ኢትዮጵያዊው ፃዲቅ አቡነ ዜና ማርቆስ
ኢትዮጵያዊውን ፃዲቅ አቡነ ዜና ማርቆስ:-
ን:: ፃዲቅ አቡነ ዜና ማርቆስ ማን ናቸው? ምንስ ቃል ኪዳን ተሰጣቸው? ምን ምን ተጋድሎ አደረጉ?ፃዲቁ አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ ትውልድ ሀገሩ በፅላልሽ አውራጃ ዞረሬ ነው፡፡ አባቱ ዮሐንስ እናቱ ማርያም ዘመዳ ይባላሉ፡፡ ልጅም አልነበራቸውም የተባረከ ልጅ ፈጣሪያቸው እንዲሰጣቸው በጾም በፀሎት ሲለምኑ ከወንጌላዊው፤ ሐዋርያ ቅዱስ ማርቆስ ወደ ማርያም ዘመዳ በሌሊት በራዕይ መጥቶ የተባረከ ልጅ እንደምትወልድ ነገራት፡፡ እንዲሁ ዮሐንስ በቤተ መቅደስ ውስጥ ዕጣን እያጠነ ሳለ ዳግም ለማርያም ዘመዳ የተናገረው ቃል ለሱም ተነገረው፡፡ አባታችንም የካቲት 24 ተፀንሶ ህዳር 24 ቀን ተወለደ፡፡
በተወለደ እለትም ሊቃነ መልአክት ቅዱስ ዑራኤልና ቅዱስ ሩፋኤል እንደ ነብዩ ኤልያስ የብርሃን ልብስ አልብሰው በክንፋቸው ጋርደውታል፡፡ እኒህም መላዕክት አባታችንን ከእናቱ ከማርያም ዘመዳ እቅፍ ወስደው ወደ ግብፅ ሀገር ከሀዋርያው ቅዱስ ማርቆስ መቃብር አስባርከውታል፡፡ አባቱ ዮሐንስ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት ይህን ነገር ይመለከት ነበር፡፡ አባታችንም በተወለደ በሶስተኛው ቀን ከእናቱ እቅፍ ወርዶ በእግሩ ቆመ፡፡ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅድስ ሶስት ጊዜ ሰገደማር 9፡23
በእናቱ እቅፍ እያለ ጾም መጾም ጀመረ፡፡ በተወለደ በአንድ አመቱ በእግሮቹ እየዳኸ ብቻውን ወደ ቤተክርስቲያን ሄደ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም በክንፎቹ አንስቶ ወደ ሰማይ ወሰደው በዚያም በመንፈሳዊ በረከት ተባረከ፡፡ በአምስት ዓመቱም የብሉያትንና የሐዲሳትን መፃህፍት አወቀ፡፡ ከአባ ጊርሎስም እጅ የዲቁና ክህነት ተቀበለ፡፡ አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ ለአቅመ አዳም በደረሰ ጊዜ ወላጆቹ ማርያም ክብራ የተባለች ልጅ አጭተው አጋቡት አባታችንም በሌሊት ተነስቶ ማቴ 10፡37 “አባቱና እናቱን፣ ሚስቱን፣ ቤቱን፣ ልጆቹንም ንብረቱንና እርሻውን ያልተወ ሊያገለግለኝ አይችልም፡፡” የሚለውን ቃል አስቦ- እህቴ ሆይ የዚህ ዓለም ኑሮ ምን ይጠቅመናል፡፡ ፍላጎቱም ኑሮውም እንደ ጥላ ያልፋልና እንደ ዱር አበባም ይረግፋልና ስለዚህ ለነፍሴ ድህነትን ለመሻት እሄድ ዘንድ አሰናብቺኝ አንቺም ለራስሽ የወደድሽውን አድርጊ አላት፡፡ ሙሽራይቱም መልሳ እንዲህ አለች አንተ የተውኸውን አለም ለእኔስ ምን ይጠቅመኛል አለች፡፡ ሁለቱም ሰው ሳያያቸው ከጫጉላ ቤታቸው በሌሊት ወጥተው የእግዚአብሔር መልአክ እየመራቸው ወደ ገዳም ወሰዳቸው፡፡ ማርያም ክብራ ብዙ ተጋድሎ ከፈፀመች በኋላ በሰላም አረፈች ሁለት አንበሶች ጉድጓድ ቆፍረው ቀበሯት፡፡ እድሜዋ አስራ ሰባት ዓመት ነበር፡፡
አባታችን በደመና እስክንድርያ ሀገር ሄዶ ከሊቀ ጳጳስ ከአባ ብንያሚን የቅስና ሹመትን ተቀበለ፡፡ ከዚያም በጫጉላነት ወደ ተዋት ሀገሩ በብሩህ ደመና 2 ነገ 2፡11 ተጭኖ ሄደ፡፡ አባትና እናቱ ጋር አብሮ ቆየ፡፡ በአባታችን በአቡነ ተክለሃይማኖት የዕረፍት ቀን ነሐሴ 24 አባትና እናቱ አረፉ፡፡ በአንድ ቀንም ተቀበሩ፡፡ አባታችንም የእናትና የአባቱን ቤት ትቶ የእግዚአብሔር መልአክ ወዳዘዘው ወግዳ ወደተባለ ሀገር ሄደ፡፡
አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ ከአቡነ ተክለሃይማኖት ጋር በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ጣኦት አምላኪዎችን በማስተማር በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቀ፡፡ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖትም ለአቡነ ዜና ማርቆስ የመልአክት አስኬማ አለበሰው፡፡ እንደ ሐዋርያት ደመና ጠቅሶ ወደ ኢየሩሳሌም በየጊዜው እየተመላለሰ ተሳለመ፡፡ ከቅድስት ኢየሩሳሌም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ከደብረ ጎለጎታም አፈር፣ ከዮርዳኖስ ወንዝም ውሃ አምጥቶ በገዳሙ በደብረ ብስራት አፈሩን ከአፈር ውሃውን ከውሃው ጋር ጨመረው፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤልም ባረከው፡፡
በደብረ ብስራት ከምድር ላይ ሳይቀመጥና ሳይተኛ እንደቆመ ሰባት ዓመት ኖረ፡፡ አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ በኢትዮጵያ ምድር ያልተመላለሰበት ቦታ የለም፡፡ ሰባት ዓመት ስለ ፀለየ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳምህ መጥተው በእናቴ ስም ለሚፀልዩ ከክፉ ነገር ሁሉ እጠብቃቸዋለሁ ብሎ የእመቤታችንን ስዕል በቃል ኪዳን ሰጠው፡፡
አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ በደመና ተነጥቆ ብሔረ ሕያዋን ደርሶ ሞትን ካልቀመሱት ከሄኖክ፣ ከኤልያስና ከዕዝራ በረከትን ተቀለ፡፡ የጥፋት መልዕክተኛ የሆነ ግራኝ መሐመድ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማትን ሲያጠፋ የአባታችን ዜና ማርቆስን ገዳም ያጠፋ ዘንድ አልተቻለውም በፀሎቱ ተጠብቃለችና፡፡
የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ የተቀደስክ አባት ሆይ ወደ አንተ ተልኬአለሁ፡፡ እግዚአብሔር ፈጣሪህ ለምን ሁልጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ትመላለሳለህ ለምንስ ትደክማለህ ለኢትዮጵያ ሰዎች ህጌንና ሃይማኖቴን ታስተምራቸው ዘንድ የህግ መምህር አድርጌሃለሁ፡፡ ከኢየሩሳሌም ምድር አፈሩን ከአፈርዋ ውኃውን ከውሃዋ በማዋሐድህ የተባረከችና የተቀደሰች ሀገርህን ኢትዮጵያን እንደ ኢየሩሳሌም አድርጌአታለሁ ሲል ነገረው፡፡ ዳግመኛም የኢትዮጵያ ሰዎች ኃጢአትን ሰርተው ንስሐ ቢገቡና ከዮርዳኖስ ወስደህ በገዳምህ ካሉ ውሃዎች በቀላቀልከው በእነዚያ ውሃዎች ቢጠመቁ በዮርዳኖስ ውኃ እንደ ተጠመቁ አድርጌ እቆጥርላቸዋለሁ፡፡ ከደዌ ስጋም ይፈወሳሉ፣ ድህነተ ነፍስንም ያገኛሉ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱና ከቅዱሳኑ ጋር ወደ አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ መጥቶ በአማላጅነትህ ታምኖ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ፣ ቤተክርስቲያንህን ለሚሰራ፣ የገድልህን መጽሐፍም ለሚጽፍ፣ ለሚያጽፍ ለቤተክርስቲያንህ ንዋየ ቅዱሳትን ለሚሰጥ ሁሉ እስከ 12 ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ ሲል ቃል ኪዳን ከሰጠው በኋላ በክብር ወደ ሰማይ አረገ፡፡ ማቴ 10፡41-42
