የበደልና የቁጭት ግጥሞች

የበደልና የቁጭት ግጥሞች

እንግዲህ አይኖርም ነገር ማለሳለስ   
እነርሱም አያርፉ እኔም አልመለስ

የማ ቤት ጠፍቶ የማ ሊለማ
የማ ቤት ጠፍቶ የማ ሊበጂ
የአዉሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ

የተጣደ ምጣድ ክሁዋላዬ ኖሮ
ለካስ ጠላት ብቻ ሆኛለሁ ዘንድሮ

ጀግና ይሙት ፈሪ ይኑር ቢሻዉ
ኣተላ መሸከም ዪቺላል ትከሻዉ

እናቴስ መች ወልዳኝ እኔስ መች ተወለድኩ
ከጠላቶቼ ጋር ኣብሬ እየዶለትኩ

ጞበዝ ክተት አትስማ ገላጋይ
ያባትህ አደራ ይከብዳል ከድንገይ

አትነካኩኝ አትንኩኝ አልኩ እንጂ
ምንስ አንቀልባ አለኝ ለጠላት ወዳጂ

ጥራኝ ጫካዉ ጥራኝ ዱሩ
ላንተም ይሻልሀል ብቻ ከማደሩ

እልም ነው ጭልጥ ነው ዉሃ አይላመጥም
ጠላት ወዳጅ ላሆን አልለማመጥም

ያመጣል መንገድ ይወስዳል መንገድ
አንድ የሚጠላ አንድ የሚወደድ
ሀገር አስነካሽ ልጅ አይወለድ

 

 

እሾክ ብቻ ሆነ እግሬን ብዳብስደው
እንዴት መራመጃ መሄጃ ያጣል ሰርው

ተልባ ጠጣሁና የተበጠበጠ
አላስቀምጥ አለ ሆድ እየቆረጠ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.