የአምሃራ ሕዝብ

የአምሃራ ሕዝብ (ከፌስ ቡክ የተገኘ)

 

ጥቂት ሥለ ነገረ ዐማርኛ

፩፣
ዐርበኛ አምደ ጽዮን፣
መላላሽ የወሰን፣
ወኸ እንደ መሰን።

ይህ በጥንቱ ዐማርኛ ባለ ቅኔዎች ለኃያሉ ንጉሰ ነገሥት ለአፄ አምደ ጽዮን ከዛሬ ስድስት መቶ ዓመታት በፊት ያቀረቡት ምወድስ ሲሆን በንጉሰ ነገሥቱ ዜና መዋእል ውስጥ ይገኛል። አፄ አምደ ጽዮን እጅግም ኃያል፣ ጦረኛ እና የማይሽነፍ ነበር። የኢትዮጵያን ግዛት በደቡብ እስከ ሕንድ ውቅያኖስ(የ አሁኑን ሶማሊያን፣ ከፊል ኬንያንን፣ በማጠቃለል)ያስፋፋ፣ በምእራብ ሜሮዬንንና ኑብያን የወጋና ያስገበረ፣ በ ምስራቅ ዘይላን፣በርበራን እና ኤደንን ያጠቃለለ፣ በሰሜን ከቀይ ባሕርና ከዳሕላክ ኦቶማን ቱርክን የደመሰሰ፣ ምስር ምድርን ያስገበረ፣ ባሕረ ነጋሽን የሾመ፣ዐርበኛ አምደ ጽዮን።

ሥለ ነገረ ዐማረኛ ሲነሳ፣ የግእዝም ጉዳይ አብሮ ይነሳል። ግእዝ ለምን ተናጋሪ የለውም? ዐማርኛስ ከየት ወዴት? የሚሉ እሳቤዎች ሁሌም ይነሳሉ። ዐማርኛ እንግዲህ ግራ ዘመም የጎሳ ብሄርተኞቱ(ኢትዮዽያ የመቶ ዓመት ታሪክ ብቻ ነው ያላት ባዮች) እንደሚሉት የአፄ ቴዎድሮስ፣ የአፄ ዮሐንስ ፣የአፄ ምኒሊክ፣የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ ከጥንት ከአክሱም ዘመን ጀምሮ ከዛጉዌና ከሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥታት ጋር የተቆራኘ ነው። በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግስት በይፋ ልሳነ ንጉስ ከመሆን ጀምሮ፣ በተከታታይ ለሰባት መቶ ዓመታት ከነገሱት ሰለሞናዊ ነገሥታት ጋር የተያያዘ ነው።

፪፣
ከቋንቋ ሥያሜነት ባሻገር የቃሉ ትርጉም

ሀ፣ ግልጽነትን ለማስረዳት
ምሳሌ፣ የምናገረው እኮ አማርኛ ነው።

ለ፣ ምን አይነት አነጋገር ነው ብሎ ለመጠየቅ
ምሳሌ፣ ይህ ደግሞ ምን የሚሉት አማርኛ ነው?

ሐ፣ ፍላጎት አለኝ ወይም እፈልጋለሁ ብሎ ለማሳወቅ(በመጠይቃዊ መልክ)
ምሳሌ፣ (እኔ)አማረኛ?
ይህም የሚሆነው በአንደኛ መደብ ነጠላ ቁጥር ነው።

 

የአምሃራ ሕዝብ

የአምሃራ ሕዝብ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.