ሰምና ወርቅ
ባላባት መሆኑን አናውቀውም እኛ፣
መተማ ላይ ኗሪ ይኸን ወሰንተኛ
ባላገር ነው ጥሩ ስልሽ፣
ለምን ከተማ መጣሽ
ባልሽ ቢለምንሽ ይዞ ገላጋይ፣
ዓለም በቃኝ ብለሽ ትሄጃለሽ ወይ
ሰኞም ገበያ ነው እግር ላደረሰው፤
ቦሩም ገበያ ነው እግር ላደረሰው
ሁልጊዜ ባንቻሮ እንዴት ይሞታል ሰው
እንደምን አርገሽ ነው ልቤን የረታሽዉ፤
ከቤት አሶጥተሽ እደጅ ያሳደርሽዉ፤
ባለ ብዙ ዘዴ መለኛ ነሽና፤
መጥተሽ ቶሎ ዳብሽኝ ህመሜ ሳይጠና
እንደምን አድርገሽ ትራመጃለሽ
የኛን ሃገር አልፈሽ ሳላይሽ ያደርሽ፧
ከበሬና ከላም የቱ ይወደዳል
ለመወደድ እማ በሬ ይወደዳል
ለወተቱዋ ሲባል ልቤስ ላም ይወዳል::
ምን አይነት ቄስ ናቸው ተስካር የለመዱ
አስታርቁኝ ብላቸው ፍታት ብለው ሄዱ
ድጉዋ ጾመ ድጉዋ ተቀምጦ ከቤቴ
አወይ አለማወቅ ሳልማር መቅረቴ
እንኩዋን ነአኩተከ በስማም ቸገረኝ
ዳዊት እንዴት ተማርክ እባክህ ንገረኝ
ያባቴን አገር ደጋዉን
ከልክየ ነበር ሳሩን
አበሉት አሉኝ ዘመዶቼ
እርሻ ማረጌን ትቼ
ድጉዋ ጾመ ድጉዋ ተቀምቶ ከቤቴ
አወይ አለማወቅ ሳልማር መቅረቴ
≈ ≈ ≈ ≈ ≈
ከዚህ በታች ያለዉ ግጥም ከአቶ ሰዉ ማለት ይኸነዉ የተገኘ ነዉ።
ማን አስተማራቸዉ ይህን ሁሉ ሚስጥር
ማን ነግሮአቸው ነበር ነገር እንደሚያደክም
በነጠላ ሲሆን እንደማያስደምም
እነዲህ እንዲያወሩ
በምሳሌ አድርገው ነገር እንዲያበራሩ
ሚስጢር እንዲገባን አእምሮ እንዲፈተን
እያስተማረና እያጨዋወተን
ሀሳብ እንዲበተን ደግሞ እንዲተነተን
አንድ ቃል ብዙን ወክሎ እንዲናገር
ማን አስተማራቸዉ ዪህን ሁሉ ሚስጥር?
ሰምና ወርቅ ግጥም | ሰም | ወርቅ |
ለባላንጣዎች ዘንቦላቸው
አምሮላቸዋል መከራቸው፡፡
|
አዝመራቸው
ጥሩ
ሆኗል::
ሰብሉ አምሯል :: ፍሬው አስደስቷል፡፡ |
መከራ
ስቃያቸውን
በሚገባ
ተቀብለዋል ::
ይበጅ ያድርግ፡፡
|
ለእኛም ደግሞ አማረ ፡
ደመናም ሆነ አልቀረ፡፡
|
ደመናው አንዣቦ ተረግርጎ አልቀረም ዝናም ጣለ ፡፡ |
ደማችን
መና ሆኖ አልቀረም::
ደማችንን ተበቀልን::
ተጠቅተን በከንቱ
አልቀረንም::
ዳኝነት አገኘን ፡፡
|
ለኃይለኛ ሴት ለመቆጣ ፡
ምነው መካሪ ባል ታጣ ፡፡
- ሰም- መካሪ አስታራቂ ሽማግሌ አይጥፋ አይታጣ ፡፡
- ወርቅ- ገስጾ መክሮ የሚያኖር ባል ባይታጣ ባይጠፋ ደግ ነበረ ፡፡
ለወልድ አብነት አለው ፡
ገድሎ ማዳኑን አየነው ፡፡
- ሰም- ወልድ ከሞት የሚያድን መድኃኒት አለው፡፡
- ወርቅ- ወልድ አብን ያየ እኔን አየ እንዳለው ከአብ ጋራ እኩልነት አለዉ ፡፡
ለጌታ አድሬ እነዴዋዛ ፡
አንድት ላም እነኳን ሳልገዛ ፡
ምን ይለኝ ይሆን ዘመድ፡
ወተት ብዬ ብሄድ፡፡
- ሰም- ለአንድት ላም እንኳን ሳልበቃ ወተት ፍለጋ በሄድ ከቶ ሰው ምን ይለኝ ይሆን ፡፡
- ወርቅ- በችግር ምክንያት አገር ጥዬ ብዞር ብንከራተት ወተት በዬ ብሄድ ከቶ ዘመድ ምን ይለኝ ይሆን ፡፡
ላም ገዝቼ ጥገት፡
እጠጣ ብዬ ወተት፤
ቅሉ ተሰብሮ አዝናለሁ ፡
በምናልባት አለሁ ፡፡
