ኢትዮጵያ ጥርስ የገባች ሀገር :- ሶስቱ የጥቃት ኢላማዎች
ኢትዮጵያ ጥርስ የገባች ሀገር :- ሶስቱ የጥቃት ኢላማዎች
(ከተሪክ መዝገቡ)
የፋሽሽት ወራሽ ባንዳ ተልእኮ
የወጭ ወራሪ ሀይሎች ኢትዮጵያን በመዉረር ሉአላዊነቷን በመድፈር የህዝቡን መብት፣ ባህል ፣እምነት፣ቋንቋ፣ ወዘተ ለማጥፋጥ ቆርጠዉ፣ የተነሱባቸዉ ጊዜያቶች፣ በርካታ፣ ናቸዉ፡፡ የኢትዮጵያን አንድነትና ደህንነት በመቃረን ግብጾች፣ ሱዳኖች፣ሊቢያዎች፣ ኢራቆች ፣ኢራኖች ፣ ሶሪያዎችና ሶማሌዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ሲፈታተኑ እንደነበር የሰዉና የታሪክ ማስረጃዎች ህያዉ ምስክሮች ናቸዉ፡፡
የአዉሮፓ ሀገራትም ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት የመያዝ ፍላጎታቸዉን እዉን ለማድረግ በተደጋጋሚ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ሙከራ ያደርጉ እንደነበር ታሪክ እዉነተኛ የምስክርነት አሻራዉን አስቀምጦ አልፎአል፡፡ ለዚህ ደግሞ በዋናነት የምትጠቀሰዉ ሀገር ኢጣሊ ነች ፡፡ጣሊያን ኢትዮጵያን በቀትታ ከመዉረሯ በፊት በተዘዋዋሪ መንገድ ለግብጾች፣ ለሱዳኖች ፣ለየመኖችና ለሶማሌዎች የተለያዩ እርዳታዎችን እያደረገች የሀገሪቱን ዳር ድንበርና የህዝቡን ሉአለዊ መብት ስትዳፈር እና ስታስደፈር የነበረች ሀገር ናት ፡፡
ይህ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያን የማጥቃት እቅድ በቀድሞ የኢትዮጵያ ነገስታቶች የሀገሬን ዳርድንበር የህዝቤን መብት አላስደፍርም ባይነትና ህዝቡ በሚከፍለዉ መስዋእትነት የሀገሪቱ ዳርድንበርና የሕዝቡ መብት በጠላት ሳይደፈር ለብዙ ዘመናት በደምና በአጥንት ተጠብቆ ኖሮአል፡፡ ጣሊያን በተዘዋዋሪ መንገድ በምታደርገዉ እርዳታ ኢትዮጵያን የማድከምና የምትፈልገዉን ዉጤት ሊያስገኝላት ባለመቻሉ በቀጥታ ወረራ ለመፈጸም የሚያስችላትን አቅም አዘጋጅታ በ1880ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ህልሟን እዉን ለማድረግ ወረራ ፈጸመች ፡፡ የሀገሪቱን ዳር ድንበር ጣሰች ፡፡የህዝቡንም ሉአላዊ መብት እረገጠች፡፡
ጣለያን በኢትዮጵ ያ ላይ ወረራ በፈጸመች ወቅት ከየመን፣ ከሱዳን፣ ከሶማሌ፣ ከግብ ጽ፣ የተዉጣጣ የአካባቢ ጠቆሚና መንገድ መሪዎችን በመጠቀም ጦሯን በቀይ ባሀርና በመጽዋ አካባቢ በማከማቸት ሰላዮችን ደግሞ አስመራና አዲስ አበባ በመላክ የወረራ አቅዷን ለማሳካት የቻለቸዉን ሁሉ አደረገች ፡፡በመረጃ አሰባሰብና በሰለጠነ የጦር አሰላለፍ፣በጦር መሳሪያ፣ በትጥቅና ስንቅ ፣ በአቅድ በመመራት ከኢትዮጵያ አጅግ በጣም እንደምትበለጥ ታሪክ ነገሮን አልፎአል፡፡
ይህንን፣ የተዋጣለት አደረጃጀትና ዝግጅት በመጠቀም ቀሰ በቀስ የኢትዮጵያ አካል የሆነችዉን ኤርትራን በመዉረር የቅኝ ግዛት ዘመቻዋን ጀመረች ፡፡ኤርተራን በቁጥጥር ስር ካዋለች በኋላ ጉዞዋን ወደ ትግራይ ክፍለ ሀገር በማቅናት ገሰገሰች፡፡ ቁጥራቸዉ ብዙ የሆነ የኤርትራና የትገራይ ባንዳዎችን በሰላይነት ፣ በመንገድ መሪነት፣ በተዋጊነት፣ በስነቅ አቀባይነት ፣በደጀንነት አሰለፈች፡፡
የጣሊያን ወረራና የኢትዮጵያ መወረር ያሰጋቸዉ የኢትዮጵያ ህዝብና ንጉሱ ምክር ጀመሩ ፡፡በጥቃቅንና አነስተኛ ምክንያቶች የተጣላንና የተኳረፍን ሁሉ ይቅር አንባባል ፡፡ ይልቁንም የሀገራችንን ዳር ደንበር ሰብሮ በመግባት ህዝባችንን፣ ሀገራችንን፣ ባህላችንን ፣እምነታችንን፣ ማንነታችንን፣ቋንቋችንን፣ ወዘተ ሊያጠፋና ሁላችንንም ሊያወድመን የመጣ ጠላት መጥቶብናልና የኛን መገፋፋት ወደጎን በመተዉ በገራ የገራ ጠላታችንን መክተን የሀገራችንን ዳር ደንደበርና የሀዝባችንን ሉአለዊ መብት እናስከበር፡፡ያለበለዚያ የምንደሰትበትም ሆነ የምናኮረፍበት ብሎም ብንሞት እንኳን የምንቀበርትም ሀገርና መሬት አይኖረንም፡፡ስለዚህ በሰሜን በኩል የመጣዉን ጠላት አሳፍረን ለመመለስ በአንድነት ዘመቻችንን ወደ ተወረሩት ከፍለ ሀገሮቻችን እንዲሆን በማለት ንጉሱ ለህዝቡ ጥሪ አቀረቡ ፡፡
ህዝቡም የንጉሱን ጥሪ በመቀበል ከመንግስት ምንም ነገር ሳይጠብቅ የራሱን ስንቅ ና ትጥቅ በማዘጋጀት ፊቱን ወደ ሰሜን አቀጣጫ በመዞር ከአቅመ ደካማና ህጻናትን ከሚጠብቁ ሴቶች በስተቀር ጉልበት ያላቸዉ ሴቶችና ወንዶች ሁሉ ወደ ጦር ግንባር ተጓዙ፡፡ ኢትዮጵያዊያኑ የመጣባቸዉን ወራሪ ሀይል ለመመከትና ከሀገራቸዉ የግዛት ድንበር ለማባረር በፍጹም እህትማማችነትና ወንድማማችነት መንፈስ አንዱ ለሌለዉ መኖር ህይወታቸዉን ለመስጠት ዝግጅታቸዉን አጠናቀዉ የመጣባቸዉን ጠላት ፈት ለፊት ገጥመዉ ጠላጣቸዉን ጥለዉ እነርሱም ወድቀዉ የሃገራቸዉን ዳርድንበር እና የበንዲራቸዉን ክብር በደማቸዉና በአጥንታቸዉ ለማስከበር ጠላት እከተመበት ቦታ ድረስ በመሄድ የካቲት 23ቀን 1888 አ.ም ባንዳንና የጣሊያን ወታደሮችን አድዋ ላይ በቁርስ ሰአት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ከሰአት በኋላ የኢትዮጵያ ባነዲራ በአደዋ ተራሮች ላይ በጀግኖች ደምና አጥንት በተከፈለ መስዋእትነት ከፍ ብሎ ተዉለበለበ፡፡
ተደራጅቶ ማንም አይነካኝም በማለት የጀግኖች ሀገር የወረረዉ የጣሊያን ወታደር ሙት ፣ቁስለኛና ምርኮኛ ሲሆን አንዲሁም፣የተረፈዉ እግሬ አዉጭኝ በማለት በመጣበት እግሩ እየፈረጠጠ ተመለስ ፡፡የኢትዮጵያ ዳር ድንበርም በሚነድ እሳት፣ በሚፋጅ እረመጥ የሚጠበቅና ተከብሮ የሚኖር መሆኑን ለአለም የሰዉ ዘር አበሰረ ፡፡ኢትዮጵያን ለመዉረር ለሚመኙት ሁሉ መቀጣጫ መሆኑን አረጋገጠ ፡፡ባንዳም መፈጠሩን ጠላ ፡፡ መሬት በቁሙ ብትዉጠዉ መረጠ ፡፡ወንድሞቹኑና እህቶቹን የወጋበት ክንዱ ዉሀ ሆነ ፡፡በጀግኖች እህቶቹና ዉንድሞቹ እግር ስር በመዉደቅ ምሀረትን ለመነ፡፡ ጀግናዉ የኢትዮጵያ ህዝብና ንጉሱ የተማረከወንና የቆሰለዉን የኢጣሊያ ወታደርና የባንዳ ጦር ምህረት ሰጥተዉ ወደመጡበት እንዲመለሱ ፈቀደ፡፡
