ዲኦንሄር

ዲኦንሄርዲኦንሄር

 

ሸንቁጥ አየለ

ዲኦንሄር የግእዝና የግሪክ ፊደላት በዉህደት የፈጠሩት ቃል ነዉ። በግሪክ ዲኦን ማለት ግዳታን መወጣት ማለት ሲሆን በግእዝ ሄር ማለት ቸርነት፣ በጎነት ፣ መልካምነት ማለት ነዉ። ስለሆነም ዲኦንሄር ማለት በቸርነትና በበጎነት ግዴታን መወጣት የሚል ጠቅለል ያለ መልዕክትን ይሰጣል። ዲኦንሄር በቴክኒካል መልኩ ሲፈታ ግን ማንኝዉም ሰዉ በፍቅር ፣ በእዉነትና በእዉቀት በመመራት ማህበራዊ ግዴታዉን በቸርነት መወጣት አለበት የሚል መልእክትን ይዞ ይመጣል። ዲኦንሄር በርዕዮት አለም ስያሜነትም ያገለግላል። ይህ የርዕዮተአለም ትርጓሜም አንዲት ሀገር የበለጸገች ታላቅና የተዋሃደች ሆና ልትመሰረትና ህልዉና ሊኖራት የሚችለዉ እያንዳንዱ የሀገሪቱ …

ማህበራዊ፣ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ሂደት በዲኦንሄር መርህ ሲመራ ብቻ ነዉ የሚል ታሳቢ አለዉ። ይህም መርህ ማንኝዉም በማህበረሰቡ ዉስጥ ያለ ሰዉ በፍቅር ፣ በእዉነትና በእዉቀት በመመራት ማህበራዊ ግዴታዉን በቸርነት መወጣት ያለበት ለሁል አቀፍ ሀገራዊ ብልጽግና ብሎም ልዕልና በማሰብ መሆን አለበት በሚል ጥልቅ ህሳቤ ዙሪያ ያጠነጥናል።

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.