አባታችን ዜና ማርቆስ በህይወት ዘመኑ ሁሉ ሰይጣንን ለቤተክርስቲያን የሚሆነውን እንጨት እያሸከመ በደብረ ብስራት እንዲያገለግል አደረገ፡፡ አባታችን ድንቅ ድንቅ ተአምራትንም አደረገ፡፡ ሙት አስነሳ፣ፈረስ አፉን ከፍቶ የእግዚአብሔርን ሃያልነት እንዲመሰክርም አደረገ፡፡ ማር 9፡23
በመንገድ ላይ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ እንዲህ አለው ወዳጄ ሆይ እነሆ ከዚህ ከኃላፊው የስጋ ዓለም የምትለይበት ጊዜ ቀርቧል፡፡ እነሆ የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ሰጠሁህ ስምህን የሚጠሩትን መታሰቢያህንም የሚያደርጉትን የእሳት ባህር አታገኛቸውም አስቀድሜ እንደነገርኩህም የሞረትና የመርሐቤቴ ሰዎች ለስምህ መታሰቢያ አስራት ይሁኑልህ በፀሎትህ ወደ እኔ የሚማፀኑትንም ሁሉ እምራቸዋለሁ አለው ይህን ቃል ኪዳን ሲሰጠው ቅዱሳን ይሰሙ ነበር፡፡ እኒህም ቅዱሳን አባታችንን ከአስር ወር በኋላ ወደ እኛ ትመጣለህ ብለው ከጌታቸው ጋር ወደ ሰማያት አረጉ፡፡
ከዚህም በኋላ ከገዳመ ደንስ ተመልሶ ወደ ደብረ ብስራት መጣ በጾም በፀሎት ያለዕረፍት ተቀመጠ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከእናቱ ጋር ቅዱሳንን አስከትሎ ወደ አባታችን መጣ፡፡ እጅግ የላቀ ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ አባታችንም መልሶ አቤቱ የሚወደኝ ሰው ለንስሀ ሳይደርስ በሞት አትቅሰፈው ንስሐ እስከሚፈፅም ድረስ ስለእኔ ብለህ ጠብቀው አለ ጌታም የለመንኸኝ ቃልኪዳን ይሁንልህ ይደረግልህ አለው፡፡
አባታችንም ልጆቹን ሰብስቦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውን ቃል ኪዳን ነገራቸው፡፡ በፀሎቱም ፀሐይን አቆመ፡፡ ታህሳስ 2 ቀን የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቦ እንዲህ አላቸው፡፡ ከዚህ ዓለም የምለይበት ጊዜ ደርሷልና እኔ ወደ ፈጣሪዬ እሄዳለሁ፡፡ የምመክራችሁን ስሙ ከበጎ ስራ ሁሉ አስቀድማችሁ እርስ በኋላ በሰላም አረፈች ሁለት አንበሶች ጉድጓድ ቆፍረው ቀበሯት፡፡ እድሜዋ አስራ ሰባት ዓመት ነበር፡፡
አባታችን በደመና እስክንድርያ ሀገር ሄዶ ከሊቀ ጳጳስ ከአባ ብንያሚን የቅስና ሹመትን ተቀበለ፡፡ ከዚያም በጫጉላነት ወደ ተዋት ሀገሩ በብሩህ ደመና ተጭኖ ሄደ፡፡ አባትና እናቱ ጋር አብሮ ቆየ፡፡ በአባታችን በአቡነ ተክለሃይማኖት የዕረፍት ቀን ነሐሴ 24 አባትና እናቱ አረፉ፡፡ በአንድ ቀንም ተቀበሩ፡፡ አባታችንም የእናትና የአባቱን ቤት ትቶ የእግዚአብሔር መልዓክ ወዳዘዘው ወግዳ ወደተባለ ሀገር ሄደ፡፡
አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ ከአቡነ ተክለሃይማኖት ጋር በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ጣኦት አምላኪዎችን በማስተማር በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቀ፡፡ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖትም ለአቡነ ዜና ማርቆስ የመልአክት አስኬማ አለበሰው፡፡ እንደ ሐዋርያት ደመና ጠቅሶ ወደ ኢየሩሳሌም በየጊዜው እየተመላለሰ ተሳለመ፡፡ ከቅድስት ኢየሩሳሌም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ከደብረ ጎለጎታም አፈር፣ ከዮርዳኖስ ወንዝም ውሃ አምጥቶ በገዳሙ በደብረ ብስራት አፈሩን ከአፈር ውሃውን ከውሃው ጋር ጨመረው፡፡ የእግዚአብሔር መልዓክ ቅዱስ ሩፋኤልም ባረከው፡፡
በደብረ ብስራት ከምድር ላይ ሳይቀመጥና ሳይተኛ እንደቆመ ሰባት ዓመት ኖረ፡፡ አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ በኢትዮጵያ ምድር ያልተመላለሰበት ቦታ የለም፡፡ ሰባት ዓመት ስለ ፀለየ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳምህ መጥተው በእናቴ ስም ለሚፀልዩ ከክፉ ነገር ሁሉ እጠብቃቸዋለሁ ብሎ የእመቤታችንን ስዕል በቃል ኪዳን ሰጠው፡፡
አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ በደመና ተነጥቆ ብሔረ ሕያዋን ደርሶ ሞትን ካልቀመሱት ከሄኖክ፣ ከኤልያስና ከዕዝራ በረከትን ተቀለ፡፡ የጥፋት መልዕክተኛ የሆነ ግራኝ መሐመድ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማትን ሲያጠፋ የአባታችን ዜና ማርቆስን ገዳም ያጠፋ ዘንድ አልተቻለውም በፀሎቱ ተጠብቃለችና፡፡
የእግዚአብሔር መልዓክ ተገልጦ የተቀደስክ አባት ሆይ ወደ አንተ ተልኬአለሁ፡፡ እግዚአብሔር ፈጣሪህ ለምን ሁልጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ትመላለሳለህ ለምንስ ትደክማለህ ለኢትዮጵያ ሰዎች ህጌንና ሃይማኖቴን ታስተምራቸው ዘንድ የህግ መምህር አድርጌሃለሁ፡፡ ከኢየሩሳሌም ምድር አፈሩን ከአፈርዋ ውኃውን ከውሃዋ በማዋሐድህ የተባረከችና የተቀደሰች ሀገርህን ኢትዮጵያን እንደ ኢየሩሳሌም አድርጌአታለሁ ሲል ነገረው፡፡ዳግመኛም የኢትዮጵያ ሰዎች ኃጢአትን ሰርተው ንስሐ ቢገቡና ከዮርዳኖስ ወስደህ በገዳምህ ካሉ ውሃዎች በቀላቀልከው በእነዚያ ውሃዎች ቢጠመቁ በዮርዳኖስ ውኃ እንደ ተጠመቁ አድርጌ እቆጥርላቸዋለሁ፡፡ ከደዌ ስጋም ይፈወሳሉ፣ ድህነተ ነፍስንም ያገኛሉ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱና ከቅዱሳኑ ጋር ወደ አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ መጥቶ በአማላጅነትህ ታምኖ ስምህን ለሚጠራ መታሰቢያህን ለሚያደርግ፣ ቤተክርስቲያንህን ለሚሰራ፣ የገድልህን መጽሐፍም ለሚጽፍ፣ ለሚያጽፍ ለቤተክርስቲያንህ ንዋየ ቅዱሳትን ለሚሰጥ ሁሉ እስከ 12 ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ ሲል ቃል ኪዳን ከሰጠው በኋላ በክብር ወደ ሰማይ አረገ፡፡