በኢትዮጵያ ህዝብ አድዋ ላይ በተሸነፈዉ የጣሊያን ወታደር የተቆጣዉ የኢጣሊ ህዝብ በሮም አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ በመዉጣት ክርስፒ ይዉረድ ሚኒልክ ይንገስ በማለት ቁጣዉን ገለጸ፡፡ በአድዋ ድልም አለም ተደመመ ፡፡ነጭ በጥቁር ህዝብ ለዚያዉም በኋላቀር መሳሪያ ተሸነፈ ፡፡ ጥቁር የሰዉ ዘር ማሸነፍ እንደሚችል ተረጋገጠ ፡፡ ጥቁርና ነጭ የሰዉ ዘር ሁሉ እኩል መሆናቸዉ የአደዋ ድል አረጋገጠ ፡፡
ኢትዮጵያዊያን የከፈሉትን መስዋአትነት እና ያገኙትን ድል በሞዴልነት በመዉሰድ አፍሪካዊያን በቅኝ ከሚገዙአቸዉ ነጮች ነጻ ለመዉጣት የነጻነት የትግል እንቅስቃሴ ጀመሩ ፡፡በአዉሮፓና ፣ በአሜሪካ እዲሁም በሌሎች የአለም ሀገሮች የሚነሩ ጥቁሮች በነጮች ላይ የተቃዉሞ ድምጽ አሰሙ ፡፡አፍሪካዊያን ነጮችን ከሀገራቸዉ በማሶጣት አንደ ኢትዮጵያዊያን ነጻነታቸዉን በማወጅ ከነጮች እኩል መኖር ጀመሩ፡፡
(ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም ) እንደሚባለዉ ጣሊያን አደዋ ላይ የተቀጣችዉ ቅጣት አልበቃም ብሏት ለአርባ አመታት ዝግጅት አካሄደች ፡፡በአለም ለይ የተወገዘዉን የመርዝ ጋዝ በመጠቀም በ1928 አ.ም በኢትዮጵያዊያን ለይ ይህ ቀረሽ የማይባል ግፍ ተፈጸመ ፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን አለም በሙሉ ኢትዮጵያን አረሳት ፡፡አንድም ሀገር ተዉ የሚል ጠፋ ፡፡ጣሊያንም የ1888 አ.ም ቂሟን ተወጣች ፡፡ህዝቡን እየሰበሰቡ እጅ ቆረጡ ፡፡ እግር ቖረጡ ፡፡ጡት ቆረጡ፡፡ በመትረጌስ አጨዱ፡፡ በታንክጨፈለቁ ፡፡ የኤርትራና የትግራይ ባንዳዎች በድጋሚ ለጣሊያን አድረዉ የመሀል ሀገር ወንድሞቻቸዉን እና እህቶቻቸዉን ብልት ቆረጡ፣ ጡት ቆረጡ፣ ልጃገረድ ሴቶችን ደፈሩ ፣የአባወራ ፣ሚስቶችን ደፈሩ፣ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ገደሉ፣ ቤተክርስቲያን አቃጠሉ ፡፡የነጋሲነት ዘር ያላቸዉን ሁሉ እየጠቆሙ አስገደሉ ፡፡ይህንን በመፈጸማቸዉ በኢጣ ሊያ መንግስትና ጀነራሎች ማእረግ ተሰጣቸዉ ፡፡ተሸሙ ተሸለሙ( ሙንጣዝ ሹምባሽ) ተባሉ ከሀገራቸዉ፣ ከወገናቸዉ ክብር ለጣሊያን እንቁላል መቀቀልን፣ ጫማ መጥረግን፣ ሴት ማቅረብን፣ እሳት ማንደድን፣ ልብስ ማጠብን፣ገላ ማጠብን፣ ሽንት ቤት ማጽዳትን፣ባጠቃላይም ባሪያ መሆንንመረጡ፡
ጣሊያን የኢትዮጵያን ህዝብ ለመግዛትና ጣሊያን ቀዱስ ነዉ ለማስኘት ኢትዮጵያዊዉን ሊቀጳጳስ ብጹእ አቡነጴጥሮስን በማሰርና በአደባባይ ቆመዉ ህዝቡ ለጣሊያን መንግስት እንዲገዛ ስለጣሊያን ሀያልነት፣ ቅዱስነት እንዲሰብኩለት ፣ህዝቡ የእርሳቸዉን ትእዛዝ የማይቀበል ከሆነም ግዝት እንዲያደርጉ ባስገደዳቸዉ ወቅት ታላቁ አርበኛ የእምነትና የሃይማኖት ተጋዳይ ብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የተሰለፈዉ ወታደር ፣የታጠቀዉ መሳሪያ ፣የቆመዉ ታንክና መድፍ ሌላም ሌላም ሳያስፈራቸዉና ሳያስድነግጣቸዉ ጣሊያን ያዘዛቸዉን ባለመቀበል የካቲት 12 ቀን 1928 አ.ም ታላቅ ሀይማኖታዊና ሀገራዊ አደራቸዉን ለመወጣት የሚያበቃቸዉን ንግግር በማድረግ ሀላፊነታቸዉን ተወጥተዉ በክብር አረፉ፡፡
ለኢትዮጵያም ህዝብ ያስተላለፉትም መልእክት ቃል በቃል ባይሆንም የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ የኢጣሊያን መንግስት እምነት ፣ባህል ፣ታሪክ፣ሀይማኖት፣ወዘተ የለዉም ፡፡ ወንድሞችህን ፣እህቶችህን በግፍ እየገደለ ነዉ ፡፡እህቶችህን ፣ሚስቶችህን፣እናቶችህን፣አክስቶችህን በግድ እያነቀ ይደፍራቸዋል ፡፡ድርጊቱ ሁሉ የአህያ ነዉ፡፡ስለዚህ ወንድሞቻችሁ ፣እህቶቻችሁ ፣ እናቶቻችሁ ፣አባቶቻችሁ ፣ልጆቻችሁ በዱር በገደል፣በበረሀና በጫከ በየወንዙና በየሸንተረሩ ይህንን እምነት የለሽ አረመኔ የኢተዮጵያና የኛ የህዝቡ ጠላት ፊት ለፊት ገጥመዉ የቁም ስቅሉን እያሳዩት ይገኛሉ ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ ወንድሞቼ፣እህቶቼ ፣ልጆቼ፣አባቶቼና ፣እናቶቸ ሁላችሁም ስሙኝ የኢትዮጵያ አርበኞች የጣሊያንን ወታደርና ባንዳ ተላላኪን አይቀጡ ቅጣት ቀጥተዉ የተደፈረችዉ ሀገራችንና የተዋረደችዉ ሰንደቅ አላማችን በአደዋ ተራሮች በጠላት እሬሳ ላይ በጀግኖች ልጆቾ ጠንካራ ክንድ አንደተዉለበለበች ሁሉ በድጋሚ በድል እንደምትዉለበለብ አርበኞቻችንም እንደሚያሸንፉ ሀገራችንና እኛም ነጻነታችን እንደሚረጋገጥ አትጠራጡ ፡፡
እንኳንስ ህዝቡ ይቀርና የሀገራችን የዱርና የቤት እንሰሳትም ቢሆኑ ለዚህ እምነት የለሽ ወታደርና መንግስት አይገዙም እናንተም በዚሁ ጸንታችሁ ኑሩ፡፡ ለጣሊን ወታደርና መንግስት እንዳትገዙ ፤፤ከአርበኞች ጎን ተሰልፋችሁ ለህዝባችሁና ለሀገራችሁ ነጻነት ለሃይማኖታችሁና ለእምነታችሁ ስትሉ ተዋጉ፡፡ይህንን ባታደርጉ ከእግዚአብሄር በተሰጠኝ የክህነት ስልጣን ገዝቻችኋለሁ ፡፡ይህንን ግዝት በመጣስ ለጣሊያን በማደር ሀገሩን የከዳ ወገኑን የገደለ ፣ያስገደለ ጥቁር ዉሻ ይዉለድ ኢትዮጵያም እንደ ልጇ አትቁጠረዉ፡፡ በማለት ለኢትዮጵያ ህዝብ እዉነተኛዉን ሀገራዊ ፣ህዝባዊ፣ ሀይማኖተዊ መልእክታቸዉን አስተለለፉ፡፡እርሳቸዉና በዙሪያቸዉ ተሰልፈዉ የነበሩ ከ40ሽሀ ህዝብ በላይ የካቲት 12 ቀን በግፍ በመትረጌስና በታንክ ተጨፈጨፉ ፡፤የጣሊያን ወታደሮችና የባንዳ ተላላኪዎች በደስታ ተንበሸበሹ፡፡ የግፍ ግድያ የተፈጸመባቸዉ ጳጳሱና ሌላዉ ህዝብ የነጻነት ጽዋቸዉን ተጎንጭተዉ በሚሞተዉ ስጋቸዉ የማይሞተዉንና የማይደበዝዘዉን ሰማእትነትና ክብር ተጎናጽፈዉ በስጋቸዉ እረፍትን በነፍሳቸዉ ህይወትን ተቀዳጁ፤፤