- ሰም- ወተቱን በምን አልበዋለሁ ዕቃ አጣሁ ማለቢያ ጮጮ ፣ ተቸገርኩ ፡፡
- ወርቅ- በምናልባት አለሁ ድንገት ይሆንለኛል ብየ ተስፋ በማድረግ በምኞት ተቀመጫለሁ ፡፡
ልብሴም አለቀ ለይ ታቹ ፡
የኔም ዘመዶች ሰለቹ ፣
ክርና መርፌ አገኘሁ ፤
ጠቃሚ ሰው አጣሁ ፡፡
- ሰም- ጨርቅ የሚጥፍ ልብስ የሚሰፋ ሰው ተቸገርኩ
- ወርቅ- ረዳት ወገን የሚጠቅመኝ አጋር አጣሁ ፡፡
ልዑል መኰንን ከልምድህ ፡
አንዳንድ እያለ ቀረልህ ፣
ዘንድሮ ግንቦትን ወዴት ዋልህ ፡
አምናስ ዓለም ማያ ነበርህ ፡፡
- ሰም- ባለፈው ዓመት ዓለም ማያ ከሚባለው ቦታ ነበርህ ከዚያ ተይተሃለ ፡፡
- ወርቅ- ልዑል መኰንን መደሰቻችን የኑሮ መጠገኛችን ነበርህ ተድላ ደስታን ዓለምን የመናይብህ ነበርክ ፡፡
ሐምሌ በባተ በሰባት ፡
ሥላሴ መጥተው ከሱ ቤት ፣
አብርሃም ልጁን መረቀው ፡
ና ተባረክ አለው ፡፡
- ሰም- ና ተባረክ በረከት ተቀበል ተመረቅ ብሎ ጠራው ፡፡
- ወርቅ- አብርሃም ልጁን ይሥሐቅን ና ተሠዋ ፡ ታረድ አለው ፡፡
ሄደ ነበረች ያች ገረድ ፡
ውሃ ልትቀዳ ለዘመድ ፣
ውላ መጣች አዘያው ሰብራ ፡
እዩት የሰው ስራ ፡፡
- ሰም- ገረድቷ የተውሶውን እንስራ ሰብራ መጣች ፡፡
- ወርቅ – እዩት የሰውን ስራ የሰውን ተፈጥሮ አስተውሉ ሞቱን ከንቱነቱን ግብዝነቱንም ተመልከቱ ፡፡
መልካም አገር ጎነደር ፡
ቤተ -ክርስቲያን ስሞ ለመኖር ፣
አይቀርምና መዳኘት ፡
ከተመሰው መግባት ፡፡
- ሰም- ዳኛ ፍለጋ ወደከተማ መግባት ግድ ነው ፡፡
- ወርቅ – ምንም ቢሆን ከተማሰ ከተቆፈረ መቃብር መግባት አይቀርም ፡
መልካም አታክልት አየሁ ፣
እኔም አጸድቃለኁ ፡፡
- ሰም – አትክልት አለማለሁ እተክላለሁ ፡፡
- ወርቅ- እኔም ቢመጠውቱኝ አስጠቅማለሁ ለነብስ እሆናለሁ ፡፡
መልካም ነበረ ጠጅሽ ፤
ምነው አይጥም ጠላሽ ፡፡
- ሰም – ጠላሽ አይጥምም አይጣፈጥም አልተዋጣልሽም ፡፡
- ወርቅ – ምነው እጠላሽ ውስጥ አይጥ ገባበት ፡፡
መልካም ፈረስ ጭነህ
ስትወጣ ስትወርድ አየንህ ፡
ከሜዳ ስትደርስ ዝግ አርገው ፣
መቸም ጊዜው ጣይ ነው ፡፡
- ሰም – ቀኑ ገና ያልመሸ ጊዜው ያልጨለመ ነው ፡፡
- ወርቅ – ዘመን አዋራጅ ነው ጊዜ የጥላል ያጐሳቁላል ፡፡
መሸ መሰለኝ ሊጨልም ፤
እንደ ቀን ጣይ የለም ፡፡
- ሰም- አንደ ቀን የሞቀ የደመቀ ፀሐይ አይታይም ፡፡
- ወርቅ – ሰውን የሚያዋርድ ጊዜ ነው ፡፡
መተኪያ እንኳን ሌላ የለኝ ፡
ጥላዬ ተሰብሮ አዝናለሁኝ ፡፡
- ሰም- የጥላየ መሰበር አሳዘነኝ ቆጨኝ ፡፡
- ወርቅ – አጋሬና ጥጌ የሆነው ጥላየ ስለሞተብኝ መመኪያና መከበሪያ በማጣቴ አዝኛለሁ ፡፡
መተው ይገባናል በወነት ፡
ይኽን ምን አለበት ፡፡
- ሰም – ምንአለበት አይጎዳም ነገርን ማቃለል ፡፡
- ወርቅ -በውስጡ መንአለበት ምን ተቀምጦበት ይሖን ብሎ መጠያየቅ ፡፡
ይቀጥላል<!–nextpage–>
Leave a Reply
You must be logged in to post a comment.