አሸባሪማነዉ ?ሸብርተኝነትስ ምንድነዉ?

አሸባሪማነዉ ?ሸብርተኝነትስ ምንድነዉ?

(ከታሪከ መዝገብ)

ሰሞኑን በኢሀዴግ  ቴሌቪዠንና ሬድዮ የፖለቲካ ድርጅቶች በወጣዉ የአሸባሪ ሀግ ዙሪያ  ከርከር ሲያካሂዱ ተመለክቻለሁ፡፡

በተለይም  በተቃዎሚ የ ፖለቲካ  ድርጅቶቹ  መነሳት የነበረባቸዉን  የታለፉ  የመሰሉኝንና  እኔ የማስታዉሳቸዉን  አያነሳሁ ለሀዝቡ  ለማሰገንዘብ  አወዳለሁ፡፡በመጀመሪያ ኢህአዴግ  የሚባለዉ  ቡድን ሀገሪቱን ከመቆጣጠሩ በፊት  በመላ ሀገሪቱ በተለይም በሰሜኑ የሀገራቸን  ክፍል በሚንቀሳቀስበት  ጊዜ ሰዎችን በጠራራ ጸሀይ ሲገድል ተቆማትን  ሲዘርፍና ሲያቃጥል  ለህግና ደንብ  የማይገዛ  የወንበዴ  ቡድን እንደነበረ  የሚታወቅ ነዉ፡፡

ሀገሪቱንም  ከተቆጣጠረ ወዲህም ቢሆን  ይህንኑ ድርጊቱን  በመቀጠል በተለይም የቀበሌ ገበሬ  የሀብረት  ስራ ማህበራትን፣የከተማዉን  ነዎሪ  ህዝብ    የህብረት  ሱ ቅ አገልግሎት  መስጫ  ተቆማትን፣  የወጣቶች፣  የሴቶች  ድርጅት ንብረቶችን፣   የሙያ  ማህበራት  ተቆማትን ፣ለምሳሌየኢትዮጵያ  ሰራተኞች  ማህበር  ንብረቶችን፣  የኢትጵያ መምህራን  ማህበር ንብረቶችን  ፣የወባ  መከላከያ ንብረትን፣  በአሰብ ወደብ ይገቡ የነበሩ የነጋዴዉንና የህዝቡን ንብረቶችን፣  የግልና  የቡድን ጥቅማቸዉን ያከማቹት ኢሀዴጎች ናቸዉ ፡፡

ህዝቡን ተረጋግቶ እንዳይኖር ከኖረበት ቀየና መንደሩ ማፈናቀል ፣ንብረቱን ዘርፎ ማባረር ፡በላዩ ላይ ቤቱን ማፍረስ  ፣የህዝቡን መሬት  ያለፈቃዱ በግድ እየነጠቁ  መሸጥ መለወጥ  ፣ህዝቡ የኔ የሚለዉ ንብረት  ሀብት  ሀገር  እንዳይኖረዉ  ማሳጣት፣  አትናገር፣ አትጻፈ  ፣አታስብ ፣ ከጎደኞችህ ጋር  ተገናኝተህ አታዉራ፣  አትወያይ፣ ማለት  አሸባሪነትና ሽብርተኝነት አይደለም፡፡

ህዝቡ  የተረጋጋ ኑሮ እንዳይኖር ማስፈራራት፣  እኔ ያልኩህን ብቻ ተቀበል ማለት፣ ለምርጫ የሰጠዉን  ድምጽ መንጠቅ  ፣ያ ለ  ፍርድ ቤት ትእዛዝ  ማሰር፣  ቤታቸዉን መበርበር ፣ የማያቁትን ነገር ተናገሩ በማለት አካላዊ  አእምሮአዊ  ሞራላዊ  ጉዳት  ማድረስ፣ በሀሰት ምስክር  በማቅረብ  እንዲመሰክሩ  ማድረግ ፣ በድብደባ  ወንጀለኛ ነኝ  ብሎ በራሱ ላይ እንዲመሰከር ማስገደድ ፣ ከዚህ የበለጠ ህገ መንግስትንና  የሰብአዊ መብትን  የጣሰ አሸባሪና ሽብርተኝነትስ  ከየት ይመጣል ፡፡

