዳዋ ሕዝብ ከአማርኛ ሌላ ሶማሊኛምኦሮምኛም እንደሚናገር ይታወቃል።ኢትዮጵያውያን በሌሎች የአገራችንጥአካባቢዎችም እንዲሁ ነው። የወልቃይትጠገዴ ሕዝብም ከአማርኛ ሌላ ትግርኛይናገራል።

ዐረብኛ ቋንቋ የሚናገሩም ብዙዎች ናቸው።ሕዝቡ ትግርኛ ይናገር እንጂ የአካባቢው ትግርኛየተለየ ነው። ወደ አማርኛ በእጅጉ ይቀርባል።የትግራይ ብሔረሰብ አባላት ይህን በሚገባያውቃሉ። በዚህ ምክንያትም ብዙ በደል አለ።ትምህርት ቤት ሞክሼ የአማርኛ ፊደላትንየሚጽፉ ተማሪዎች ካሉ በጣም

ይወገዛሉ። ለምሳሌ ኀ፣ ሠና ፀ የአማርኛ ፊደላትናቸው ተብለው ስለሚታሰቡ መምህራንለፊደላቱ ያላቸው ጥላቻ የበዛ ነው።እንደሚታወቀው ጉራጌ ዞን ውስጥ ለምሳሌለኦሮሚያ ክልል ቅርብ በሆነው ሶዶ ወረዳውስጥ ብዙዎች ኦሮምኛ ቋንቋ ይችላሉ።ኦሮምኛ ስለሚናገሩ ኦሮሞ ናቸው በሚልወደኦሮሚያ ክልል ለመጠቅለል ጥረት ቢደረግምሕዝቡ ማንነቱን አሳልፎ አልሰጠም። መታወቅያለበት የብሔረሰቦች መብት ተከብሯል እየተባለድቢ በሚመታበት ዘመን የወልቃይት ጠገዴሕዝብ ያለታሪኩና ፍላጎቱ ወደትግራይ ክልልእንዲጠቃለል የተደረገው በሕወሓት ውሳኔበመሣሪያ አፈሙዝ ነው። ሕዝቡ ፈጽሞአልተጠየቀም፤ ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድልምአልተሰጠውም። አካባቢው በትግራይ ክልል ሥርእንዲሆን ከተወሰነ ጀምሮ የመብት ጥያቄየሚያነሱ ልጆቻችንን ስንቀብር ኖረናል።ጥያቄው ወደፊት እንዳይቀርብና ለአንዴናፋይሉን ለመጨረሻ ጊዜ ለመዝጋት ሲባልበሺህዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆችንበአያት ቅድመ አያቶቻችን ርስት ላይ በማስፈርየትግራይን የበላይነት ለመፍጠር ያልተሞከረነገር የለም። የሕዝባችን በደል ድርብ ድርብርብነው የምንልበት ምክንያት በደሉበባለመሣሪያው ሕወሓት የሚፈጸም በመሆኑእንደሌሎች ሕዝቦች ጥያቄ በኢትዮጵያሕዝብና በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድእስካሁን ጎልቶ ባለመውጣቱ ነው። ከቅርብጊዜያት ወዲህ የተሻለ ሁኔታ ቢኖርም ከደረሰብንበደል ጋር ስናወዳድረው በጣም የሚያሳዝንነው።

የሱዳን መንግሥት ለኢትዮጵያ የአጥንት ቲቢነው!

የሱዳን መንግሥት እኮ ለአገራችን የአጥንት ቲቪነው። የሱዳን መንግሥት የወልቃይትን አማሮችከሕወሓት ጋር እንዴት አድርገው እንደፈጇውበሚገባ እናውቃለን። ከ1972 ጀምሮ ሕወሓቶችአስቀድመው የሚያጠና ሰው ይልካሉ። ሰላይመሆኑ ነው። አስቀድመው የሚመጡት ሰላዮችበራሱ መተማመን ያለውንና ቆይቶምለሕወሓቶች ተቃውሞ ያነሳል የሚሉትን ወጣትበስም ዝርዝር ይልካል። ሕወሓቶች ለሱዳኖችይናገራሉ። ሱዳኖች መኪና ይዘው ይገባሉ።ወጣቶቹን ይይዙና ወደ ግዛታቸው ይወስዷዋል።‹‹ዛሬ እከሌ ጠፋ! ዛሬ ከሌ በሱዳኖች ተወሰደ!››ሁልጊዜም የሚሰማ እሮሮ ነው። ይህ እሮሮበሕወሓቶች የሽፍትነት ዘመን ብቻም ያቆመአይደለም። እስካሁን ድረስ የቀጠለ ደረቅ ሐቅእንጂ። ሱዳን ድንበር ከገቡ በኋላ በጥይትተደብድበው ይገደላሉ። ትልልቅ ከተማዎችአደባባይ ላይ ይሰቀላሉ። ከተማ አደባባይ ላይየሚሰቀሉትን በተመለከተ ሱዳኖቹ የሚሉት‹‹ሐበሻ ራሱን አጠፋ›› ነው። ሕወሓቶችራሳቸው የወልቃይት አማራ ወጣቶችን ጉድጓድእንዲቆፍር ካደረጉ በኋላ በቆፈሩት ጉድጓድይቀብሯቸዋል። ‹‹የትግሬ እናት ሐዘን ተቀምጣአንተ ጠግበህ ትበላለህ?›› በማለት ውኃ በቀጠነይገድሏቸዋል።

