ትንሽ ስለ ሰምና ወርቅ (ቅኔ)

ኢትዮጵያ ዉስጥ ብዙ የጥበብ ስራወችና ገና ያልተጠቀምንበት እዉቀት እንዳለ ጥናቶች ብቻ ሳይሆኑ በግልጽ የሚታዩ ተጨባጭ ማስረጃዎች ይመሰክራሉ ። ከነዚህ የጥበብ ስራወች አንደኛዉ የስነ-ፊደልና የስነ-ጽሁፍ አፍላቂ መሆናችን ነው።  ቀደምት አባቶቻችን ከማንም በፊት ፊደሎቻችንን ቀርጸው ሰባት ናጋሪወችን በመለየት በቃል የሚሰማው ማንናዉም ድምጽ እንዲነበብ በማድረግ ታሪቸውን ሃይማኖታቸውንና ባህላቸውን ከመጠበቅ አልፈው እጅግ ጥልቀት ያላቸዉን እዉቀቶች ለኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን ለመላው አለም ጭምር ጠብቀው በማስቀመጥ ለትዉልድ አስተላልፈዋል።

በአማርኛ ስነጽሁፍ ዉስጥ አንዳንድ ሆሕያትን በድምጻችን በማጥበቅና በማላላት ወይም ቃላትን አንድ ላይ በማገናኘት በመለያየት ትርጉማቸዉን እንዲለዉጡ ማድረግ ይቻላል። በዚህ የተነሳ ሚስጥረኖች አዉቀው  (ሆን ብለው) ተራ ተናጋሪዎች ደግም ሳያዉቁት አዳማጩ ያልተባለ ነገር አእምሮው ዉስጥ እንዲቀረጽ ያደርጋሉ። የአማርኛም ለዛ የሚንጸባረቀውም እዚህ ላይ ነው።

ጥንታዊዉንና ታሪካዊዉን ቅርሳችንን የጎደለዉን አሙአልቶ ስህተቱን  አርሞ ሌሎች ሃገሮች እንደሚያደርጉት ማሻሻልና ማሳደግ እንጂ መናቅና መተው ወደሁዋላ ያስቀራል እንጂ አያሰለጥንም። ይልቁንም ያለንን ጥሩ ነገር ከጊዜው ጋር በተግባር እያዋሃድን ጥበብን በመቅሰም ና መጭዉን ትዉልድ የአባቶቹን እዉቀት በማስጨበጥ በማንነቱ እንዳያፍርና ሃገር በቀል የሆነዉን እዉቀት እንዲጠቀምበት መርዳት ይኖርብናል

ሰምና ወርቅንና ሌሎች ግጥሞችን ለማንበብ መገናኛዉን ይጠቁሙ 

ከፍ ዓለ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.