በሀሰት ምስክር በማቅረብ  በድበደባ ወንጀለኛ  ነኝ  ብሎ  በራሱ  ላይ እንዲመሰክር ማስገደድ ወዘተ ህዝብን የማሸበር የነበሩ ያሉና  ወደፊትም እነዲቀጥሉ  አየተሰራባቸዉ ያሉት የኢሀዴግ  መገለጫዎች  ናቸዉ፡፡አሸባሪነት እኮ ማስፈራራት ነዉ፡፡ አጅ  እንቆርጣለን  እግር  እንቆርጣለን  እርምጃ እንወስዳለን  ማንም  አያድናችሁም  እያሉ ባደባበይ ህዝቡን ያሸብሩት  ኢሀአዴጎች  አይደሉም ፡፡ ይህ ደግሞ የግለሰቦችን ትቅም  ለማርካት የሚሊዮኖችን  በሀግ የተደነገገ ሰብአዊ  መብትን፣  የዜጎችን የመምረጥና  የመመረጥ  የፖለቲካ

መብትን፣  የዜጎችን የመኖር፣  የመስራት፣  ከቦታ ቦታ የመዘዋወር ፣በአካላዊ  ደህንነት የመጠበቅ መብትን፣    የመናገር፣  የመጻፍ ፣የመሰብሰብ ፣ የመብላት የመጠጣት  መጠለያ  የማግኘት የተፈትሮ  መብትንም  ሙሉ በሙሉ  በመደፍጠጥ ዜጎችን  እያሸበረ  መዉጫ መግቢያ ያሳጣቸዉ ኢህአዴግ  ነዉ፡፡ ይህም የሆነዉ ቡድናዊ  ፍላጎትን ለማርካት  የሌሎችን  ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ  መብትን የጨፈለቀ  ነዉ፡፡
አሸባሪነት  እኮ ፈንጁ ወይም ቦምቡ ወይም ጥይት በመተኮስ ብቻ የሚከናወን  በሰወች ወይም በንብረት ለይ ጉዳት ማድረስ ብቻ  አይደለም፡፡ ሽብርተኝነትም የግልን ወይም የጥቂት ቡድኖች ፍላገት ለማሳካት ሰወች በግልም ይሁን በቡድን  የሚፈጽሙጽ ት  የሌሎችን  ሰብአዊ  ዲሞክራሲያዊ  ፖለቲከዊ  ተፈጥሮአዊ  መብትን  በመደፍጠጥ  የኛ ፍላጎት መቀጠል አለበት በሚሉ ሰወች  የሚፈጸም እኩይ ተግባር  ነዉ፡፡
ታዲያ  ኢህአዴግ  የእርሱ  ፍላጎት  ባይሆን ኖሮ አሸባሪነትንና  ሽብርተኝ ነትን ለምን ናፈቀዉ፡፡የኢትዮጵያ  ህዝብ ፣ ፖለቲከኛች  ፣ጋዜጠኞች፣ እንዲሁም  የተለያዩ የአለም  ሀገራት መሪወች፣  አምባሳደሮች፣ የአዉሮፓ  ህብረት፣ የአለም  የሰብአዊ  መብት ተሞጋች ድርጅቶች፣  ባነድ ድምጽ  ኢህአዴግ እያወጣዉ ያለዉን  የአሸባሪነት ሀግ  ተቃዉመዉታል፡፡  ህዝብ  ያለዉንስ  ለምን መስማት አልፈለገም  ፡፡ይህ  ደግሞ  ለስልጣኔ  ያሰጉኛል በማለት  የሚጠላቸዉን  ሁሉ  ምክንያት እየፈለገ  ፐለቲከኞችን  ጋዜጠኞችን  የፖለቲካ ተንታኞችን  የብእር ሰወችን  ለማጥቃት የምትጠቀምበት ህጋዊ   ሸፋን ነዉ ሲባል  አይኑን  ጨፍኖ ለመከራክር ይሞከራል ፡፡

