ለኢትዮጵያ ፖለቲካ አዉራ ወይስ በህግ መሰረት ላይ የቆመ ስርአት?
ለኢትዮጵያ ፖለቲካ አዉራ ወይስ በህግ መሰረት ላይ የቆመ ተåማዊ ስርአት?i
ሸንቁጥ አየለ (shenkutayele@yahoo.com)
ተመስገን ደሳለኝ ባለፈዉ ሳምንት “አዉራዉን ፍለጋ” በሚለዉ ጽሁፉ በኢህአዴግ ፓርቲ ዉስጥ የስልጣን ሽኩቻ ተፈጥሮአል የሚለዉን ታሳቢ ወስዶ ይህ የስልጣን ሽኩቻም ሀገሪቱን ወደ አጉል ነገር ሊገፋት ይችላል የሚለዉን ስጋቱን አካፍሎናል:: ለዚህ ስጋቱም መዉጫ መፍተሄ አድርጎ ያጠነጠነበት የኢህ አዴግ ፓርቲ አዉራ ማግኘቱ ወሳኝ ሂደት መሆኑን አለዚያ ግን ለሀገሪቱ አደጋ ያለዉ ጉዳይ መሆኑን ሊያመላክተን ሞክሮአል:: ከዚሁ ጋር በማያያዝም የፖለቲካ ፓርቲዎች አዉራ ፍለጋ ክሽፈት የገጠማቸዉ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ዘንድ ጭምር መሆኑንም አብራርቶ አቅርቦአል:: እኔም የተመስገንን ጽሁፍ ካነበብሁ ብሁዋላ “እረ ተሜ ተዉ የምን አዉራ ፍለጋ አመጣህብን? ማንሰላሰል የሚገባን በህግ መሰረት ላይ የቆመ ተåማዊ ስርአት የሚመራዉ ፖለቲካ መቼ ሊኖረን ይችላል የሚለዉን ጉዳይ ነዉ እንጅ” ስል በስልክ ብሞግተዉ እይታህን ለአንባቢዎቻችን እንድታካፍል እድሉን እንሰጥሃለን የሚል መልስ ስላገኘሁ ይህን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ቀጣይነት ወይም ፈዋሽ ፖለቲካዊ መድሃኒት መሆን የሚገባዉ አዉራ ፍለጋ ነዉ ወይስ ተåማዊ ስርአት? የሚለዉን ጭብ በተወሰነ ደረጃ ልዳሰሰዉ እሞክራለሁ::
ከሁሉ ቀድሞ አይን ሊጣልበት የሚገባዉ ጉዳይ ማህበረ ፖለቲካ እና ባህለ ፖለቲካ እሴት ዉስጥ የተሰነቀረዉ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ሰብዕና ነዉና በእሱ ዙሪያ እናጠንጥን :: ፖለቲካ ማህበራዊ ይዘት አለዉ እናም ይህ ማህበራዊ ይዘት ደግሞ መገለጫዉ ማህበራዊ እሴት ነዉ:: ፖለቲካ ባህላዊ ይዘት አለዉ :: ይህ ባህላዊ እሴት መገለጫዉም ያዉ ባህላዊ እሴት ነዉ:: ፖለቲካ በማህበራዊና በባህላዊ መሰረት ላይ ቆሞ እራሱን የሚገልጸዉ ደግሞ በማህበረሰቡ ዉስጥ በሚቀርጸዉ የፖለቲካ ሰብዕና ነዉ:: ይህ የፖለቲካ ስብዕና ደግሞ የሚገለጸዉ ማህበርሰቡ ዉስጥ በተለይም ፖለቲካዉ ያባናል በሚሉ ሀይሎች ዘንድ ባለዉ የፖለቲካ እሴት : የፖለቲካ ቅኝትና አመለካከት : ርዕዮተ አለም : ስለስልጥኣን ያለ ግንዛቤ : ስለ ሀገር መስተዳድር ባለ እዉቀት: ስለ ስልጣን ተፎካካሪዎች ባለ ግንዛቤ : ስለ ጋራ ሃገር ባለ ራዕይና በተያያዥ ጉዳዮች ጭምር ነዉ::
