ቅዱስ ያሬድ

ቅዱስ ያሬድ

ቅዱስ ያሬድ

ቅዱስ ያሬድ

ስመ-ጥሩው፡ ኢትዮጵያዊ የዜማ ደራሲና ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ፡ በመንፈስ ቅዱስ ተመሥጦ፡ የደረሰውን የምስጋና ድርሰት ያዜመው፡ መላእክት፡ በአብ፥ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ሥላሴነት ለሚመለከው ፈጣሪያቸው፡ ለእግዚአብሔር፡ በዚሁ የሥላሴ ምሥጢር፡ በሰማያት በሚያቀርቡትና አጥንትን በሚያለመልመው፡ “ግእዝ፥ ዕዝልና አራራይ” በተባሉት የዜማ ስልቶች ነው።

ልዩ ጣዕም ካለው፡ ከዚህ የላሕይ ድምፁ የተነሣ፡ ቅዱስ ያሬድን፡ ማኅሌታዊ ድርሰቱን ሲያዜም የሚያደምጠው ኹሉ፡ በዚያው በመንፈስ ቅዱስ የመመሰጥ ዕድል ፈንታን ያገኛል።

በቅዱስ ያሬድ ዘመን፡ ኢትዮጵያን ያስተዳድር የነበረው ዕድለኛ የዘውድ መሪ፡  የገናናው፡ የአጼ ካሌብ ልጅ፡ አጼ ገብረ-መስቀል ነበር። ማኅሌታዊው ካህን፡ ድርሰቱን በሚያዜምበት ጊዜ፡ እርሱም፡ እንደቅዱስ ያሬድ፡ በመንፈስ ቅዱስ፡ እጅግ ይመሰጥ ነበር።

ከሥነ በዓላቱ በአንደኛው ላይ፡ ቅዱስ ያሬድ፡ ማኅሌታዊ ድርሰቱን እያስሰማ፡ በሚያዜምበት ጊዜ፡ ሳይታወቀው፡ ወደዚሁ አጼ ዙፋን ቀርቦ ኖሮ፡ ኹለቱም፡ በማኅሌቱ ድርሰትና ዜማ፡ በጽኑ በመመሰጣቸው፡ አጼውም፡ ሳያውቅ፡ የጦሩን ጫፍ፡ በካህኑ ያሬድ እግር ላይ አሣርፎ ሲወጋው፥ ማኅሌታዊውም፡ መወጋቱ ሳይሰማው፡ ዜማውን ዝም ብሎ መቀጠሉ ሲነገር የሚኖር ዜና ነው።

ይህ ሥዕል የሚያዘክረው እውነታ፡ ያን ትንግርታዊ ኹኔታ ነው።

ከፌስ ቡክ የተገኘ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.