አባታችን ዜና ማርቆስ በህይወት ዘመኑ ሁሉ ሰይጣንን ለቤተክርስቲያን የሚሆነውን እንጨት እያሸከመ በደብረ ብስራት እንዲያገለግል አደረገ፡፡ አባታችን ድንቅ ድንቅ ተአምራትንም አደረገ፡፡ ሙት አስነሳ፣ፈረስ አፉን ከፍቶ የእግዚአብሔርን ሃያልነት እንዲመሰክርም አደረገ፡፡
በመሄድ ላይ ሳለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦ እንዲህ አለው ወዳጄ ሆይ እነሆ ከዚህ ከኃላፊው የስጋ ዓለም የምትለይበት ጊዜ ቀርቧል፡፡ እነሆ የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ሰጠሁህ ስምህን የሚጠሩትን መታሰቢያህንም የሚያደርጉትን የእሳት ባህር አታገኛቸውም አስቀድሜ እንደነገርኩህም የሞረትና የመርሐቤቴ ሰዎች ለስምህ መታሰቢያ አስራት ይሁኑልህ በፀሎትህ ወደ እኔ የሚማፀኑትንም ሁሉ እምራቸዋለሁ አለው ይህን ቃል ኪዳን ሲሰጠው ቅዱሳን ይሰሙ ነበር፡፡ እኒህም ቅዱሳን አባታችንን ከአስር ወር በኋላ ወደ እኛ ትመጣለህ ብለው ከጌታቸው ጋር ወደ ሰማያት አረጉ፡፡
ከዚህም በኋላ ከገዳመ ደንስ ተመልሶ ወደ ደብረ ብስራት መጣ በጾም በፀሎት ያለዕረፍት ተቀመጠ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከእናቱ ጋር ቅዱሳንን አስከትሎ ወደ አባታችን መጣ፡፡ እጅግ የላቀ ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ አባታችንም መልሶ አቤቱ የሚወደኝ ሰው ለንስሀ ሳይደርስ በሞት አትቅሰፈው ንስሐ እስከሚፈፅም ድረስ ስለእኔ ብለህ ጠብቀው አለ ጌታም የለመንኸኝ ቃልኪዳን ይሁንልህ ይደረግልህ አለው፡፡
አባታችንም ልጆቹን ሰብስቦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውን ቃል ኪዳን ነገራቸው፡፡ በፀሎቱም ፀሐይን አቆመ፡፡ ታህሳስ 2 ቀን የደቀ መዛሙርቱን እግር አጥቦ እንዲህ አላቸው፡፡ ከዚህ ዓለም የምለይበት ጊዜ ደርሷልና እኔ ወደ ፈጣሪዬ እሄዳለሁ፡፡ የምመክራችሁን ስሙ ከበጎ ስራ ሁሉ አስቀድማችሁ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ ፍቅር ሰማያዊ መንግስትን ለማግኘት በባለሟልነት ወደ እግዚአብሔር ፊት ያደርሳል እያለ ብዙ ምክር መከራቸው ወደ ፈጣሪው ቀና ብሎ አቤቱ የሰጠኸኝን እኒህን ልጆቼን በቸርነትህ ከክፉ ስራ ሁሉ ጠብቃቸው እያለ ፀለየ፡፡ በታህሳስ 3 ቀንም ነፍሱ ከስጋው ተለየች፡፡
የእግዚአብሔር መልአክትም የፃድቅ ሰው ሞቱ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው አሉ፡፡ መዝ 115/116፡6
ፃዲቁ አባታችን አቡነ ዜና ማርቆስ
በትዕግስቱ ፃዲቅ የሆነ፣
ለኢትዮጵያ ሀገር ብርሃን በሆነ ሃይማኖቱና ትምህርቱ ያበራ፣
አራቱን ወንጌላት ዙሮ ያስተማረ ታላቅ ሐዋርያ፣
ሙሴ የፃፈውን አስርቱ ቃላተ ኦሪትን የሚያስተምር ነቢይና ካህን፣
በሚያመለክተው ትንቢቱ ከእግዚአብሔር ዘንድ በጎ ነገር የሚያመጣ፣
በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ራዕይን የሚያይ፣
በደመና ከሀገር ሀገር የሚንቀሳቀስ፣
አጋንንትን በፀሎቱ ድል ያደረገ፣
ኃላፊውን ዓለም ጥሎ የኮበለለ፣ነው፡፡
የአባታችን የአቡነ ዜና ማርቆስ በረከት ይደርብን!!!