ኢትዮጵያዊም  ሆነ ማንም  በአለም  ላይ የሚኖር  የሰዉ ዘር ሁሉ  ማንም  ሰዉ በማንም  እዲገደል  አካሉን  እንዲያጣ፣  ንብረቱ  እንዲወድም ፣ የሚፈልግ   የለም ፡፡ እንደዚህ  አይነት ሰወች ይኖራሉ ተብሎ  ቢታሰብ እንኳየህዝብንና ሀገርን ቅድሚያ ጥንቃቄ ለመዉሰድ  የሀግ ከለላን  መኖር የሚቃወም  አይኖርም  ፡፡ ነገር ግን ይህ  ሀግ  ከመዉጣቱ በፊት  ከፖለቲካ  ትርፍነት  ባሻገር  የህዝብንና የሀገርን  ጥቅም  ያስቀድም ነዉ ጥያቄዉ፡፡አነድ ህግ  የሚከበረዉም ሆነ የሚያስከብረዉ  በህዝብ እና ህዝብ ብቻ ነዉ ፡፡ ስለዚህ ነዉ  ህዝቡ በእኔነት  ስሜት  ከወዲሁ እራሱንም  ሀገሩንም እንዲከላከልና የድርሻዉንም  እንዲወጣ  ልምከርበት  ልመንበት  ኢህአዴግ  ሆይ  ብቻህን  ልትወጣዉ  አትችልምና  ጉደዩን  የ ጋራ እናድርገዉ  በማለት የሚጠይቀዉ ፡፡ ሲጠይቅ ይህ የሚሆነዉ  በኢሀዴግ  መቃብር ላይ ነዉ በማለት  ግብዛዊ  የስልጣን  ጥሙን  ለማርካት  ሲራወጥ  ይስተዎላል  ፡፡

አሸባሪነትን  ለማስረዳት የቀረቡት የኢሀዴጉ ተከራካሪ   አቶ  ሽመልስ ከማል ከዛሬ  22 አመት በፊት በሶማሌ በኦሮሞ  በደቡብ ክልሎች  በአማሮች  ላይ  የተፈጸመዉን  ዘር የማጥፋት ዘመቻ  የግፍ ጭፍጨፋ በተለይም የበደኖዉን በብርዙ  ሽህ  የሚቆጠሩ አማሮችን ከነ; ነፍሳቸዉ  በበደኖ  ገደል የተሰደዱበትን እዉነት  በአሸባሪነት  የተፈጸመ  ግፍ  ነዉ በማለት  በድፍረት  ሲመሰክሩ ሰማሁ ፡፡ ይሀ ደግሞ  አቶ  ሽመልስ  ከማልን  ጎሽ አበጀህ  በመባል ሊያስመሰግናቸዉ  ይገባል ፡፡ነገር ግን  ጭፍጨፋዉን  የፈጸመዉ  አሸባሪዉ  ኦነግ ብቻ ነዉ ማለታቸዉ  ከኢሀዴግ ድርጅታቸዉ  የተካኑትን  ዉሸት በመተዉ በጀመሩት  አንደበታቸዉ  በዋናነት  ድርጊቱን  የፈጸመዉ  ፊታዉራሪዉ  ወያኔ መሆኑን  በድፍረት መናገርና  ወያኔም በአሸባሪነት  መፈረጅ  እንደሚገባዉ  አቆማቸዉን ለህዝብ ግልጽ  ማድረግ ይጠበቅባቸዎል  ፡፡