የኢትዮጵያ ህዝብም የጳጳሱን መልእክት በመቀበል የጣሊያንን ግፍ አምርረዉ በመቃወም ከአምስት አመት የነጻነት ተግል በኋላ የጣሊያን ወታደርና ባንዳ ተሸነፉ ፡፡ኢትዮጵያና እዝቡ ነጻ ወጡ ፡፡የእትዮጵያ ህዝብም የኢጣሊያን ወታደርና ባንዳ ለሀለተኛ ጊዜ በመቅጣት ለዘላለም አይደፈሬነታቸዉን በድጋሚ በማረጋገጥ የኢትዮጵያን ዳርድነበርና የህዝቡን ክብር ለዘላለም እንዲኖር አስችለዉታል ፡፡ለሀገርና ለህዝብ የሚከፈል ተወዳዳሪ የሌለዉ ክፍያ አጥንትን ከደም ፣ሀይማኖትን ከእምነት ፣ማንነትን በእዉነት ፣ባህልንና ታሪክን ፣ስምንና ክብርን ፣አርአያነትንና በትዉልድ ዉስጥ መኖርን አዋህደዉ የሰጡ ተወራሽ ባለታሪክ አባቶችና እናቶች የነበሩን የባለታሪክ ህዝብ ልጆች ነን፡፡
ታዲያ ጣሊያን ከዚህ ሸንፈት በኋላ ለ3ኛ ጊዜ በቀ ጥታ ወረራ መፈጸምን አልመረጠችም ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያን ከተቻለ ለማጥፋት ካልተቻለ ደግሞ ለማድከም ፣ለመበታተን የረጅም ጊዜ እቀድ በማዉጣት የኢትዮጵያን ደካማ ጎን በመጠቀም ህዝቡን እርስ በርስ በማጋጨት ተጠቃሚ እንደምትሆን እና አላማዋን ማሳካትና ህልሟንም እዉን ማድረግ እንደምትችል አረጋገጠች ፣
ለዚህም የሀገር ወስጥ ባንዳዎችን፣የአረብ ሀገራት የኢትዮጵያ ጠላቶችን በማደራጀት እርዳታና ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን በመስጠት በእጃዙር መጠቀምን መረጠች ፡፡ መጥፋት አለባቸዉ የምትላቸዉን ሶስት ዋናዋና ነገሮችን በስራላይ ለማዋል ወሰነች፡፡
እነርሱም 1ኛየንጉሳዊያን ሰርአት
2ኛየኦርቶዶክስ እምነትና ሀይማኖት
3ኛ የአማራ ህዝብና ቋንቋዉ ናቸዉ፡፡
የኢጣሊያ መንግስት አምርሮ ከሚጠላቸዉና ማየትም ሆነ መስማትም ከማይፈልገዉ አነዱና ዋናዉ የኢትዮጵያን የንጉሳዊያንን ስርአት በመሆኑ ይህንን ጥላቻዉን እዉን ለማድረግ ሰፊ የሆነ የማጥላላት ዘመቻዉን በመክፈት ጥረት አድረጉአል ፡፡በተለይም በዘመኑ የዉጭትምህርት እድል በማገኝት በአሜሪካ ፣በአዉሮፓና በሌሎችም ሀገሮች በትምህርት ላይ ነበሩትን ኢትዮጵያዊያን ወጣት ተማሪዎችን በተለያዩ ጥቅማጥቅምና በሚያማልለዉ የአዉሮፓና የአሜሪካ የዴሞክራሲና የለዉጥ የፕሮፓጋንዳ ቃላቶች እና ፕሮግራሞችን እነዲያነሱና በንጉሳዊያንስርአቱ ላይ እንዲያምጹ በተዘዋዋሪ መንገድ ጥረቷን ስታደርግ ቆይታ ለች ኢትዮጵያዉያን ወጣቶቸበሚኖሩባቸዉ የተለየዩ የአለም ሀገራት የተማሪዎች ህብረት ፣የወጣቶች ህብረት ፣የምሁራን ህብረት ወዘተ ማህበራትን እያቋቋሙ የንጉሱን ሰርአት ይገርሰስ ፣ፊዉዳሊዝም ይዉደም ፣ጭሰኝነት ይብቃ ፣መሬት ላራሹ ፣የወዛደሩ የበላይነት ያብባል፣ ንጉሱ ከሰልጣናቸዉ ወርደዉ ለፍርድ ይቅረቡ፣ ወዘተ የመሳሰሉት ጥያቄዎች ያሰተጋቡ ጀመር ፡፡
እነዚህ ጥያቄዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ወደ ሀገር ቤት ዘልቀዉ በመግባት ገበሬዉን፣ የተማሪዉን የመምህራኑን ፣የወዛደሩን ፣የከተማ ነዋሪዉን፣የወታደሩን፣የሀማኖት መሪዉን፣የወጣቱን ወዘተ ልብ ክፉኛ አማለለዉ፤፤ለዉጥ እያለ በየቦታዉ በመጮህ ድምጹን አሰማ ፡፡ወጣቱ በትምሀርት ቤት፣በኮለጅ ፣በዩኒቨርስቲ የለዉጡን እንቅስቃሴ አቀጣጠለዉ፡፡በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ ክፍለ ሀገራት ፣ወረዳዎች ፣ቀበሌወች መልእክቱ በፍጥነት ተዳረሰ ፡፡
ሁሉም በአንደ ድምጽ ለወጥ አለ፡፡የንጉሱ ስርአትም ተተራመሰ ፡፡መፍትሄ ለማምጣት የሚችል የሀሳብ ፍጭት ጠፋ፡፡ያ ገናና ንጉስም በእድሜ ብዛትና በግትርነት የተሸለ ነገር ለመስራት ፣አቅምም ወኔም፣ብልሀትም አነሳቸዉ፡፡ካቢኔዉም የተሻለ ነገር ከመስራት ይልቅ እንደ ወትሮዉ ሁሉ የንጉሱን ትንፋሽ ይጠባበቅ ጀመር ፡፡ የእርስ በርስ መደማመጥም ጠፋ፡፡ ለመስራትም ሆነ ለመወሰን አቅም አነሰዉ ፣የለወጥ ፈላጊዉ ጩኸት ካቢኔዉን አቅም አሳጣዉ ፡፡የሚረባ ነገር ሳይሰራ ተሸመደመደ የንጉሱና ካቢኔያቸዉ ዉድቀት ዘላለማዊ ሆኖ ተደመደመ፡፡
ለዉጥ የፈለገዉ ህዝብም ምን አይነት ለዉጥ እንደሚፈልግ የአጭር የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅዱን ሳያዘጋጅና የቤት ስራዉን ሳይሰራ ፣ስልጣኑን ሊረከብ የሚችል አካል ሳይቋቋም የለዉጡ መንስኤ የሆኑትን ጥያቄዎች ሰብስብ ባለመልኩ አቅጣጫ ሳይበጅለት ሁሉም በየፊናዉ ለወጥ ለወጥ እያለ ሲንጫጫ ያለምንም ፕሮግራም የንጉሱንስርአት ከስሩ ተገረሰሰ እና ወደቀ፡፡ሀገሪቱም ትልቅ ትርምስ ዉስጥ ገባች ፡፡ ያልታሰበዉና ያልተጠበቀዉ የወታደሩ ክፍል ሀገሪቱን አረጋጋለሁ በሚል ወደ ስልጣኑ ጫፍ ላይ መንጠላጠል ጀመረ፡፡
የስልጣን ሽግግሩ ሰላማዊ መሆን ሲገባዉ /አድርግ አታድርግ በሚለዉ የወታደርሳይንስ አድርግ የሚለዉን ትእዛዝ በመስጠትና በመቀበል ደም እንደዉሀ የፈሰሰበት የሰርአት ለወጥ ተካሄደ ፡፡ንጉሱና ካቢኔያቸዉ ተደመሰሱ ፡፡ጠያቂም ሆነ ተጠያቂ ሳይኖር አድርግ የሚለወ ትእዛዝ አይሎ ያ ሁሉ ምሁራን ሚኒስትሮችንና የካቢኔ አባላት ተደመሰሱ ፡፡ስርአቱም ላይመለስ ግብአተ መሬቱ ተፈጸመ፡፡ኢትዮጵያም ጠበቃዋን አክሊሉ ሀብተወልድን ጭምር አጣች፡፡የኢጣሊያም አቅድ ሙሉበሙሉ ተሳካ፡፡አዋጭ ፕሮጀክትም ማለት ይህ ነዉ፡፡