እናም ወደ ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሰብዕና ስንመጣ የሰብዕና መገለቻዎች በሁለት ጽንፎች ላይ ተንጠልጥለው ይገኛሉ:: ወይ ታሸንፈኝና እገዛልሃለሁ አለዚያም አሸንፍህና እገዛሃለሁ በሚሉ ጽንፈኛ እሤቶች የታሸ የፖለቲካ ሰብዕናን ተላብሶ የሚንከላወስ ሀይል እዚህና እዚያ ተሰባስቦ ጎራ ለይቶ ተዳፍጦ ይገኛል:: ይህ ዛሬ አይደለም ትናንትም ከትናንት ወዲያም የነበረ ፖለቲካዊ ሰብዕና ነዉ:: ይህ የፖለቲካ ሰብዕና ታዲያ በአንድ ፓርቲ ስር ለሚሰባሰቡ ሰዎችም ጭምረ በቀጥታ የሚሰራ ጉዳይ ነዉ:: አንዱ ገባሪ ሌላዉ አስገባሪ ሆነዉ አንድ አላማና ራዕይ አለን በማለት በአንድ ሰዉ ዙሪያ ተሰባስበዉ ተåማዊ ስርዓትን ለራሳቸዉም: ለልጆቻቸዉም; ለሀገሪቱም ሳይገነቡ ሌላ አስገባሪ ሀይል አስኪመጣባቸዉ የሚጠብቁ ፖለቲከኞች በግራም በቀኝም ከፊትም ከሁዋላም ሞልተዉናል:: እነዚህ ባንድ ፓርቲ ዉስጥ የተሰባሰቡ ሰዎች ሌላዉ ቀርቶ የስልጣን ክፍተት : የሀሳብ ክፍተት: የአቅጣጫ ለዉጥና አዳዲስ ስትራቴጅአዊ ለዉጥ በፓርቲያቸዉ ዉስጥ ወሳኝ በሚሆንባቸዉ ወቅቶች እንኩዋን የራሳቸዉን አቁዋም ደፍረዉ ለማራመድ ፈቃደኝነት አይኖራቸዉም:: ይህን በቀደሙት ዘመናት ማስተዋል ችለናል:: አንባቢ እዚህ ጋ ልብ እንዲልልኝ የምፈልገዉ የምናተኩረዉ በየፓርቲዉ ዉስጥ አቅም ስላላቸዉ ሰዎች እንጅ ችሎታ ስለሚያጥራቸዉ ሰዎች አይደለም:: ለዚህም ነዉ የራሳቸዉን አቁዋም ደፍረዉ ለማራመድ ፈቃደኝነት አይኖራቸዉም የተባለዉ::
አሁን በተመስገን ትንታኔ መሰረት ግን ያ የሀገራችን የፖለቲካ ሰብዕና ተለዉጦ በርካታ እኔ ያገባኛል የሚሉ ሀይሎች ወይም ግለሰቦች በገዥዉ ፓርቲ ዉስጥ ተነስተዋል:: እዉነት ይህ የተመስገን ታሳቢ እዉነት ሆኖ ከሆነ ኢትዮጵያ በአዉራ ከሚመራ ፖለቲካ ይልቅ በተåማዊ ስርዓት ወደ ሚመራ 2ፖለቲካ መግቢያ ዘመኑዋ እየተቃረበ ነዉ ማለት ነዉ:: ፖለቲከኞቹዋም የሰብዕና ለዉጥ እያመጡ ነዉ ማለት ነዉና ሁላችን የዚህች ሀገር ፖለቲካ ጉዳይ የሚያሳስበን ዜጎች በአድናቆት ልንከታተለዉ የሚገባ ጉዳይ ነዉ:: እንደት?