ይሀ ሲሆን የአሸባሪ  ሀጉ እንዴት ተፈጻሚ  እንደሚሆንና አቶ ሽመልስ ከማልም  አቃቢ ሀግም  እንደመሆነቸዉ መጠንም እነማንን  ለፍረድ  ማቅረብ  እንዳለባቸዉ   እንዲሰሩና  ለሀግ የበላይነት እንዲቆሙ  ድፍረቱ  ይኖራቸዋል ፡፡   አማሮች  ላይ ግፍ የተፈጸመዉም በበደኖ  ገደል ብቻም  ሳይሆን በአሰቦት ገዳም  በዋሻ  ዉስጥ እያሉ ዋሻዉን በመዝገት ከነ-ህይወታቸዉ በእሳት የተቃጠሉትንም  የሀይማኖት  አባቶች  በግፍ ያለወንጀላቸዉ  አማራ በመሆናቸዉ ብቻ የተጨፈጨፉ መሆናቸዉን  አቶ ሽመልስ ከማል  ባላቸዉ መረጃ መሰረት ለህዝቡ ግልጽ ማድረግ  ይጠበቅባቸዎል ፡

ይህ ብቻም አይደለም  የኢሀዴጉ ጠቅላይ ሚኒስትር  የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ በሶማሌ ክልል በመገኘት ባደረጉት ንግግር  በዘህ  አካባቢ የሚኖሩት አማሮች  ከዚህ  በፊት  እናንተን  ሽርጣም እያሉ ሲገዙአችሁ  የነበሩ  ስለሆነ  አሁን  የምትፈልጉትን  እርምጃ  መዉሰድ  ትችላላቸሁ በማለት ባስተላለፈዉ  መልእክት  የተጨፈጨፉትንም አማሮች  አቶ ሽመልስ ከማል በጀመሩት  አካሄድ  አሸባሪወቹ ወያኔና  ኦነግ  በገራ የፈጸመት  በመሆኑ  ወያኔም  አነግም  በገራ በፈጸሙት ወንጀል በአሸባሪነት እንዲጠየቁ  አቶ ሽመልስ ከማል  የአቃቤ ህግ ሙያቸዉን ተጠቅመዉ  ለፍርድ  ማቅረብ እንዳለባቸዉ  ላስገነዝብ  እወዳለሁ ;;

በሀረር ጋራ ሙለታና በዙሪያዎ  በሚገኙ ወረዳወችና ቀበሌ ወቸ  የተፈጸመዉ አሰቃቂ ግድያ  ሁሉ አነድም  ሳይቀር ዛሬ የአሸባሪ ህግ ለማዉጣት እና በድጋሚ  በህግ  ሽፋን ስም  ሌሎችን ለማጥቃት ከመሯሯጥ  በፊት በአሸባሪ  ስራ ላይ ተሰማርተዉ  የነበሩትን    ወያኔወች ሁሉ ልክ እንደ ኦነጎቹ  በህግ ሊጠየቁ ይገባቸዎል አላለሁ ;;   ይህ ሲሆን ደግሞ አቶ ሽመልስ ከማል ከብዙ አመታት በኋላም ቢሆን  ወደ አእምሮአቸዉ በመመለስ የሀግ የበላይነት ከወያኔም ከኢሀዴግም በላይ መሆኑን በተግባር ሲያስመሰክሩ   እዉነትን  ከነ ሙሉ ወርድና ቁመቷ  እንዲናገሯት ያስፈልጋል፡፡