ኢጣሊ በነደፈችዉ የረጅም ጊዜ እቅድ መጀመሪያ መጥፋት አለበት በማለት በስራ ላይ እንዲዉል ባደረገችዉ የንጉሳዊያንን ስርአት የማጥፋት ዘመቻ እንደ ድሮዉ የቀጥታ ወረራ ሳያስፈልጋት በራሱ በኢትዮጵያ ህዝብ የኢጣሊ መንግስት የቤት ስራ ተጠናቀቀ ፡፡በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የደርግ መንግስት በፈጻሚነት ተግባራዊ ክንዋኔዉን አካሄደ ፡፡
ሁለተኛና በኢጣሊያ መንግስት አስተሰሰብ ትልቅ ችግር ፈጥሮብኛል በሚል ቢቻል እንዲጠፋ ካልተቻለ ደግሞ አንዲዳከምና አንዲበታተን የተፈረደበት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲሆን ነገር ግን እንዲህ በቀ ላሉ የሚሆን አልነበረም ፡፡በህዝብ ሳይመረጥ በጉልበት የህዝብን ስልጣን በመንጠቅ ስልጣን የጨበጠዉ የደርግ መንግስት የኢትዮጵያን ዳር ድንበር በማስከበሩ እና ህዝብ በአንድነት ፣በአኩልነት ከማስተዳደሩ ባሻገር ለኦርቶዶክስ ሃይማኖት የሰጠዉ ግምት ግን እጅግ የሚያስተቸዉና እንዲያዉም ክርስትና ልጆቻችሁን አታስነሱ ፣በአላትንም አታክብሩ ወደ ሚል አስተሳሰብ በማዘንበሉ በእምነቱ ተከታዮች ዘንደ ትልቅ ቅሬታን የፈጠረ እንደነበር የቅርብ ጊዜ እዉነት ነበር፡፡
ከዚህም ባለፈ የስርአቱ መሪዎች ጳጳሳት እስከመግደል የደረሱበት እንደነበር የምናስታውሰው ነው፡፡ይህ ደግሞ በደርግ ባለስልጣናት አእምሮ ውስጥ ብቻ የተጠነሰሰና ተፈጻሚነት ያገኘ አልነበረም፡፡ ኢጣሊ ደርግ በሚመራበት የሶሻሊስት ርዕዮት ዓለም ውስጥ በተዘዋዋሪ መንገድ እጇን በማስገባት የራሷን ሚና እንደምትጫወት ምልከታዎች ነበሩ፡፡ ነገርግን የደርግ መንግስት የጣሊያን አካሄድ በርግጠኝነት እንደማይቀበላት ሰለተረዳችና አዋጭ አለመሆኑን ስለተገነዘበች የተንኮል መረቧን ወደሊላ መስመር መቀየርን መረጠች፡፡
አንደሚታወቀውኢትዮጵያ ዙሪያዋን በአረብ ሀገራት የተከበበች እንደመሆኑ መጠን፡፡ጣሊያንም ፊቷን ወደነዚህ ሀገራት በማዞር የደርግ መንግስት የሚዳከምበትን እና የሚወገድበትን አማራጭ መከተልን መረጠች ፡፡ እነ ኢራቅን፣ኢራንን፣ሊቢያን፣ግብጽን ፣ሱዳንን፣የመንን አና የኤርትራ ሀማሴን እስላሞችን እርዳታ በመስጠት በማባበልና በማግባባት የረጅም ጊዜእቅዷን አውን ለማድረግ ሰራዋን ጀመረች፡፡
ከዚህበኋላ የኤርትራ ሀማሴኖችን በማደራጀት ኢትዮጵያዊነት እና የኦርቶዶከስ ሀይማኖት በእናንተ ላይ በሀይል የጠጫነባችሁ በመሆኑ መታገል ይገባችኋል በማለት አባቶቻቸዉን በባንዳነት እንደተጠቀሙበት ሁሉ ልጆቻቸዉን በማሸፈት ወታደራዊ ሰልጠና ፣ትምህርት ፣ትጥቅ ና ስንቅ በማዘጋጀት በኢራን፣በግብጽ፣በሊብያ ፣ ሶሪያ እና ሱዳን እንዲሰለጥኑ አርዳታዋን ታጎርፍ ነበር፡፡
ከዚያም የከርስትና እምነት ተከታይ የሆነዉን የኤርትራ ክፍለ ሀገር ህዝብ ቀስ በቀስ እየሰረስሩ በመግባት የአማራህዝብ በሀይል የጫነብህን ኢትዮጵያዊነት አሸቀንጥረህ ለመጣል መታገል አለብህ በማለት የማደራጀት ስራወችን በመስራት ልክ እንደ ጀበሀዉ ሁሉ የተለያዩእርዳታዎችን በማበርከት ልጆቹም እንደአባትና አያቶቻቸዉ ለጣሊያን በማደር በኢትዮጵያዊያን ወንድሞቹና እህቶቹ ላይ ጥቃት መፈጸምን ተያያዘዉ ፡፡
ጣሊያን ሁለት ጊዜም ኢትዮጵያን በቅኝግዛት ለመያዝ ወረራ የፈጸመችዉ በኤርትራ በኩል በመሆኑ ዛሬም በልጆቻቸዉና በልጅ ልጆቻቸዉ አማካኝነት የኢትዮጵያን የመበታተኛ መንገድ አልጋ በአልጋ እንዲሆንላችዉ በትግራይ ክፍለ ሀገር ዉስጥም የነበሩትን ባንዳና የባንዳ ዝርያ ያላችዉን ሰዎች ማሰባሰብ ጀመሩ ፡፡ህዋሀት (ወያኔ) የሚል ስም በማወጣት ኢትዮጵያንና የአርቶዶክስ ሀይማኖት ብሎም አማራን የማጥፋት የተቀነባበረ ዘመቻቸዉን እንዲሰምር ሌት ከቀን ኳዋተኑ ፡፡
ሻቢያና ወያኔ በተሰጣችዉ የቤት ስራ የተጣመረ የትግል እንቅስቃሴ በማካሄድ የኤርትራና የትግራይ ክፍለ ሀገሮችን ከሌላዉ የኢትዮጵያ አካል ለመገንጠል በኢጣሊያንና በሌሎችም የአዉሮፓ እና የአረብ ሀገራት አርዳታ ጭምር የትጥቅ ትግል እየተፋፋመ ሄደ፡፡እነዚህ የኤርትራና የትግራይ የባንዳ ልጆች እና፣የልጅ ልጆችለጣሊያን በመገበር ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻቸዉንና እህቶቻችዉን ሲወጉና ሰያሶጉ የነበሩትን ልጆችና የልጅ ለጆችን በማፈላለግ ወደ መሀል ሀገር በሚገቡበት ወቅት ሊያሰቸግራቸዉ የሚችለዉን ሁሉ ለማሶገድ የኦሮሞ ነጻ አዉጭ ናችሁ ፡፡
እናንተ ደግሞ የአማራ ነጻ አዉጭ ናችሁ እያሉ በማበጃጀት ያልተጨቆኑትን አርተፊሻል ነጻ አዉጭዎች በማደራጀት ወደ መሀል ሀገር ተያይዉ አብረዉ ገቡ፡፡በሻቢያ ፣በህወሀት ፣በኢህአዴግና(ብአዴን ፣በኦነግ ስር ) የተሰባሰበት የባንዳ ልጆችና የልጅ ለጆች በጣምራ ሆነዉ አገሬን ብሎ ፣ድንበሬን በሎ ፣ህዝቤን ወገኔን ብሎ ፣ማንነቴን ብሎ ፣ክብሬን ብሎ ለዘመናት ከወራሪ ጋር ታግሎ ፣ወድቆ እርሱም ጥሎ በደምና ባጥንቱ ሀገር አስከብሮና ጠብቆ ያቆየዉን የአማራ ህዝብ እንዲጠፋ ጣሊያን ያቀደችወን እቅድ በስራ ላይ በማዋል ሲጠቀ ምበት የኖረዉን መሬቱን ነጠቁት ፣ከሚሰራበት ከማንኛዉም የመንግሰትና የግል መስሪያ ቤቶች ከስራ አባረሩት ፣ከሚኖርበት ቤት ወሰጥ አሰወጥተዉ ሜዳለይ ጣሉት ፣ከሚኖርበት አካባቢ በመሄድ በጅምላ በጥይት ደበደቡት፣ከነ-ነፍሱ ገደል ሰደዱት ፣በእሳት አቃጠሉት በአሀኑ ሰአትም ከሚኖርበት የኢተዮጵያ ክልል ዉስጥ ሀገርህ አይደለም በማለት ንብረቱንና ሀብቱን ነጥቀዉ በግፍ አባረሩት ፣የሚችሉትን ሁሉ ፈጽመዉበታል ፡፡ ገድለዋል ፣አስረዋል ፣የደረሱበት ጠፍቶአል ፣ጣሊንም በቀጥታ ወረራ የልቻለችዉን የማጥፋት ዘመቻ ፍርፋሮ በምትወረዉርላቸዉ ቅጥረኛች አማካኝነት ያቀደችዉ አቅድ ቀስበቀስ እየሰመረላት ይመስላል፡፡