በአውራ ፖለቲከኛ የሚመራ ፓርቲና ሀገር የሆነ ወቅት ስብራታ ያጋጥመዋል:: ምናልባት አንዱ አዉራ ገለል ሲል ሌላ አዉራ በብዙ ምጥና ጣር ሊያወጣ ይችላል:: ሆኖም ሂደቱ ሰንካላና ቀጣይነት የሌለዉ ነዉ:: ስብራቱም የሚታሽ ወይም የሚጠገን አይደለም:: የፓርቲዉም ሆነ የሃገሪቱ ህልዉና በመጨረሻ መፍትሄ የሚገኝለት ከቆሙበት መሰረት ላይ በብዙ ርቀት ወደሁዋላ በሚደረግ መንሸራተት ይሆናል:: ያም ላጠቃላይ ሀገር ክስረት ነዉ:: በአዉራ ፖለቲከኛ የሚመራ ሀገርና ፓርቲ ህግ : ስርአት እና ተåማዊ አካሄዶች አሉኝ ቢልም እነዚህ ነገሮች የሚኖሩት እሱን እስከተመቹት ጊዜ ድረስ ብቻ ነዉ:: ወይም የሶሻሊዝም የህግ ፈላስፎች እንደሚሉት ህግ የሚያገለግለዉ መቀጥቀጥ ያለበት መደብን ለመቀጥቀጥ ነዉ ከሚል ታሳብ የዘለለ ፍሬ ነገር አንጠልጥሎ አይታይም:: ይህ ማለት ድግሞ ህጉም : ስርአቱም; ተåሙም የሚኖረዉ በአውራዉ ህሊና ዉስጥ ብቻ ነዉ ማለት ነዉ :: ያማለት ደግሞ ተከታታይ ትዉልድ ምንም በወረቀት ላይ : በባህል ዉስጥ : በማህበረሰብ ልቦና ዉስጥ ብሎም በተደራጀ ተåማዊ ስርአት ዉስጥ እየተወራረሰ የሚያዳብረዉ ህግ ላይ የቆመ እሴት የለም ማለት ነዉ ::
የዚህ ነገር ዋና መነሻዉም በፖለቲካ ሂደቱ ዉስጥ የሚሳተፈዉ ሀይል በሀሳብ ፍጭትና ግጭት ብሎም የተሻለዉን የሀሳብ አማራጭና ማዕከላዊ አቁዋምን የመያዝ ሂደት ዉስጥ ስለማይሳተፍ ይህ አካሄድም በህግና በተåማዊ ስርአት የተደገፈ ስለማይሆን በሂደቱ ዉስጥ የሚሳተፉት ሁሉ ስልጣን ይገባናል : ችሎታ አለኝ ከእከሌ ይልቅ እከሌ የተሻለ ነዉ ብለዉ አåማቸዉን በገሃድ ማራመድ ስለማይችሉ አጠቃላይ ሂደቱ ህያዉነት የተላበሰ አይሆንም:: በዚህ መሰል ሂደት ዉስጥ አገር አልፈረሰም ወይም ቀጣይነት አለዉ ብሎ አፍን ሞልቶ መናገር ከባድ ነዉ:: አሁን ተመስገን እንዳነሳዉ በገዥዉ ፓርቲ ዉስጥ ልዩ ልዩ ግለሰቦችና ቡድኖች እኔ እሻላለሁ የሚል የአቅጣጫ ተቁዋሚነት: የፓርቲዉን ስትራቴጅ ቀያሽነት: የስልጣን ብሎም የሃሳብ ባለቤትነት ጥያቄ ካነሱ ግን በልዩ ልዩ አቅጣጫ የሚደረገዉ መሳሳስብ የተሻለዉን ሀሳብ ለመምረጥ ብሎም አማካይና አካታች የሆነዉን አåም ለመዉሰድ ያግዛል:: የተለያዩ ቡድኖችና ግለሰቦች ያገባኛል ብለዉ ሲነሱና አååአቸዉን በግልጽ ሲያራምዱ የሚከተሉት ሁነቶች ሊከሰቱ ይችላሉ:- አንድም ተመስገን እንደሰጋዉ አገር ሊፈርስ ይችላል:: አንድም ማዕከላዊ: ሁሉን አካታች እና ለሀገር የሚበጅ አåም ብሎም በተåማዊ ስርአት የሚመራ ፓርቲ ብሎም ሀገር ሊመሰረት ይችላል::