አቶ ሽመለሰ ከማልና አቶ ጌታቸዉ ረዳ ምን ያህል መረጃ እንዳላቸዉ ባለዉቅም የሶማሌ ነጻ አዉጭ ግንባርን  አሸባሪ ነዉ ሲሉ በከርክራቸዉ  ላይ ሲናገሩ ተደምጠወል፡፡ መቸም በኢሀዴግ ቴሌቪዠንና  ራደዮ  እዉነት መቸ እንደሚነገር ባላዉቅም ከአምስት አመት በፊት ይመስለኛል  አቶ አባይ ጸሀይ የፌደረል ጉደዮች ሚኒስትር በነበሩበት ጊዜ  አሸባሪ  ተብሎ  በወያኔ ኢሀአዴግ  የተፈረጀዉ ኦብነግ  ጋር የኦብነግ አሸባሪ ቡድን ህገ መንግስቱንና  ህገ መንግስታዊ  ስርአቱን አክብሮና  ተቀብሎ  በሰላማዊ  መንገድ  ለመንቀሳቀስና  በልማትና በዴሞክራሴዊ ግንባታዉ ላይ  አብረዉ  ለመቀጠል ትጥቃቸዉን  ፈትተዉ  እጃቸዉን  ሰጥተዎል ፡፡ በማለት በልማደኛዉ  ቴሌቪዠንና  ሬድዮ  አይተናል  አድምጠናል ፡፡አቶ አባይ ጸሀይም  በተደጋጋሚ ይህንኑ  ሲናገሩ አንደነበር እሩቅ ሳንሄድ ማስረጃዉን  ከቴሌቨዠን ደርጅት  ማግኘት ይቻላል ፡፡

በአሁኑ ሰአትም ኢሀዴግ ከህዝቡ ጀርባ  አሸባሪ በማለት ከፈረጃቸዉ ድርጅቶች  ጋር በኬንያ  እያደረገዉ  ያለዉን  ድርድርም  አቶ ሸመልስና  አቶ ጌታቸዉ  አሸባሪዉ  ማን  እንደሆነ  በግልጽ  ማስቀመጥ  ይጠበቅባቸወል ፡፡ ያለበለዚያ  በህዝቡ  ዘንድ  ኢሀዴግም  አሸባሪ  ነዉ የሚል  ድምዳሜ ላይ  መድረሱ አይቀርም  ፡፡ምክንያቱም የአሸባሪ ህጉ  ከአሸባሪ  ድርጅቶችም  ሆነ ግለሰቦች  ጋር  ከተነጋገረ  ከተጻጻፈ  እንደሽብርተኛ  ይቆጠራል በማለት  ይደነግጋል  ፡፡

በተጨማሪም  አቶ ሽመልስና  አቶ ጌታቸዉ ከ22 አመት በፊት በበደኖ  ገደል  የተፈጸመዉን  ግፍ ካነሱት እና  እወነታዉን  ከመሰከሩት  አይቀር  በ1998 አመተ  ምህረተ በጅማ ዞን በከርስትና  አምነት ተከታዮችና  በቤተክርስቲያናቸዉ  ላይ  ሰዉ  ሆኖ የተፈጠረ  ሊፈጽሙዉ  የማይገባ  ዘግናኝ  ድርጊት ነዉና  ድርጊቱን  የፈጸሙትን  ሁሉ  አቶ ሽመልስና አቶ ጌታቸዉ  በነካዉ አጃቸዉ   ኦብነግ  ኦነግ ወይንስ  ኢሀአዴግ   በማስረጃ አስደግፈዉ ለህዝቡ  ማቀረብ  ይጠበቅባቸወል ፡፡

ዉሸት በመናገር የሚታወቁት የኢሀዴግ ባለስልጣናት  ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ  እጅግ  በጣም  ትላልቅ ዉሸቶችን ዋሽተዋል ፡፡ዛሬ በህይወት  የሌሉት አቶ መለስ ዜነዊ  ስለ  ኦነግ ሲናገሩ(ኦነግን አከርካሬዉን  መትተን ለአንዴና  ለመጨረሻ ጊዜ  አጥፍተነዋል  ፡፡ ከእንግዴህ  ወዲህ ኦነግ አለ ብለዉ ቢነግሩአችሁ  የነገሩአችሁን  ሰዎች  ዉሸታሞች   በሉአቸዉ በማለት በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡  ታዲያ  የእርሳቸዉን ራእይ እናስፈጽማለን  የሚሉት ኢህአዴጎቹ  አቶ ሽመልስ እና አቶ ጌታቸዉ  አነግ አሸባሪ ነዉ በማለት ለህዝቡ በሚዲያ ሲናገሩ ዉሸታቸዉን ነዉ ማለት ነዉ  ፡፡