ጣሊያን በከፈተችዉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖትንና አማራን የማጥፋት ዘመቻ ዉስጥ ኢህአዴግ የሚባለዉ ተላላኪ ቡድን እየተጠቀመበት የነበረዉና አሁንም የሚጠቀምበት ዘዴዉ የሌላዉን እምነትና ቋንቋ ፣ባህል፣ ጨፍልቀዉ አንዲት ሀገር፣አንዲት ሀይማኖት እያሉ በማለት ለ22 አመታት በተከታታይ ባራገበዉ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ እና የእምነቱ ተከታዮች ባልሆኑ ጳጳሳት የሲኖዶሱ መመራት በዋናነት የኦርቶዶክስ ሀይማኖት በከፍተኛ ሊጎዳ ችሎሏ ፡፡እጅግ በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸዉ የእምነቱ ተከታዮች የሌላ እምነት ተከታዮች ለመሆን ተገደዋል፡፡በተቃራኒዉ የሌሎች ሀይማኖቶች በፍጥነት አየተስፋፉ ሄየደዋል ፡፡
የኦርቶዶክስ ሀይማኖትንና አማራዉን በማጣመር አብረዉ ለመምታት እንዲያመቻቸዉ ለቅስቀሳ የሚጠቀሙበት የጥላቻ ፕሮፓጋንዳም እጅግ በጣም የሚያሳፍርና የሌላዉን ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ ሰብአዊ መብት የደፈጠጠነዉ፡፡የኦሮሞዉን ፣የትግሬዉን፣የጉራጌዉን፣የደቡቡን ወዘተ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይነት በመናቅ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ የሆኑት አማራዉ ሁኑ ስላላቸዉ ነዉ በማለት በመብታቸዉ ላይ ቁማር በመቆመር የፈለጉትን እምነት የማምለክ የተፈጥ ሮና ህገ-መንግስታዊ መብታቸዉን በመርገጥ ይላገጥባቸዋል ፡፡ሲፈልገዉም የኦርቶዶክስ ሀይማኖት የነፍጠኛ መወሸቂያ ነዉ በማለት ያጥላላ መስሎት የእምነቱ ባለቤት አማራዉ ብቻ ነዉ ይላል ፡፡የኦርቶዶክስ ሀይማኖት በግድ እያነቀ በባሀር ዉስጥ እየጨመረ ሰዎችን ያጠምቃል በማለት እምነቱን ሲያነቁአሽሽ አንድም የሀይኖቱ መሪዎች ተቃዉሞ ያስሙበት ጊዜ አልነበረም፡፡ ይህ ደግሞ የሚያሳየዉ ሀይማኖቱ በነማን እየተመራ እንደሆነ ነዉ፡፡
በዚህም የተነሳ የእምነቱ ተከታይ ያልሆኑ ሰወች የቤተከርስቲያን አስተዳዳሪና የቅዱስ ነዋያት ሃላፊወች በመሆናቸዉ ቤተከርሰቲያናት የጥላቻ፣ የእርስ በረስ መካሰሻ፣ የሙስና መናኸሪያ ፣የዘረፋ ቦታ ሆነች፡፡ ጥጋብና ቅንቶት ፣እራስ ወዳድነት ተስፋፋ ፣እዉነተኛ የሆኑት የእምነቱ ተከታዮች ተገፍትረዉ ከቤተክርስቲያኒቱ ቅጥር ጊቢ እንዲወጡ ተደረጉ፡፡ ቅዱሰነት፣ታማኝነት ፣እግዚአብሐየርን ፈሪነት፣የተጎዱንና የተበደሉን ፣የተራቡንና የተጠሙን ማሰብን ቀረ፡፡ጠያቂና ተጠያቂ ነት ጠፋ፡፡በሲኖዶሱ፣በቤተከርስቲያኑና ፣በምእመናኑ መካከል አንድነት ጠፋ፡፡ጥላቻ ክፍፍል፣ክህደት፣የግል፣ብልጽግና ነገሰ፡፡በዚህን ጊዜ የጣሊያን እቅድ እዉን ሆነ ማለት ነዉ ፡፡
ሻቢያ ፣ወያኔ፣ኢህዴንና ኦነግ በጋራ በመሆን በጣሊያን የተሰጣቸዉን ባንዳዊ ተልእኮ እዉን ለማድረግ አማራዉን ለማጥፋት የተለያዩ ስሞችን በመስጠት የጥላቻ ዘመቻቸዉን ቀጠሉ፡፡ነፍጠኛ ፣ያለፈዉን፣ስርአት ናፋቂ፣የደርግ ኢሰፓ ቅሪት፣ የደርግ ንክኪ ጨቁዋኝ አማራ ወዘተ በማለት ማብጠልጠሉን ተያያዙት፡፡አማርኛ ቋንቋ መናገር የሚችለዉም ሆነ የማይችለዉ የባንዳ ልጅና የልጅ-ልጅ ሁሉ አፍ መፍቻ ያደረገዉ አማራዉን ነፍጠኛ በማለት ነበር፡፡አማራዉም ይኸንን እንደ ስድብ በመቁጠር አንገቱን በመድፋት ያደምጣቸዉ ጀመር፡፡
ነገር ግን ጠብ-መንጃዉን ወልዉሎ ጀበርናዉን ታጥቆ ጎራዴዉን ታጥቆ፣ ጦሩን ወድሮ፣ ጋሻዉን መክቶ፣ ለህይወቱ ሳይሳሳ ልጄን፣ሚስቴን፣ንብረቴንና ሀብቴን ሳይል ደረቱን ለጦር ፣እግሩን ለአጋምና ለቆንጥር በመስጠት ጠላትን እያርበደበደ የሀገርና የህዝብ ዘበኛ መሆን ያኮራል እንጅ አንገትን አያስደፋም ነበር ፡፡
የሌላ ቋንቋ ተናገሪ የሆኑት ኢትዮጵያዊያን የኛም አባቶችና እናቶች ነፍጥ አንግተዉ ጠላትን ተከላክለዉ ሀገርንና ህዝብን ለማኖር ህይወታቸዉን ፣ አካላቸዉን ንብረታቸዉን ፣ያለምንም መሳሳት ለሌላዉ በህይወት የመኖር እና በሀገሩ እንዲኮራ አድርገዋል፡፡ ነፍጠኛ የሚለዉ ስም ለምን ለአማራዉ ብቻ ተሰጠብን በማለት መከራከር እና አባትና እናቶቻቸዉ የፈጸሙት ተጋድሎ የሚያኮራ እነጅ የሚያሳፍር አይደለም በማለት የባንዳዎችን ተልእኮ ማሳፈር ሲገባቸዉ ፤ እንደባንዳዎቹ ሁሉ እነርሱም አማራዉን ብቸኛዉ ነፍጠኛ በማድረግ የሀገርና የህዝብ ጠባቂ እና የአርበኝነት ስምም እንዲሰጠዉ እናም የጀግንነት ካባዉንም ደርቦ ደራርቦ እንዲጎናጸፍ አስችሎታል፡፡
ሌሎቹ ኢትዮጵያዊያን የአባቶቻቸዉና የእናቶቻቸዉ ተጋደሎና የሀገር ባለዉለታነት የማያኮራቸዉና የማያስመካቸዉ ከሆነ እኛ ኢተዮጵያዊያኑ ግን አያቶቻችን በፈጸሙት አኩሪ ተጋድሎ እጅግ በጣም አድርገን እንኮራለን ፡፡ አንመካለንም፡፡ለሀገርና ለህዝብ ባለዉለታ ከመሆን የበለጠም በምድር ላይ ምንም ነገር የለም ፡፡
ኢሀአዴጎች በጣሊያንና በሌሎችም ሀገራት በተሰጣቸዉ አማራዉን የማጥፋት የቤት ስራ ለመምታት እንዲያመቻቸዉ በተለያዩ ስሞች በመጥራት ጥላቻቸዉን ያራምዳሉ ይኸዉም፤
1ኛ ጨቁዋኝ አማራ
2ኛ ትምክህተኛ አመራ
3ኛ ነፍጠኛ አማራ በማለት የጥላቻ ቅስቀሳቸዉን አራምደዋል ፤