ሆኖም ሀገር ሊያፈርስ የሚችል አåምን በአሁኑ ዘመን ግለሰብ ወይም ቡድን ይዞ ሊሄድ ይችላል ብሎ ለማሰብ የሚከብደዉ አለማቀፋዊ እዉነታዉና የትኛዉም ሀይል ተነጥሎ ቢንቀሳቀስ የሚያተርፍና የሚያጎለዉን ነገር አስልቶ ስለሚቀሳቀስ ነዉ:: ይህም ማለት ለማንኛዉም ወገን አትራፊ የሚሆንለት የራሱን አåም የተወሰነ ደረጃ ድረስ ገፍቶ የሌሎችን አåም ደግሞ የተወሰን ደረጃ ድረስ ተቀብሎ ማዕከላዊ መስመር ላይ በመቆም የጋራ ጥቅም ያለበት ሁኔታ ላይ መጫወትን ስለሚመርጥ ነዉ:: በተለይም አገርን በ እጁ ጭብጦ በ እግሩ ረግጦ እየገዛ ያለ ሀይል ሀገር ብትፈርስ አይጎዳኝም ስለሆነም እስክትፈርስ ያለዉን አማራጭ እንኩዋን እከተላለሁ ብሎ እዚያ ጽንፍ ድረስ ከሄድ ይሄ የፖለቲካ ስሌት ሳይሆን የቀመር አልቦ ጉዳይ ስለሚሆን ለትንታኔ ምቹ አይመስለኝም::
እያንዳንዱ ሀይል ወዶ ሳይሆን ተገዶ የሌላዉን ህልዉና የሚቀበልበት ሂደት ዉስጥ ብሎም ለሁሉም ህልዉና ወሳኝ ወደ ሆነዉ ማዕከላዊ የአካታችነት: የብዙሃንነት እና የጋራ አሸናፊነት አካሄድ ፍለጋን መባዘኑ አይቀርም:: ይህ አካሄድ ደግሞ ቀጣይነት ያለዉና ለሁሉም ወገኖች የሚበጅ የሚሆነዉ ህግ ላይ በቆመ ተåማዊ ስርአት ሲመራ ብቻ ስለሚሆን ሁሉም ወገን ለለሚመሰረተዉ ተåማዊ ስርአት ቤዉነት ይሰራል:: ይህ ሂደት ደግሞ ተጠናክሮ ከቀጠለ ከገዥዉ ፓርት ወደ ሃገራዊ ፖለቲካ በመሸጋገር ሀገራዊ መልክና ቅርጽ ይይዛል:: በዚህም ሰአት ሀገር በህግ ላይ በቆመ ተåማዊ ስርአት የምትመራበት እድል ይፈጠርላታል::
3ሀገር በተåማዊ ስርአት በምትመራበት ወቅት ፓርቲዉንም ሆነ ሀገሪቱን የሚመራዉ ሰዉ ሚናዉ የተወሰነ: ተለይቶ የተቀመጠና በስርአትና በህግ የተገደበ ይሆናልም ማለት ነዉ:: በህግ መሰረት ላይ በቆመ ተåማዊ ስርአት በሚመራ ሀገር ዉስጥ እንቶኔ እንደ መሪ ሄድ እንቶኔ እንደመሪ መጣ የሚለዉ ጉዳይ የዜጎች ጭንቀት መሆኑ ያከትምለታል ማለት ነዉ:: በሂደትም ማህበራዊና ባህላዊ እሴቱ መቻቻል: አካታችነት : ሁሉም ወገን በሀገሩ ላይ ያገባዋል የሚል እንዲሁም ያንዱ ህልዉና የሌላችንም ነዉ የሚል ጭብጥ ገኖ ስለሚወጣ የፖለቲከኞችም ፖለቲካዊ ሰብዕና በዚሁ መሰረት ይቀረጻል ማለት ነዉ::
ስለሆነም የዚህ ጽሁፍ ጭብጥ አንድ ነዉ:: በእዉነት ተመስገን የጠቃቀሳቸዉ ሀይሎች : ግለሰቦች እና ቡድኖች በገዥዉ ፓርቲ ዉስጥ የፖለቲካ ሂደቱም ሆነ ስልጣኑ ያገባኛል ብለዉ ተፋጠው ከሆነ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ታላቅ የትንሳኤ ቀን መጣ ማለት ነዉ የሚል አዎንታዊ ታሳቢን መያዝ ይገባል:: ፓርቲም ሆነ ሀገር በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ዉስጥ ሲገቡ ከተቀረቀሩበት ማጥ የሚያወጣቸዉና በቀጣይነት መሰረት ላይ የሚያቆማቸዉ በህግ መሰረት ላይ የቆመ ተåማዊ ስርአት ፖለቲካዉን ሲመራዉ ብቻ ነዉ:: ስለሆነም አሁን ኢትዮጵያም ሆነች ገዥዉ ፓርቲ ወይም ተቃዋሚ ፓርቲዎች አንድ ነገር ነዉ ማሰስና መፈለግ ያለባቸዉ:: ያም በህግ መሰረት ላይ የቆመ ተåማዊ ስርአት የሚመራዊ ፖለቲካ:: አዉራ ፍለጋ ግን ማክተም ያለበት የፖለቲካችን እሴት ነዉ ብዬ አስባለሁ::