ወይነስ የእርሳቸዉን  ራእይ እናስፈጽማለን  መፈክር  እነርሱን አይመለከትም ማለት ነዉ ፡፡ አከርከሬዉን ተመትቶ ግብአተ መሬቱ የተፈጽ መዉ  ኦነግስ  ከየት መጥቶ ነዉ ለሸብር ጥቃት ስጋት የሆነዉ ፡፡ነዉ ወይንስ እንደተባለዉ  በሀገር ዉሰጥ ሆነዉ በሰላማዊ መንገድ  የሚታገሉትን  ፖለቲከኛች  ጋዜጠኛች  የብእር  ሰዎች ለማጥቃት የወጣ የአሻባሪ ሀግ ነዉ፡፡በሌላ መልኩ በገምቤላ ህዝብ ላይ የደረሰዉን የጅምላ ጭፍጨፋ የፈጸመዉ  ኦብነግ  ኦነግ  ሻቢያ  ወያኔ  ወይንስ ማነዉ ፡፡

የ1997 አመተ ምህረት ግንቦት 7 ምርጫን ተከትሎ በጠራራ  ጸሀይ በገፍ  ግንባር  ግንባራቸዉን   ተመትተዉ ለተገደሉት ተጠያቂዉ  ኦነግ  ኦብነግ  ሻቢያ  ወይነስ  ማን  ይሁን  ለጥያቄዉ  መልስ እንዲሰጡን አቶ ሽመልስ ከማልንና አቶ ጌታቸዉ ረዳን እጋብዛሉ፡፡ታዲያ  በእነዚህ  ሁሉ  ችግሮች  የተተበተበ ቡድንስ እንዴት የአሸባሪነትና  የሽብርተኝነት  ሀግ ብቻዉን ሊያወጣ  ይችላል፡፡ተአማኒነትስ  ይኖረዋል ፡፡ይልቁንስ የሚበጀዉና   የሚያዋጣዉ  ሀጉ የሀገሪቱን  ደህንነትና  የህዝቡን ሰለም  አንዲያስከብር ከተፈለገ ይህ ሀግ ተሰርዞ የሀገሪቱን  ህገ  መንግስትና አለም  አቀፍ የሰብአዊ መበት  ህግ ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ ህግ ሆኖ እንዲወጣና በህዝብ  ተአማኒነት ኖሮት ለተፈጻመነቱ መሳካት ህዝቡ በእኔነት መንፈስ የደርሻዉን እንዲወጣ  የሀግ  ባለሞያዎችን፣ ፖለቲከኛችን ፣ጋዜጠኛችን፣  የሀይማኖት መሪዎችን፣  ምሁራንን፣ የተመሪ ተወካዮችን፣ እና ሌሎችንም ያገባናል የሚሉ ባለድርሻ አካላትን ያካተተ  ዉይይት ተደርጎበት  የአሸባሪ ህጉ እንዲወጣ  ህዝቡ ባገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ ድምጹን  ማሰማት ይኖርበታል፡፡

በመጨረሻም  ለክርከር ቀርበዉ የነበሩት የፖለቲካ  ድርጅቶች ከላይ ለማንሳት የሞከርኩአቸዉን  በህዝብ ላይ የደረሱ የሽበር  ጥቃቶች  ባለማንሳታቸዉ  ይልቁንም  የኢሀዴጉ ተከራካሪ  አቶ ሽመልስ የተፈጸመዉን ግፍ  የሽብር ጥቃት ነዉ በማለት ምስክርነታቸዉን ሲሰጡ  ተቃዋሚወቹ  ግን  የሽብር ጥቃቱን  ወያኔም  አብሮ  የፈጸሙዉ  በመሆኑ በአሸባሪነት  ሊፈረጅ  ይገባዋል በማለት  አስምረዉ  ማለፍ እንደነበረባቸዉ  ሳልጠቅስ ማለፍ እንደሌለብኝ  ላሰምርበት  እወዳለሁ፡፡

 

ከታሪከ መዝገብ  ነኝ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.