የኢትዮጵያን አንድነትና የህዝቡን ክብር ለማሰጠበቅ ከአንደኛዉ ከፍለ ሀገር ጠላት ወደ መጣበት ከፍለ ሀገር በመዘዋወር ከሌሎች ኢተዮጵያዊያን ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመተባበር የከፈለዉን ዋጋ ከምንም ባለመቁጠር እንዲሁም በባህል ፣በእምነት ፣በቋንቋ ፣በስራ አብሮ የኖረዉን የአማራ ህዝብ ጨቋኝ በማድረግ በወንድሞቹና እህቶቹ እንዲጠላ ያደርጉታል ፡፡ሌላዉ ሲራብ መራቡን ፣ሲጠማ መጠማቱን ፣ሲሞት መሞቱን፣ እዉነቱን በመካድ እናንተን ለመጨቆንና ለመግዛት የመጣነዉ (ሽርጣም እያለ ሲሰድባችሁ የኖረ ነዉ ) እያሉ ጊዜ አገኘን፣ ወራት ገጠመን ፣ ቀን ሞላልን ብለዉ የግፍ አርምጃ ወሰዱበት፡፡ እየወሰዱበትም ነዉ፡፡ይህም የሚሆነዉ በገዛ ሀገሩ ነዉ ፡፡
አንዲት ሀገር፣አንዲት ድንበር፣አንዲት ባንዲራ አንድ ህዝብ በማለት በአርበኝነትና በሀገር ወዳድነት ድንበር ያስከበረዉን ፣ለህዝብ የሞተዉን ጨቋዋኝ በማለት የባንዳ ልጆችንና የልጅ ልጆች የሆኑትን ተጨቁዋኝ በማድረግ የጊዜ ጉዳይ ሆኖ ባንዳ አርበኛን ለማጥፋት ቆርቶ ተነስቷል ፡፡ የአርበኛ ልጆችና የልጅ-ልጆች የአባቶቻቸዉንና የእናቶቻቸዉን ሀገርን የመጠበቅና ህዝብን የማዳን ተጋድሎ በትምክህት እና በኩራት ከመቀበልና እንገታቸዉን ቀና አድርገዉ ከመኖር ይልቅ ማንነትን መካድን ፣ዝቅተኝነትን፣ታሪክን መጥላት ፣ተገዠነትን ፣መለያየትን፣ሀገራዊ ፍቅርን እና ሀገራዊ አንድነትን መሸሽን መርጠዉ ጊዜ የሰጠዉን ባንዳ ከምንም በላይ አግዝፈዉ በመመልከት ለዱላዉ እራሳቸዉን አመቻችተዉ በመስጠት የአባቶቻቸዉ ወኔ ከድቶአቸዉ በተላላኪ ባንዳ ይገደላሉ ፣ይደበደባሉ እንዲሁም ከሀገር ይሰደዳሉ፡፡
የአርበኛ ልጆችና የልጅ-ልጆች አባቶችና እናቶቹ በሰሩትና በፈጸሙትየአርበኝነት ተጋድሎ ከመመካትና ከመኩራት ይልቅ የባንዳዎችን ያላዋቂነት ፕሮፓጋንዳ በየቀኑ በመስማት የአርበኞችን እዉነተኛ ታርክ በመጠራጠር እራሳቸዉን ያዋርዳሉ፡፡ይህ ደግሞማንነትን መካድ ነዉ ፡፡በእኔ እምነት የአያቶቼ ያርበኝነት ተጋድሎ ትምክህቴ በመሆኑ እመካበታለሁ፡፡አላፍርም አንገቴንም አልደፋም ትላንትናም ፣ዛሬም ሆነ ነገም ታሪኩ ትምክህቴነዉ እመካበታለሁ፡፡ እኮራበታለሁ፡፡የሀገር ጠባቂ የጠብመንጃ አንጋች የነፍጠኛ ልጅ በመሆኔ ከፍ ያለ ትምክህትና ኩራት ይሰማኛል ደግሜ ደጋግሜ እኮራበታለሁ፡፡
የሌሎች ቋንቋተናጋሪ ነፍጠኞችን፣ ትምክህተኞችን የማያሰከፋና ታሪክ አልባ የማያደርጋቸዉ ካልሆነ በስተቀር እኔን የነፍጠኛ አማራ ፣የትምከህተኛ አማራ ልጅ ቢሉኝ ባለ ታሪክ ኢትዪጵያዊ መሆኔ በሚጠሉኝ እና በባንዳወች አንደበት ሲመሰከር ትምክህት እንጅ ሀፍረትም ሆነ ዉርደት አይሰማኝም ፡፡የነፍጠኞች የልጅ ልጅ ነኝና ተመካሁ ነገር ግን ጠላቴ ይፈር አንገቱንም ይድፋ ፡፡አንገቴን ቀና አድርጌ እሄዳለሁ እንጅ በአያቶች ማንነት አፍሬ አንገቴን አልደፋም ፡፡ ለሚጠሉኝም ተመቻችቼ የበትራቸዉ ማሳረፊያ አልሆንም ፡፡ የኋለኛዉም ታሪኬ ለወደፊቱ መነሻ ስለሚሆነኝ በሀገር አንድነትና በህዝብ ደሀንነት ላይ አልደራደርም ፡፡ ይህ በደሜዉስጥ የነበረ፣ ያለ፣የሚኖር በመሆኑ በእኔ ዉስጥ ለዘላለም ይኖራል፡፡ምክንያቱም የነፍጠኛ ልጅ ነኝና በሀገርና በህዝብ ጉዳይ ቀልድ የለም፡፡
የጣሊያን ጉዳይ አስፈጻሚ የባንዳ ስብስቦች በሚገርም ሁኔታ አማራዉን ለማጥፋት የጎንደር ፣የጎጃም ፣የወሎ ፣የሸዋ አማራ በማለት እንደሚታረደ ከብት ብልት አያወጡ ተራ በተራ የጥፋት ዘመቻቸዉን እዉን ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ፣የማይጠነስሱት ብቅል፣የማይሸርቡት እና የማይገምዱት የተንኮል ገመድ፣የማያጠምዱት ስማርድና ወጥመድ ፣የማይዘሩት የዘረኝነት መርዝ፣የማያወሩትና የማያሶሩት የዉሸት ታሪክ የለም፡፡
ሲፈልጋቸዉ ጎንደር የሚባለዉን ክፍለ ሀገር ሰሜን ጎንደር እና ደቡብ ጎንደር እያሉ ፣ጎጃም የሚባለዉንም ፣ወሎ ፣ሸዋ ምራብ ጎጃምና ምስራቅ ጎጃም፣ሰሜን እና ደቡብ ወሎ እንዲሁም ሰሜን ሸዋ ፣ምራብ ሸዋ ፣እና ምስራቅ ሸዋ እያሉ አንደኛዉን በሌላኛዉ ላይ የጥላቻ መርዝ እየዘሩ እርስበርስ ያጣሉአቸዋል ፡፡አንድ ቋንቋ ‹አነድ ሀይማኖት ፣አንድ ባህል ፣አንድ መንደር የሚኖረዉን፣በአነድ ማህበራዊ ህይወት ዉስጥ በመኖር በደቦ ፣በለቅሶ ፣በሰርግ ፣በገበያ፣በአድር፣በእቁብ፣በበአል ለምሳሌ በጥቅምት ፣በፋሲካ፣በገና፣በኢዳልፈጥር፣በመዉሊድ ወዘተ አብሮ ለዘመናት የኖረዉን የአማራ ህዝብ ይበታትኑታል፡፡
በተጨማሪም ጎንደርን፣ከጎጃም፣ወሎን ከሸዋ፣እርስበርስ እንዲጣላ ያደርጋሉ ፡፡የአማሮቹን መሬት በመዉሰድ ለትግራይና ለሱዳን ሰጥተዋል ፡፡ አማራዉን ለማጥፋት የመጀመሪያዉ እርምጃም አማራዉን በኢኮኖሚ ማድከም፣ከቦታዉ ማፈናቀል አቅም እንዳይኖረዉ ማድረግ የተዋጣለት የጣሊያን እቅድ ሲሆን ፈጻሚዉ ደግሞ የባንዳዎች ስብስብ ነዉ፡፡ ህዝቡ ስለኢትዮጵያ አንድነት አንዳያስብ ፣ስለነጻነቱ እንዳይወያይ እና ጠላቶቹን በዉል በመለየት እንዳይታገላቸዉ የሌለ ጸብ በመፍጠር ከወንድሞቹና ከእህቶቹ ጋር አጣለተዉታል ፡፡ህዝቡም ጠላቶቹ የዘረጉለትን የማጥፊያ ዘዴ ከመረዳትና ጠላቶቹን በጋራ ከመታገል ይልቅ ይኸንን የዉሸት ጸብ እዉነት አድርጎ በመቀበል ለ22 አመታት እርስ በርሱ በመደባደብ የጎሪጥ በመተያየት ለጠላቶቹ በመመቸት ለዱላዉ ጀርባዉን አመቻችቶ በመስጠት እራሱን የችግሩ ሰለባ አድርጎ አመታትን አስቆጥሯል፡፡
ሌላኛዉ የማዳከሚያ ዘዴ ደገሞ የእነርሱ አባል ሆኖ የባንዳነት ተግባር ለመፈጸም ለሚችሉት የሌላዉን መሬት በመንጠቅ ይሰጡታል ፡፡ለጊዜዉ ባንዳዉም የወንድሙን መሬት ነጥቀዉ ሲሰጡት በደስታ ይቀበላል፡፡ነገር ግን በስተመጨረሻ ብቻወን እንደሚያገኙትና እርሱንም በተራዉ እንደሚበሉት አለመረዳቱ የእዉነተኛ ባንዳ ሆዱ ከህሌናዉ እንደሚበልጥበት ያሳያል፡፡
