አባባሎች በግጥም
እሳትና እራት
አማትና ምራት
ድር ቢያብር
አንበሳ ያስር
ያላወቁ
አለቁ
እባብ ለባብ
ይተያያሉ ካብ ለካብ
አንቺዉ ታመጪዉ
አንችዉ ታሮጪዉ
ምከረዉ ምከረዉ
እምቢ ካለ መከራ ይምከረዉ
ሳይከካ
ተቦካ
ቀና ሲታጣ
ይመለመላል ጎባጣ
ያለ አንድ የላት ጥርስ
በዘነዘና ትነቀስ
የምታቦካው የላት
የምትጋግረው አማራት
የጅብ ፍቅር
እስኪቸግር
በቅሎ ግዙ ግዙ
አንድ አሞሌ ጨው ላያግዙ
ይቀጥላል
1 2
Leave a Reply
You must be logged in to post a comment.