የኢትዮጵያ ታሪክ ባጭሩ
የአርኪኦሎጂና የጽሁፍ መረጃዎች እንድሚገልጹት ኢትዮጵያ የመንግስት አስተዳደር ከጀመረችበት አንዲ ሺህ አመት በኃላ ወይንም ከአምስት ሺህ አመት በፊት የነበሩት ነገስታት ዝርዝር ታሪክ ላይ ንጉስ አሜን አንደኛ አራተኛው የኢትዮጵያ ንጉስ ነበር።
ይህ ታላቅ ንጉስ ግዛቱን በማስፋት ግብፅንም ያስተዳድር የነበረ ሲሆን ግብፆችም በታሪካቸው ትልቅ ቦታ ከሰጡት ነገስታቶቻቸው መካከል ዋንኛው ነው።
ንጉስ አሜን ኢትዮጵያዊ ንጉስ እንደነበር የሚቀርቡ መረጃዎች የሚከተሉት ናቸው።
1, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን መዝግባ የያዘቻቸው የነገስታት ታሪክ እና ዝርዝር
2, የጥንታዊ ሜሮይ ፍርስራሾች በማጥናት ንጉስ አሜን ኢትዮጵያዊ መሆኑን ያረጋገጠው የታሪክ ተመራማሪ ሆስኪንስ የጥናት ውጤት
3, በኑብያ ፒራሚዶች ውስጥ ንጉስ አሜን እና ሰራዊቱ ጋር ግብፅን በኃይል በያዙበት ወቅት ስላደረጉት ጦርነት የሚያሳዩ የተቀረፁ ምስሎች።
4, የንጉስ አሜን ዝርያዎች ግብፅ በውጭ ዜጎች በመዳቀሏ አገራችን ብለው ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸው
5, የሃርቫርድ ዩንቨርስቲ የቁፋሮ ተልእኮ ቡድን ግብፅን ስለገዙ ኢትዮጵያውያን ያቀረበው መረጃ
ወዘተ (ራፋቶኤል)::
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
በዓለም ዉስጥ ክሚገኙ ጥንታዊ አገሮች ዋነኛ ስትሆን ከሁሉም የበለጠ ረጅም እድሜ አስቆጥራለች፡፡ አምስት ሚሊዮን አመት የሚሆነውና በጣም ረጅም እድሜ ያስቆጠረው የሰው ቅሪት የተገኘው በኢትዮጵያ አዋሽ ሸለቆ አካባቢ ሲሆን ይህም፣ 3.2 ሚሊዮን አመት የሆነውን እዛው አካባቢ የተገኘውን የሉሲን (ድንቅነሽን) አጽም በእድሜ ይበልጣል፡፡
ሄሮደስ የሚባለው ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ታሪክ ፀሀፊ የጥንቷን ኢትዮጵያ በጽሁፎቹ ላይ ይገልፃታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ላይም ብዙ ግዜ የምትወሳ ስትሖን በተለይም ብሉይ ኪዳን ላይም የንግስት ሳባ ኢየሩሳሌም መሄድና ለንጉስ ሰለሞን ከባድ የሆኑ ጥያቄዎች ማንሳት ተጽፏል፡፡ኢትዮጵያ ዛሬ ያላትን መልክ እንድትይዝ ያደረጋት ንጉስ ሚኒሊክ የንግስት ሳባና የንጉስ ሰለሞን ልጅ እንደሆነ ይነገራል፡፡
የንግስት ሳባ ቤተ መንግስት ፍርስራሽ ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ በአክሱም አካባቢ ይገኛል፡፡ ክርስትናን ኢትዮጵያዉያን ከመቀበላቸዉ በፊት (ኣስቅድመዉ) የኦሪትን ህግ ሰለሚያዉቁ ኣመተ ዓለምን ወደታች እየቆጠሩ የጌታን መወለድ ይጠብቁ ሰለነበረ በአራተኛው ክፍለ ዘመን ክርስትናን ለመቀበል ኣላስቸገራቸዉም፡፡ ነገር ግን