የእነርሱ አባል ያልሆነወንና የባንዳነት ተግባር አልፈጽምም ያለዉን ከማዳበሪያ ፣ከአረም ማጥፊያ ፣ከተባይ ማጥፊያ ፣ይከለክሉታል፡፡ነጋዴዉን የንግድ ፈቃድ አዉጣ ይሉታል ፡፡የንግድ ፍቃድ አዉጥቶ ሲነግድ በአንድ የንግድ ፈቃድ ተመሳሳይ ነገሮችን መግዛትም ሆነ መሸጥ አትችልም በማለት ፍቃዱን ይነጥቁታል፡፡የሚሸጠዉና የሚገዛዉ እቃ ምን እንደሆነ ሳይታወቅ የቀን፣የሳምንት፣የወርና የአመት ገቢዉ በሂሳብ ሳይሰላ የግምት ግብር ገብር ይሉታል ፡፡
እቃ በረከሰ ጊዜ ገዝቶ በእቃ ገምጃ ቤቱ ዉስጥ በማስቀመጡ በተወደደ ጊዜ ነገዴ እንደመሆኑ መጠን እሸጠዋለሁ ብሎ ያሰቅመጠዉን ንብረቱን እንደ ሌባ በመቁጠር የቤቱን በር ሰብረዉ በመግባት ንብረቱን ይቀሙታል ፡፡በሕግ ሽፋን ስም በጠራራ ጸሀይ የዘረፋ ተግባር ይፋጽሙበታል ፡፡በሌላ መልኩ ነጻ የገበያ ስርአት ስለዘረጋንልህ እንደ ፈለገህ የመሸጥና የመግዛት መብትህን አረጋግጠንልሀል ይሉታል፡፡
በሌላ መልኩ ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሸማቾች ማህበር በየመንደሩ አቋቁመንልሀል እያሉ በሀሰት ፕሮፓጋንዳ ያማልሉታል ፡፡ ነገር ግን ህብረተሰቡ የተባለዉን ነገር ለማገኘት ወደ ሸማቾች ሲሄድ አያገኘዉም፡፡ በየቀበሌዉ ፣በየክፍለ ከተማዉ በተሰገሰጉት እና በሙስና ቅብብሎሽ በሰለጠኑት ካድሬዎች እቃዉ በተባለዉ ቦታ እና ሱቅ ሳይደርስ በአየር ላይ ይሸጣል ፡፡ለህዝብ ዴንታ ቢስ የሆነ ስርአት ባይሆን ኖሮ በትክክል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረገ የገበያ ማእከል ቢኖር እንደሚባለዉ ህዝቡ በስግብግብ ነጋዴዎች ይበዘበዝ ነበር ፡፤ ነጋዴዉስ ቢሆን ገዠ ከሌላዉ ዋጋ በመጨመር ይሸጥ ነበር ፡፡ በእቃ ግምጃ ቤታቸዉ ዉስጥስ ያስቀምጡ ነበር ፡፡በገንዘባቸዉ ገዝተዉ ባስቀመጡት ንብረታቸዉስ ሌባ ተብለዉ ይዘረፉ ነበር፡፡ ይህ የሚያሳየዉ የስርአቱ አራማጆች ሊጎዱ የፈለጉትን የሚያጠቁበት ህጋዊ ልባስ ያለዉ የጥቃት በትር ነዉ፡፡
በሚያስገርም ሁኔታ ማንኛዉም ነጋዴ የሽያጭና የግዠ መመዝገቢያ ማሽን በግድ እንዲገዛ አድርገዉታል ፡፡ግዥዉን እንኳን ከፈለገዉ ቦታ እንዳይገዛ ሻጮቹ እንርሱና የእነርሱ አጨብጫቢዎች ናቸዉ ፡፡ ነጋዴዉ በግድ እንዲገዛ በተገደደዉ የሽያጭ ማሽን የአመት የሽያጭ ሂሳቡን በሂሳብ ባለሙያ ሰራተኞች አሰርቶ ግብር ለመክፈል ገንዘብ ይዞ ወደ ግብር ተቀባዮች ቢሮ ሲሄድ ከሳይንስ ዉጭ እናንተ አካባቢ ያላችሁትን ግብር የምንቀበላችሁ በሂሳብ ሰራተኛ የተሰራዉን የግብር መጠን ሳይሆን ቢሮዉ በወሰነዉ የግምት ግብር ክፍያ እንድትከፍሉ ታዛችኋል ተብለዉ ይገደዳሉ፡፡ ይህ የሚያሳየዉ እንዳይነግዱ የተፈለጉ ሰዎች ስላሉና ቦታዉን ወይም ሱቁን አስለቅቀዉ ለካድሬና ለታላላኪ ለመስጠት የሚደረግ ሴራ ነዉ፡፡
ሻቢያ ፣ህዋሀት፣ኦነግ፣አሁን ደግሞ ኢሀአዴግ የሚባለዉ ቡድኖች ባለፉት አርባ አመታት በጫካና በስልጣን ላይ ባደረጉአቸዉ አማራን የማጠፋት ዘመቻወች እጅግ በጣም ብዙ ሃሳቦችን፣ዉሳኔዎችን፣እቅዶችን፣የስራ ክንዉኖች፣እንደ ፈጸሙ ፣እንዳስፈጸሙ አብሮአቸዉም የተሰለፈዉም አማራ ከእነርሱ ጋር ያልተሰለፈዉም አማራ በተቃዋሚነት የተሰለፈዉም አማራ የእነዝህን ሰዎች አሰላለፍ አላወቀም ፣አልገባዉም ፣አልተረዳዉም ፣ምንም ግንዛቤ አልወሰደም በማለት እራሴን አላታልልም ፡፡
ነገር ግን የተወሰነዉ ግሩፕ በሀሰቱና መሰረት በሌለዉ የባንዳዎች ጩኸት ተደናብሮ የአባቶቹንና የእናቶቹን ታሪክ እና ማንነት በመካድ የባንዳዎች ባንዳ ለመሆን ከወንድሞቹና ክእህቶቹ ላይ እየነጠቁ በሚሰጡት ጥቅም ዐይኑ ታዉሮ አእምሮዉ ታዉኮ በወገኖቹ ላይ ሰይፉን መዝዞአል ፡፡
ሌላዉ ምን ያገባኛል በማለት አንገቱን በመድፋት የወገኖቹ መጎዳት ፣መሞት ፣መሰደድ ፣መታሰር ፣መገረፍ ምንም አልመስልህ ብሎት እጅና እግሩን አጣጥፎ የእርሱን ወር ተራ በመጠባባቅ ላይ ይገኛል ፡፡
ሌሎቹ የስልጣን ተጋሪ የሆኑ መስሎአቸዉ በስርአቱ ዉሰጥ በመንቦራጨቅ በሀገርና በህዝብ ላይ ታሪካዊ የስህተት ዉሳኔወችን ይወስናሉ ፡፡ጊዜ የማይለወጥ መስሎአቸዉ ወስነዋል፣ እየወሰኑም ነዉ፡፡ነገር ግን የእንጨት ጉልቻ ነዉና ነገሩ ትንሽ ወጣ ሲሉ ወጥመዱ እነርሱንም እያነቀ ወደ ጉረኖ ይታጎራሉ ፡፡ሌሎቹ ደግሞ ኢሀአዴግ በቀደደዉ ቦይ በመፍሰስ የሸዋ፣የወሎ፣የጎንደር.፣የጎጃም አማራ በመባባል ቡድን በመለየት እርስ በራሱ ሲነታረክ ይስተዋላል ፡፡ከዚህ የበለጠስ ወራዳነትስ ምን ሊመጣ ይችላል ፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቤንች ማጅ ዞን ከ78 ሽህ በላይ አማሮች እንዲባረሩ ሲወሰን ይህ አማራን የማጥፋት ዘመቻ አይደለሞይ ተብሎ የተጠየቀዉ የስርአቱ ቁንጮ አቶ መለስ ዜናዊ መልስ ሲሰጥ ቤንች ማጅ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የዞኑም ፣ የወረዳዉም ፣የቀበሌዉም፣ አሰተዳዳሪወች ፣ ሀላፊወች የምስራቅ ጎጃም አማሮች ናቸዉ ነበር ያለዉ፡፡ ለመባረር ያበቃችዉ ወንጀል ደግሞ አማራነት ብቻ መሆኑ ነዉ ፡፡
አእምሮ ላለዉ ሰዉ በሀገር ቤትም ሆነ በዉጭ ሀገር ለሚኖረዉ አማራ ከዚህ የበለጠ በማንነቱ ላይ ያነጣጠረ የጥቃት እርምጃ አመላካች እንደሆነ ከዚህ የበለጠ ማስረጃ ሊኖር የሚችል አይመስለኝም፡፡ከዚህ በላይ አማራን ለማጥፋት ሌላ ማስረጃም ሆነ አማራ ነኝ ለሚለዉም ሁሉ እኔ ማነኝ ብሎ እራሱን በመጠየ ቅ የመሰባሰቢያዉና የእርስ በርስ ዉይይት የሚደረግበት ጊዜዉ የቀረበ መሆኑን ሲያበስር ነገ ይህ ዘመቻ ወዴት ሊመጣና ሊሄድ እንደሚችል ቁልጭ ያለ ማስረጃ መሆኑን ልብ ያለዉ ልብ ይበል ፡፡