ማኅሌተ ጽጌን የደረሰው የአባታችን የአባ ጽጌ ድንግል ታሪክ
+++++++
ማኅሌተ ጽጌን የደረሰው ሰው አባ ጽጌ ይባላል፡፡ አባ ጽጌ በሰሜን ሸዋ በይፋት አውራጃ ውስጥ ሲኾን ፤ መጀመሪያ ኢአማኒ(ያላመነና ያልተጠመቀ) ነበር፤ ከዕለታት አንድ ቀን ይህ ሰው በወጣትነት ዕድሜው አውሬ ለማደን ወደ ጫካ ሄደ፡፡ ጫካዋም በዚያው በይፋት አውራጃ የምትገኝና ልዩ ስሟ ደንስ ገዳመ-ደንስ የሚባል ነው፡፡(አባ ጽጌ ከቤተ እስራኤላውያን ወገን እንደሆነ ይገመታል፡፡)
በጫካዋ ውስጥ ፊቷ በጽጌሬዳ አበባ የተከበበና ያጌጠ፤ እጅግም ደስ የምታሰኝ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል አይቶ፤ በሥዕሏ ውበት እየተደነቀ በአግራሞት ሲመለከት አንደ እርሱ ያልተጠመቀ ጓደኛው መጥቶ “ምን እየፈለግህ ነው… የክርስቲያኖችን ሥዕል ነውን” በማለት ተቆጣና በያዘው በትር ሥዕሏን ሲመታት ወዲያው ተቀስፎ ሞተ፡፡
ከዚኽ በኋላ ክንፎቹ በጽጌሬዳ አበባ ያጌጡ የመሰለ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በነጭ ወፍ ተመስሎ ወደ አባ ጽጌ መጥቶ አንድ ቀይ መነኩሴ እስኪመጣ ድረስ ይህችን ሥዕል ጠብቃት ብሎ በሰው አነጋገር ነግሮት ተሠወረ፡፡
በዘመኑ ታላቅ አባት የነበሩት አቡነ ዜና ማርቆስ በሌላ ጊዜ አባ ጽጌ ወዳለበት ወደ ይፋት መጥተው ከነቢዩ ኢሳይያስ ትንቢት (ኢሳ.11፡1) “ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ፤ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ” እያሉ በግእዝ ሲያነቡ አባ ጽጌ ሰማና “አባቶቼ አይሁድ የነቢያትን ትንቢት ንባቡን አስተምረውኛል አውቀዋለሁ፤ ትርጉሙን ግን አላውቀውምና ይተርጉሙልኝ” አላቸው፡፡
አቡነ ዜና ማርቆስም ሲተረጉምለት እንዲህ አሉ “ትወጽእ በትር እምሥርወ እሴይ የሚለው ንባብ፤ ከእሴይ ወገን የሕይወት በትር የኾነች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትወለዳለች ማለት ነው፡፡ ወየዐርግ ጽጌ እምኔሃ የሚለው ንባብ ደግሞ፤ ከእመቤታችን ጌታ በድንግልና ይወለዳል፤ ከጌታም ክብር ይገኛል ማለት ነው፡፡ ይኽም ጌታ ተወልዶ ትንቢቱ በእውነት ተፈጽሟል” ብሎ ተረጎሙለት፡፡
አባ ጽጌም በዚኽ ትርጉም ደስ ተሰኝቶ “አባት ሆይ የኢሳይያስን ትንቢት በመልካም ሁኔታ ተረጎሙት፤ መልካም ነገርንም ተናገሩ” አላቸውና ሥዕሏ ወዳለችበት ቦታ አቡነ ዜና ማርቆስን ወስዶ ታሪኩ ከላይ እንደተገለጸው በጫካ ውስጥ ያያትን ሥዕል ጓደኛው በያዘው በትር ሲመታት ወዲያው እንደተቀሰፈና ክንፎቹ በጽጌረዳ አበባ ያጌጡ አንድ ነጭ ወፍ (ቅዱስ ሩፋኤል) ወደ እርሱ መጥቶ “ቀይ መነኩሴ እስኪመጣ ድረስ ይህችን ሥዕል ጠብቃት” ብሎ በሰው አነጋገር ያነጋገረውን ሁሉ ነገረው፤ አቡነ ዜና ማርቆስም በሥዕሏ የተደረገውን ተዐምር ሰምተው እጅግ ደስ አላቸውና “በል መጀመሪያ እመቤታችን በድንግልና በወለደችው በፈጣሪ ልጇ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፤ ይህችን ሥዕል ያስገኘ፤ ሰማይና ምድርን በውስጣቸው ያለውንም ሁሉ የፈጠረ፤ እርሱ እንደሆነ እወቅ አለውና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቀው ጽጌ ብርሃን ብለው ሰየሙት፤ ከዚህ በኋላ ሥዕሏን ከገዳመ ደንስ ደብረ ብሥራት ወደሚባለው ገዳም ወስደው በዘመነ ጽጌ፤ ጥቅምት አንድ ቀን በክብር አስቀመጧት፡፡ የምትከብርበትንም ቀን ጥቅምት ሦስት እና ሰኔ ስምንት ቀን አደረጉ፡፡ ጽጌ ብርሃንንም ለመዓርገ ምንኩስና አበቁት፡፡
አባ ጽጌ ብርሃን ጽጌ ድንግል የሚለው ቅጽል ስሙ ነው፡፡ አባ ጽጌ ብርሃን/ ጽጌ ድንግል ከመጠመቁ በፊት በአባቶቹ በአይሁድ ሥርዓት እያለ የብሉያት መጻሕፍትን የተማረ ነበር፡፡ የሐዲሳት መጻሕፍትን ትርጓሜ ግን የተማረው ከአቡነ ዜና ማርቆስ ነበር፡፡
በማኅሌት አገልግሎት ጊዜም ታላቁ ፃድቅ አቡነ ዜና ማርቆስ ቤተክርስቲያኒቱንና ሥዕሏን እየዞረ ሲያጥን፤ እመቤታችን የካህናቱን አገልግሎት እነደምትባርክ ካህናቱ በግልፅ ይረዱ ነበር፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ በተወለዱ በ140 ዓመታቸው ዓርብ ጠዋት ታኅሳስ ሦስት ቀን 1402 ዓ.ም. ዐረፉ፡፡
ከዚህ በኋላ አባ ጽጌ ብርሃን በወሎ ክፍለ ሀገር በወራይሉ አውራጃ፤ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ ለሚባለው ገዳም የሕግ መምህር ሆኖ ከተሸመውና ከጓደኛው ከአባ ገብረ ማርያም ጋር እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ በመሆን እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ በጎ መዐዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ማኅሌተ ጽጌ የተባለውን ድርሰት፤ በአባቷ በዳዊት መዝሙር መጠን 150 አድርጎ ደረሰ፡፡
አባ ጽጌ ድንግል/ጽጌ ብርሃን/ እና አባ ገብረ ማርያም የዘመነ ጽጌን የማኅሌት አገልግሎት በጋራና በፍቅር ያገለግሉ ነበር፡፡ አንዱን ዓመት አባ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በኾነው መስከረም 25 ቀን ከደብረ ሐንታ መጥቶ አባ ጽጌ ድንግል ካለበት ደብረ ብሥራት ገብቶ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ አገልግሎት በአንድነት ፈጽመው ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብረ ሐንታ ይመለሳል፡፡ በቀጣዩ ዓመት ደግሞ አባ ጽጌ ድንግል ወደ አባ ገብረ ማርያም ይሄዱና በአንድነት በፍቅር ያገለግላሉ፡፡
የአባቶቻችን የአቡነ ዜና ማርቆስ፤ የአባ ጽጌ ብርሃን እና የአባ ገብረ ማርያም ረድዔት ሳይለየን ከዘመነ ጽጌ አገልግሎት በትጋት እንድንሳተፍ ያድርገን! አሜን፡፡
ምንጭ- ገድለ አቡነ ዜና ማርቆስ
-የማኅሌተ ጽጌ ትርጉምና ታሪክ፤ ሊቀ ጠበብት አስራደ ባያብል፤ 2004 ዓ.ም.፤ አዲስ አበባ
©ዘሕሊና
አሜን!