በሰባተኛው ክፍለ ዘመን በእስልምና መስፋፋት ምክንያት ኢትዮጵያ ከአውሮፖውያኑ ክርስትያን ርቃ ቆይታለች፡፡ ከዛም በ1500 ዎቹ ኢትዮጵውያን በግራኝ መሃመድ ወረራ የተነሳ ከፖርቱጋሎች ጋር ግንኙነትን መሰረቱ፡ አንድ ክ/ዘመን ያህል የፈጀ የሀይማኖት ግጭት በ1630ዎቹ ተነስቶ ከውጪ የመጡትን ሚሲዮናዊያንን በሙሉ ከኢትዮጵያ ተባረው ሲወጡ ሰላም ተመልሷል፡፡ ይህ የከፋ የግጭት ጊዜ ኢትዮጵያ የውጭ ክርስትያኖች ላይ እና አውሮፖውያኖች ላይ እስከ ሀያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ፊቷን እንድታዞር አስተዋጾ ከማድረጉም በተጨማሪ እስከ 19ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ድረስ ኢትዮጵያ ከመላው አለም ተገልላ እንድትቆይ አድርጓታል፡፡
ከ1700ዎቹ ጀምሮ 100 ለሚሆኑ አመታት ኢትዮጵያ ማዕከላዊ አገዛዝ ሳይኖሯት ቆይታለች፡፡ ይህም “ዘመነ መሳፍንት” የተለያዩ የኢትዮጵያን ክፍል ይገዙ በነበሩ ገዢዎች መሀል በነበረው ፉክክር የተነሳ ሲሆን በ1869 አፄ ቴዎድሮስ መሳፍንቶችን አንድ ላይ በማምጣት ዋነኛ አሰባሳቢ ሀይል ሆነዋል፡፡ ከ1881 እስከ 1905 ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ በአፍሪካ ይዞታቸውን እያሰፉ የነበሩትን የአውሮፖ ሀይሎችን ጥቃት በመከላከል ኢትዮጵያን በስርዓት አስተዳድረዋል፡፡ በዚያን ጊዜ ጣልያን ኤርትራን በከፊል ቅኝ ገዝታ የነበረችበትና በ1880ዎቹ አጋማሽ ላይ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ቅኝ ገዝታት የነበረችበት ጊዜ ስለነበር ከሌሎች አውሮፖ አገራት በበለጠ ለኢትዮጵያ አስጊ ነበረች፡፡ በ1880 ግን እስከዛሬ ድረስ ዝነኛ በሆነው የአድዋ ጦርነት ኢትዮጵያ ጣልያንን አሸንፋ በአፍሪካ የቀኝ ገዥ ሀይሎችን ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች፡፡ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ የቅኝ ገዥዎችን ወረራና መስፋፋት በመመከትና ድልን በመቀዳጀት ለኢትዮጵያዉያን ብቻ ሳይሆን በባርነት ቀንበር ተጠምደዉ ለሚማቅቁ የመላዉ ዓለም ህዝቦች ከፍተኛ ክብርና ተስፋን አጎናጥፈዋል::
በ1908 የዳግማዊ ሚኒሊክ ልጅ የሆኑትን እቴጌ ዘውዲቱ ስልጣን ያዙ ፡፡ የሳቸው የቅርብ የስጋ ዘመድ የነበሩት ራስ ተፈሪ መኮንንም ሞግዚት አስተዳደርና ወራሽ ሆነው ተሹመዋል፡፡