አገሪቱ አሁንም በህግ መሰረት ላይ የቆመ ተåማዊ ፖለቲካ ሳይመራት ግለሰባዊ አዉራ የሚመራት ከሆነ ግን ገና የፖለቲካ ሃሁ ብዙ አመት በኢትዮጵያ ይቆጠራል:: ፖለቲከኞች ደግሞ ትምህርተ ቶሎ የማይገባቸዉና ሰነፍ ተማሪ ናቸዉ:: ትምህርት ብዬ ስል ዲግሪ የማንጠልጠል ጉዳይን ማለቴ አይደለም:: በርግጥ የመማርና ያለመማር ጉዳይን ማጣቀሴ እንጂ:: እናም የፖለቲካ ሀሁ ዉስጥ የተሰነቀር ሀገር ከፖለቲካ ሀሁ ቢያንስ አቡጊዳ ወይም መልዕክተ አስኪደርስ ስንት ዘመናት ይፈጃል? ያ ማለት በአጭሩ አገር አለ ቢባልም የለም:: ብሎም አንዱ አዉራ ባንዱ አዉራ በተተካ ቁጥር አገርም ሆነ የፖለቲካ ባህል በብዙ እርቀት ወደሁዋላ እየተንሸራተተ ሲዛቁን ማህበረሰብም ማህበራዊ ብልጽግናን በህልም ወይም ከሩቅ አገሮች በስማ በለዉ እያደመጠ የቁጭት ከንፈሩን ይነክሳል:: አንድ ጊዜ የተዋጣለት ህግ መሰረት ላይ የቆመ ተåማዊ ስርአት የገነባች ሀገር ግን የእድገት ባቡር ሃዲዱዋን የመሪ መሰበር ወይም የፖለቲከኛ መለዋወጥ አያንገራግጭባትም::
ሆኖም አሁን ዋናዉ እና እኔ መመለስ የከበደኝ ጥያቄ ወይም ደግሞ ከተልያዩ ሚዲያዎች ላይ ከማነባቸዉ ሀሳቦች ሊያሳምነኝ ያልቻለዉ ነጥብ እዉን በገዥዉ ፓርቲ ዉስጥ ያሉ ፖለቲከኞቻችን እንደሚባለዉ የኔ ሀሳብ ይሻላል : በስልጣን ጉዳይም እኔ ያገባኛል: በሀገሪቱ ጉዳይ እኔ የተሻለ ራዕይም ሆነ ስትራቴጅ አለኝ የሚሉበት ብቃት ላይ ደርሰዋል ወይ የሚለዉ ነጥብ ነዉ:: ይሄዉ ጥያቄም ወደ ተቃዋሚዎች ሲዘምትም በአንድ ፓርቲ ዉስጥ ጸንተዉና ቆመው የፓርቲዉን እና የአዉራን ህጸጽ ከማረም ይልቅ እንደወጥ ቀማሽ ፓርቲ ሲቀያይሩ የሚዉሉ ምሁራን ፖለቲከኞቻችን አይበዙም ወይ? እናስ ማህበረ ፖለቲካ እና ባህለ ፖለቲካ እሴት ዉስጥ የተሰነቀረዉ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ሰብዕና አሸንፌ ልርገጥህ ወይም አሸንፈህ ርገጠኝ ከሚል ጽንፍ ላይ የተንጠለጠለ እሴት ተላቆ በድፍረት እያንዳንዱ የፓርቲ አባል የራሱን ህሳቤ ለማራመድ እዕምሮአዊ ጀግንነት ላይ ደርሶአል ወይ? ለእነዚህ ጥያቄዎች አንድም መልስ የለኝም:: ሆኖም የአጠቃላይ በሁሉም መስክ ያሉ የፖለቲከኞቻችን ፍሬን ላስተዋለ ሰዉ ግን አይይ ……ብሎ ጥያቄዉ በመነሳቱ ከንፈሩ ላይ መራራ ነገር ሳይቸልስበት አይቀርም:: የሆነ ሆኖ ግን ከአዉራ ፍለጋ ይልቅ ሊያሳስበን የሚገባዉ ጉዳይ የሀገራችን ፖለቲካ በህግ መሰረት ላይ በቆመ ተåማዊ ስርአት እንዴት ይመራ የሚለዉ ጉዳይ ይመስለኛል::
FYI: This article has been published on the weekly Amharic Fact magazine
Leave a Reply
You must be logged in to post a comment.