በድርቅ በተጠቁ የአማራ ክልል አካባቢዎች የውኃ ወለድ በሽታዎች ሥጋት ፈጠሩ (ሪፖርተር ጋዜጣ)
በድርቅ በተጠቁ የአማራ ክልል አካባቢዎች የውኃ ወለድ በሽታዎች ሥጋት ፈጠሩ (ሪፖርተር ጋዜጣ)
በአማራ ክልላዊ መንግሥትበድርቅ በተጠቁ በተለያዩ ዞኖች የተከለሉ ውኃምንጮች ውስንነት፣ ከንፅህና ጋር ለተያያዙበሽታዎች መፈጠር ምክንያት መሆኑ ተገለጸ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት በዚህሳምንት በወጣው ሪፖርት፣ ‹‹ስካቢስ›› የተሰኘወረርሽኝ በምሥራቅ ጎጃም፣ በሰሜን ጎንደር፣በደቡብ ወሎና በዋግ ህምራ ዞኖች በሚገኙ 20ወረዳዎች መከሰቱን አስታውቋል፡፡ በዋግ ህምራዞን ብቻ 88,905 ግለሰቦች በወረርሽኙ መያዛቸውታውቋል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በበሽታውለተጠቁ ሥፍራዎች መድኃኒቶችን በመላክ ላይመሆኑን የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፣ የችግሩ መጠንከፍተኛ በመሆኑ የተለያዩ ዘርፎችን ትብብርየሚጠይቅ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡
በሽታው ተዛማች በመሆኑ ወረርሽኙንለመቆጣጠር የተጀመረው ጥረት በአፋጣኝተስፋፍቶ መቀጠል እንደሚኖርበት የገለጸውጽሕፈት ቤቱ፣ ወረርሽኙ የተከሰተው ከድርቁ ጋርተያይዞ እንደሆነ በሪፖርቱ አስፍሯል፡፡
ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ በምግብ እጥረትየተጎዱ ሕፃናት ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፡፡ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑየምግብ ፕሮግራም የሚያስፈልጋቸው ሕፃናትቁጥር ከሌላው ጊዜ በ20 በመቶ መጨመሩን፣የተጎጂዎቹ ቁጥር በየወሩ እየጨመረ መሄዱንጽሕፈት ቤቱ በሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
በመስከረም ወር የተመዘገቡ በምግብ ዕጦትየተጎዱ ሕፃናት ቁጥር 35,216 የነበረ ሲሆን፣በነሐሴ ወር ከተመዘገቡት 43,391 ሕፃናት የ19በመቶ ቅናሽ ያሳየ ቢሆንም፣ በአገር አቀፍ ደረጃበመስከረም ወር የተመዘገበው በምግብ ዕጦትየተጎዱ ሕፃናት ቁጥር ከሌላው ማንኛውምዓመት የ20 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
ከፍተኛው ቁጥር የተመዘገበው በአማራ ክልልእንደሆነ የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፣ በየወሩ በክልሉ6,489 በምግብ ዕጦት የተጎዱ ሕፃናት ወደምግብ ፕሮግራም እንደሚገቡ ጠቁሟል፡፡
በኤልኒኖ ምክንያት በተፈጠረው አየር መዛባትየተከሰተው ድርቅ እየተባባሰ መምጣቱን ጠቅሶ፣እየጨመረ የመጣውን የምግብ ዕርዳታ ፍላጎትመጠን ለማሟላት የኢትዮጵያ መንግሥትተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርብም አጥጋቢ ምላሽአለመገኘቱን አስታውቋል፡፡ እ.ኤ.አ. የ2015 እናየ2016 የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ ፍላጎት ማሟላትየሚያስችል የገንዘብ ምንጭ አለመኖሩ አሳሳቢእንደሆነ ተገልጿል፡፡ እ.ኤ.አ. ለ2016የሚያስፈልገው ዕርዳታ በአስቸኳይ መገኘትእንዳለበት የገለጸው ጽሕፈት ቤቱ፣ ዕርዳታውንአጓጉዞ ከሚፈለገው ሥፍራ ለማድረስ ከሦስትእስከ አምስት ወራት ቀድሞ መዘጋጀትእንደሚኖርበት ጠቁሟል፡፡
መንግሥት ከለጋሾች የሚፈለገውን ያህልየገንዘብ ድጋፍ ባለማግኘቱ ሁኔታዎች በከፉበትአካባቢ በራሱ ወጪ ዕለታዊ ዕርዳታዎችበማድረግ ላይ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከመንግሥት የመጠባበቂያ ምግብ ክምችት50,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴና 300 ሜትሪክ ቶንየምግብ ዘይት በመከፋፈል ላይ መሆኑተጠቁሟል፡፡ የከብቶች መኖ በመታደል ላይመሆኑን፣ የውኃ ጉድጓዶች ጥገና ሥራእየተከናወነ እንደሆነና የውኃ ማጣሪያኬሚካሎች በመሠራጨት ላይ መሆናቸውተገልጿል፡፡
በአሁኑ ወቅት በተፈጠረው ድርቅ ምክንያት 8.2ሚሊዮን ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታየሚያስፈልጋቸው ሲሆን፣ የዕርዳታ አቅርቦቱካልተፋጠነና የአየር ፀባዩ ካልተለወጠየተረጂዎች ቁጥር በሁለት ወራት ውስጥ 15ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል፡፡