ሕወሓቶች እንዲህ ይላሉ። መሬቱ እንጂ ሕዝቡአያስፈልገንም። የሱዳን ዜጎች ድንበር አካባቢየሚያገኟቸውን ኢትዮጵያውያን ሳይጠይቁየማያልፉት ነገር አለ። ይኸውም ‹‹አማራ ነህትግሬ!›› የሚል ነው። ለሱዳኖች ሰው ማለትትግሬ ነው። አማራ የሱዳን ጠላት አድርገውይቆጥሩታል። የሱዳን ደህንነቶች የፈለጉትንየወልቃይት ተወላጅ በፈለጉት ጊዜ መጥተውመውሰድ ይችላሉ። የህወሓትም ደህንነቶችእንዲሁ። የወልቃይት ተወላጆች ወደ ሱዳንምቢገቡ እዚህ ቢቀመጡ ያው ነው። የወልቃይትተወላጆችን ግፍ ሊያስረዳ የሚችል አንድ ምሳሌእንጥቀስ። ቄስ ተገን እንየው የሚባል ካርቱምእስጢፋኖስ የሚያገለግል የወልቃይት አማራአለ። ቄስ ተገን በቤተ ክህነት ትምህርት ከዚህቀረህ የማይባል ምሁር ነው። በግዕዝከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ በዐረብኛ ደግሞከግብጥ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያኖች ይቀድሳል።ቄስ ተገን ያለውን ለአገሩ ልጆች አካፍሎይበላል። ሕወሓቶች ቄስ መስፍን አገር ውስጥላሉ ለሚማሩ ልጆች ገንዘብ እንደሚረዳደረሰቡት። ለተቸገረ ገንዘብ መለገስየሚያስመሰግን እንጅ የሚያስወቅስ ሆኖአልነበረም። ባለፈው መጋቢት ወር 2007 ዓ.ም.ካርቱም የተላከ የወያኔ ደህንነት ይዞት መጣ።ማዕከላዊ እስከ ጥቅምት 2008 ዓ.ም. ከማንምከምንም ጋር ሳይገናኝ ጨለማ ቤት አቆይተው‹‹ለማንም እንዳትናገር›› ብለው ለቀቁት። ቄስተገን ምንም አማራጭ ስላልነበረው አሁን ወደካርቱም ተመልሷል። የወልቃይት ልጃገረዶችበትምህርት ቤት የሚደርስባቸው አበሳምከፍተኛ ነው። ሐሙስ ሐሙስ ሴት ተማሪዎችየመምህራንን መኖሪያ ያጸዳሉ የሚባል ያልተጻፈሕግ ነበር። ገና ለአቅመ ሔዋን ያልደረሱ ሕፃናትየመምህራኖቻቸውን ቤት ማጽዳት በተራሁልጊዜ ሐሙስ ‹እነ ጋሽዬ› ቤት ይሄዳሉ።ሕፃናቱ በመምህራኖቻቸው ይደፈራሉ።ያረግዛሉ ይወልዳሉ። በሕግ ሊያገቡ የታጩልጃገረዶች ሁሉ እየተደፈሩ ያገባሉ። ምክንያቱደግሞ አማሮችን ትግራዊ ለማድረግ ብቻ ነው።የወልቃይት አባቶች ተጨነቁ። ልጆቻቸውንትምህርት ቤት ላለመላክ ወሰኑ። በዚህ ጊዜደግሞ ለትምህርት የደረሰ ልጁን እቤትያስቀመጠ ሰው ይቀጣል የሚል ሕግመጣባቸው። ወላጆች አሁን ሌላ አማራጭፈለጉ። ‹በመምህራን› ልጆቻቸውከመደፈራቸው በፊት በልጅነታቸው መዳር።መጨነቅ ነው። ይህም ሌላ ጣጣ አስከተለ።በሴቶችና ሕፀናት ጉዳይ ‹‹ያለ ዕድሜ ጋብቻ››በሚል ክስ ይመሰረትባቸዋል። ያለ ዕድሜያቸውበሚደፍሯቸው መምህራን ላይ ግን ማንምምንም አይልም። ይህ ሁሉ ችግርየሚደራረብባቸው ወልቃይቴዎች ያላቸውአማራጭ ሁለት ብቻ ነው። አንደኛውልጆቻቸውን ወደ ጎንደርና ሌሎች አካባቢዎችወስዶ ማስተማር ሲሆን ሁለተኛው ግንየመምህሮቹን ‹‹ዲቃላ›› ማሳደግ። መታወቅያለበት አንድ መሠረታዊ ነገር አለ። የወልቃይትጠገዴ ሕዝብ ጥያቄ የመልካም አስተዳደርጥያቄ አይደለም። ይህ ማለት ሕዝቡ የመልካምአስተዳደር ችግር የለበትም ማለት አይደለም።በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች እንደሚታየውበእኛ አካባቢም የመልካም አስተዳደር ችግረአለ። የእኛ ዐቢይ እና የሕወሓት ሰዎች የቱንምያህል ቢገድሉንና ቢያሳድዱን የማንተኛለት፤ እኛመፈጸም ባንችል ጉዳዩን ለልጅ ልጆቻችንየምናወርሰው ጥያቄ የማንነታችን ጉዳይ ነው።አማሮች ነን። ትግራይ አይደለንም።

የደረሰብንና እየደረሰብን ያለውን ያልተነገረለትበደል ኢትዮጵያውያንና የዓለም አቀፉማኅበረሰብ እንዲገነዘብልን እንፈልጋለን።

(ማሳሰቢያ፡ ይህ ጽሑፍ ለሕትመት ከመብቃቱበፊት የሱዳንን ኢምባሲ የሚሉት ነገር ይኖርይሆን ብለን ለመጠየቅ ብንሞክርም ኢምባሲውሊያናግረን ፈቃደኛ አልሆነም)

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.