እቴጌ ዘውዲቱ በ1922 ሲሞቱ ተተኪያቸው ዐጼ ሀይለስላሴ ስልጣን ያዙ ፡፡ ነገር ግን በ1928 ዓ.ም የጣልያን ሀይሎች ኢትዮጵያን ለአጭር ጊዜ ወረው ሲቆጣጠሩ ግዛታቸው ተቋርጦ ነበር፡፡ ይህን ጊዜም አፄ ሀይለስላሴ ለሊግ ኦፍ ኔሽንስ ይግባኝ ብለው ሰሚ ስላጡ ወደ በእንግሊዝ አገር በመሰደድ ለአምስት አመታት ታግለዉ የኢትዮጵያን አርበኞች ከብሪታንያ ጋር በማስተባበር ጣልያን ተሸንፎ እንዲወጣ አድርገዋል፡፡ፋሽስቶች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ክፍተኛ ግፍ ከመፈጸማችዉም በላይ በኤርትራና በትግራይ ወንድሞቹ ላይ ከፍተኛ የስነልቦና ቡርቦራ በማድረግ እስካሁን ድረስ በአካባቢዉ ሰላም እንዳይሰፍን አድርገዋል::
አፄ ሀይለ ስላሴ እስከ 1966 ድረስ ስልጣን ላይ ከቆዩ በኋላ በምትካቸው የጊዜአዊ ወታደራዊ ምክር ቤት (ደርግ ወይም ኮሚቴ) ስልጣን ይዞ ወታደራዊና ሶሻሊዝም አመራር ተመሰረተ፡፡ በዛን ጊዜ ሀምሳ ዘጠኝ ኢትዮጵያ በከፍተኛ ጥረት ያፈራቻቸዉ ምሁራን፣ ሚኒስትሮች፣ ጀነራሎችና ንጉሳዊ ቤተሰቦች፣ ሲገደሉ ንጉሱም በ1967 ዓ.ም በቤተ መንግስታቸው ውስጥ ተገድልዉ ተገኙ ከመባሉ ዉጭ ጥርት ያለ መረጃ የቀረበ አይመስልም፡፡
ከዚህ ክስተት በኋላ ሻለቃ መንግስቱ ሀይለ ማሪያም እንደ ኘሬዝዳንትና እንደ ደርግ ሊቀ መንበር ስልጣን ያዙ፡፡ ስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜም አምባገነናዊዉ መንግስት በሶቪየት ህብረትና በኩባ እርዳታና እገዛ ይደረግላቸዉ ነበረ፡፡ ለ 17 አመት የቆየው ይህ አገዛዝና በዛ ጊዜ የተከሰተው ድርቅና ረሀብ የደርግን መውደቅ አፋጥነውታል፡፡
በ1981ዓ.ም የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ትህነግ) ከብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) እና ከኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ጋር አንድ ላይ ነን ብሎ ራሱን የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) በማለት በሀይል ተመሰረተ:: በግንቦት 1983 ላይም ወያኔ አዲስ አበባ በመግባት ኮሎኔል መንግስቱ ወደ ዙንባቢዌ ሲሰደዱ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሽፍጥ የተሞላበት ጸረ አንድነት ፕሮፓጋንዳ ከማካሄዱም በላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ መብት ረገጣ ፈጸመ፡፡
በ1983 ከወያኔ እና ከሌሎች ኣሻንጉሊት የፖለቲካ ድርጅቶች የተውጣጡ 87 ተወካዮች የኢትዮጵያ ሽግግር መንግስት በማለት አቋቋሙ:: በዚያው አመት በኢሳያስ አፈወርቅ መሪነት የኤርትራ ህዝቦች ነፃ አውጭ ግንባር (ኤህነግ) ከ30 አመታት የአንድነት ትግል በኋላ ኤርትራን ገንጥለዉ መንግስት መሰረቱ፡፡ ሁኔታዉን እንዲያመቻች እስከ ግንቦት 1985 ዓ.ም ድረስም በጊዜአዊነት ስም ወያኔ እስልጣን ላይ እንዲቆይና በ1987 መንግስት እንዲመሰርት ተደረገ ::
Leave a Reply
You must be logged in to post a comment.