ማፈሪያዎቹ የአፍሪካ መሪዎች (ማሙሸት አማረ)
ህዝባቸዉን በክህደትና በውሸት የሚመሩት የቅድም ስማቸው የአፍሪካ አንድነት ድርጀት የአሁኑ መጠሪያቸው የአፍሪካ ህብረት የሆነው የአፍሪካ መሪዎች ማፈሪያዎች፣ የታሪክ ጠላቶች፣ የእውነት ገዳዮቶች፣ እራስ ወደዶችና በሌላቸው ታሪከ ባለታሪክ ለመሆን የሚዳዱ የአምባገነን ስብስብ ና ቸው ፡፡
እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አብዛኞቹ የአፍሪካ ሀገሮች ከባርነት ቀንበር ዉስጥ የወደቁ ነበር ፡፡ ታዲያ የዛሬው አፍሪካ ህብረት ቀድሞ ስሙ አፍሪካ አንድነት ድርጅትን ለመመስረትና አፍሪካ ዉያንን ነጻ አዉጥቶ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ጉዳይ፣ በፖለቲካ እና በተለያዩ ዘርፎች የሚደርሰባቸውን ማናቸውንም ችግሮች በጋራ ለመታገል፣ ለመቋቋም እና ብሎም አፍሪካዊ ወንድማችንነትና እህትማማችነትን ለማጠናከር ድርጅቱ እንዲመሰረት ኢትዮጵያ ከፍተኛውን አስተዋጽኦ ማበርከቷ የነበረ፣ ያለና፣ ወደፊትም የሚኖር እውነት ነው፡፡
ኢትዮጵያን የማያውቋት የታሪክና የእውነት ጠላቶቹ የአጼ ኃይለ ስላሴን መለኪያ የማይገኝለትንአ ስተዋጽኦ እንዳልነበረ በማደረግ ታሪኩን ክደው እውነትንም ገደሉ፡፡ ያንን እውነተኛ ታሪክ መሪ ተብዬዎች ሳይናገሩ፣ ሳይጽፉ እንዲሁም ምስክርነታቸውን ሳይሰጡ ዝም ማለታቸው የአፍሪካ ህብረት ስብስቦችን ማንነት ቁልጭ አድርጎ አሳይቶአል፡፡
ኢትዮጵያውያዊዉ ንጉስ አጼ ኃይለስላሴ በአፍሪካ ህብረት ምስረታ ላ ከማንም መሪ የበለጠ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ይካዳል እንዴ? ከወንድማማችነትና ከእህትማማችነት የሚመልጥብን ሊኖር አይገባም ማለታቸው ይክዳል እንዴ? የጋራ ጠላታችንን በጋራ ቆመን መመከት አለብን ማለታቸው እውነት አይደለም አንዴ? የያኔው የአፍሪካ አንገድት ድርጅት የዛሬው አፍሪካ ህብረት መኖር ምክንያቱ የእርሳቸው ጥረት መነሻ ሆኖ አይደለም እንዴ የአፍሪካ አንድነት ጽ/ቤት ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ከተማ መቋቋሙ? የኢትዮጵያና የንጉሱ አስተዋጽኦ የጎላ ድርሻ በመሆኑ አይደለም አንዴ? ኢትዮጵያ ለነጻነት የአደረገችው ከባድ ትግል ቅኝ ገዥዎችን አሸንፋ አፍሪካዊያን ብሎም ጥቁር የሰው ዘር በሙሉ በኢትዮጵያዊያን አሸናፊነት አልኮሩም እንዴ? ሁሉም አፍሪካዊያን የኢትዮጵያን ተጋድሎ በመከተል አፍሪካዊያን ቀኝ ገዥዎቻቸውን ለመታገል አልወሰኑም? ኢትዮጵያንስ ስለአፍሪካዊያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የነጻነት ትግል የሚቻለውን ሁሉ አላደረግንም?
የሁሉም አፍሪካዉያን የነጻነት ፈር ቀዳጂ የሆነችውን ቀንዲል የኢትዮጵያን አረንጓዴ ቢጫና ቀይ አላማ በተለያዩ አቀማመጥ በመጠቀም የነጻነታቸው ተምሳሌት መሆኗን አልመሰከሩም እንዴ? አብዛኛው አፍሪካ ሀገሮች መንገዶች ላይ የንጉስ የአጼ ኀይለስላሴ ሀውልት አልቆመም እንዴ? መንገድና ትምሀርት ቤት በስማቸው አልተሰየም እንዴ? ያአፍሪካ ሀገሮች ህዝብ በአንድ ድምጽ “ Father of Africa ” የአፍሪካ አባት እያሉ አልጠሩአቸውም እንዴ? ታዲያ ሀሳቡን አፍልቀው ወደ ተግባር እንዲለወጥ ላደረጉት አስተዋጽኦና ኢትዮጵያ በዓላም ላይ ተቀባይነት ታማኝነትና ክብር አይደለም እንዴ? አፍሪካ አንድነት ድርጅት ዋና ጽ/ቤት አዲስ አበባ እንዲሆን የተወሰነውስ በሳቸዉ ድካም አይደለምን?
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ስሙን ቀይሮ የአፍሪካ ህብረት ቢባል የተመሰረተበትን አላማ ይስታል እንዴ? የአፍሪካ ህብረት አዲስ ፎቅ ቢሰራ ይዞት የተነሳውን መደጋገፍ ፣የመተባበር ፍላጎት በአዲስ ይቅይረዋል እንዴ? ይህ ከሆነ ዘንድ በአዲሱ ፎቅ ጊቢ ውስጥ የመስራቾች የስራ መገለጫ ሀውልት ሲቆምላቸው የንጉስ ነገስት አጼ ኃይለስላሴ ሀውልት መከልከሉ ወይም ሳይቆም መቅረቱ ከአሀዲነት ወይም እውነትን ገዳይነት ወይንም ፍጹም የሆነ ጠላትነት ሌላ ምን ሊሰጠው ይችላል?
እንዴት አንድ እውነተኛ ወይም ለምስክርነት የሚበቃ አፍሪካዊ መሪ ይጠፋል? ኢትዮጵያን የያዘው የወያኔ ቡድን አጼ ኃ/ስላሴን የጎዳ መስሎት ይሆን እንዴ የኢትዮጵያን ታሪክ የሚያዋርደው?
“እውነት ትመነምናለች እንጂ አትበጠሰም” ኢትዮጵያውያን በአፍሪካዊያን መሪዎች አፈርን::
Leave a Reply
You must be logged in to post a comment.