ለሀገርና ለወገን የማይሆን ጉልበት ፣እዉቀትም ፣ሆነ ገንዘብ ምን ሊፈይድ አንደሚችል አለመረዳትም ጤና የሚነሳ ህመም ይሆናል አንጅ ፋይዳ ይኖረዋል ብየ አላስብም ፡፡ለዚህ ማሳያዉ ደግሞ እየተለቀሙ ወደእስር ቤት የሚወረወሩት ባለሀብቶች እነማን እንደሆኑና ከማን ጋር ሆነዉ የማንን መሬትና ሀብት ሲዘርፉና ሲያዘርፉ እንደነበር፡፡ ነገርግን እነርሱ ያመኑበት ገንዘብ ማግኘታቸዉን ብቻ ነበር አማራነታቸዉ በስርአቱ የማይፈለግና ችግር እንደሚሆንባቸዉ አልተረዱም ገንዘብ በማግኘታቸዉ አሁን የት እንዳሉ የቅርብ ጊዜዉን መመልከቱ በቂ ነዉ፡፡
የአንደኛዉን አማራ መሬቱን ፣የሚኖርበትን ቤቱን፣የሚሰራበትን መስሪያ ቤቱን፣የንግድ ስራዉንና ቦታዉን ነጥቆ ለሌላኛዉ ሲሰጠዉ ተሸቀዳድሞ መቀበሉ (ዶሮን ሲያታልሎት በመጫኛ ጣሎት) ወይም ( የእንቁጣጣሽ በግ ስትታረድ የ መስሏ በግ ትስቃለች ) እንደተባለዉ ተራዉ እስከሚደርስዉ ድረስ የወንድሙ የሆነዉን ሁሉ ሲሰጡት አየተቀበለ በወንድሙ እና ቤተሰቡ ላይ በሚደርሰዉ ችግር ከመጸጸት ይልቅ ከጠላቱ ጋር በማበር በወንድሙ ጉዳት ይሳለቅበታል፡፡
በሌላ መልኩ በተለያዩ ከተሞች ከ50 አመት በላይ የኖረበትን ቤቱን በግድ ዉጣ ተብሎ ከነ-ንብረቱ በዶዘር ተጨፍልቆ የተወሰደዉን ቦታዉን ወንድሙ ከነ–ቤተሰቡ ሜዳ ላይ ሲወድቅ በአዉሮፓና በአሜሪካ ኖርኩ የሚለዉ ኢትዮጵያ ዊ በወድ ዋጋ ከስርአቱ ባለስልጣኖች ተሸቀዳድሞ በመግዛት በወንድሙ ቁስል ላይ ይሳለቃል፤፤
የእርሱ ቢጤ ደንታ ቢስ የአማራ ባለሀብቶች እየተለቀሙ ወህኒ ቤቱን ሲያጣብቡት ነገ የእርሱ ፎቅና የንግድ ተቆማት እንደሚነጠቅ እንኳን ለሰከንድ ቆም ብሎ ማሰብ አልቻለም ፡፡ለማስረጃነትም የእስታር ቢዝነስስ፣ባለቤቶችና ንበረታቸዉ፣የሀያት መኖሪያ ቤቶች ድርጅትና ባለቤቱ ፣ኬኬ የተወሰነ የግል ድርጅትና ባለቤቱ ፣የኢንተር ኮንትኔታል ሆቴል እና ባለቤቱ የት እንዳሉና ተረኛቹ እነማን እንደሆኑ በማስረጃነት ማቅረብ ይቻላል፡፡
በእኔ እምነት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሚደረግን የእርስ በርስ መጎተት ወደጎን በመተዉ ወይም የዲግሪ ሰርተፊኬት በማንጠልጠል፣ወይም ብዙ ገንዘብ አለኝ በማለት መመጻደቅ የትም የሚያደርስ ባለመሆኑ የጋራ ጠላትን በጋራ ለመታገል ከምን ጊዜዉም በላይ መነጋገር ፣መወያየት ፣የአጭር ፣የመካከለኛና የረጅም ጊዜ እቅድ እያወጡ ህዝብንና ሀገርን መታደጊያዉ ጊዜዉ ፣መሆኑን ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡
በአማራ ህዝብ ላይ የተቃጣዉን የጥፋት ሰይፍ ወደሰገባዉ እንዲመለስ ማድረግ የሚቻለዉ አማራ የሆነዉ ህዝብ አያቶቹ በፈጸሙት አኩሪ ታሪክ በመመካት አወን ትምክተኛ ነኝ እመካለሁ በማለት በኩራት አንገቱን ቀና በማድረግ በኢትዮጵያዊነት ጉዳይ ላይ የማይደራደር መሆኑን በኢትዮጵያ ጠላቶች ፊት ለፈት መናገር ሲችል ብቻ ነዉ፡፡
ጠላቶቹ ጊዜ አገኘን ብለወ በሸረቡት ተንኮልና በተሰጣቸዉ የቤት ሰራ ማንነቱን ለማጥፋት ነፍጠኛ በማለት ከተወሰኑ ባንዳና የባንዳ የልጅ- ልጆች በስተቀር ጠብ–መንጃ (ነፍጥ) አንግተዉ ህዝብንና ሀገርን ጠብቀዉ ለትዉለድ ያስተላለፉትን አርበኛ አባቶችና እናቶችን ታሪክ ጠቅልለዉ ለአማራዉ በመስጠት (ኘፍጠኛ) ሀገር የጠበቅህ ህዝብን በማንነቱ እንዲኮራ ያደረግህ ያርበኛ ልጅና የልጅ ልጅ ነህ ብለዉ ሲመሰክሩልን እሰይ አበጀሁ ለካንስ ከትዉልድ ትዉልድ የሚወራረስ ታርክ ያለኝ የባለታሪክ ሰዉ ልጅ ነኝ ፡፡በማለት ትምከህተኛ ለሚሉኝ ሁሉ አዎ እመካለሁ ፡፡ ኢትዮጵያዊ ነፈጠኛ የሀገር ጠባቂ ልጅ እና የልጅ ልጅ በመሆኔ እኮራለሁ እያልኩ እናገራለሁ እንጅ እንገቴን አልደፋም፣አላኮርፍምም፣አላፍርምም፡፡
የአማራ ምሁራን ይልቅስ በአጉል ይሉኝታ ተሸብበዉ ከገሀዱ የእዉነት አለም ተሸሽገዉ ከመኖር የማይነጥፈዉን ብእራቸዉን ከወረቀት ጋር በማገናኘት የባንዳዎችን ሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ በአዉነት በመቀልበስ እዉነተኛዉን ሊነገር የሚገባዉን አያቶቻቸዉ ለሀገርና ለህዝብ የከፈሉትን ታሪክ መናገር ይኖርባቸዋል ፡፡ለተተኪዉ ትዉለድ ም ከዉሸቱ ባሻገር ለንጽጽር የሚሆን እዉነተኛ ታሪክ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡ይህ ካልሆነ አዲሱ ትዉልድየሚሰማዉ፣የሚያየዉ ፣የሚነገረዉ፣የሚያነበዉ ፣በአጠቃላይም እየጨበጠ ያለዉ እዉቀት ከባንዳዎች የሚንቆረቆርን አርበኝነትን፣ሀገር ወዳድነትን፣የባንዲራ ክብርን ማዋረድን፣ድንበር ማስከበርን በማስጠላት በባንዳዎች ታሪክ መቀየርን ስለሆነ ምሁራን ብዕራቸዉን በማንሳት ለትዉልዱም ሆነ ለባንዳወች አማረጭን ማቅረብ የአትዮጵያነት ግዴታ አለባቸዉና ዝምታዉን በመስበር ፊት ለፊት መጋፈጥ አለባቸዉ ብየ አምናለሑ፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘራቸዉን፣ቋንቋቸዉን ፣መንደራቸዉን ፣ወንዛቸዉን ፣ሀይማኖታቸዉን ፣ጾታቸዉን ፣ሳይሉ ለአንድ ሀገር ፣ለአንድ ድንበር ፣ለአንዲት ባንዲራ ፣ለአንድ ህዝብ ነፍጥ (ጠብመንጃ) ጦር፣ጎራዴ ፣ጋሻቸዉን ፣መጥረቢያቸዉን ፣ዱላቸዉን አንስተዉ ጥለዉ ወድቀዉ ኢትዮጵያ የምትባለዋን ሀገር አሰረክበዉናል ፡፡ በዚህ ደግሞ የአሁኖቹ ትዉልዶች የምንኮራበት ሀገር በመኖሩ እድለኞች ነን ማለት ነዉ፡፡ ነገር ግን ይህንን የሚያስመካ ፣የሚያኮራ ከዘመናት ወደ ዘመናት ሲሸጋገር የሚኖር ታሪክ ነፍጠኛ ፣ትምክህተኛ ፣በማለት ለአማራዉ ብቻ የሚሰጡት ከሆነ እና ሌሎቹ የሚቃዉሙ ካልሆነ አማራ ነን ለሚሉት እና አንገታቸዉን ደፍተዉ ለተቀመጡት የምላቸዉ ነገር ቢኖር የሀገር ጠባቂ ልጅ ነፍጠኛ ፣ የድንበር አሰጠባቂ ልጅ ነፍጠኛ ፣ለትዉልድ የሚተላለፍ ባለታሪክ ልጅ ትምክህተኛ፣ ወዘተ ለሚሉኝ ሁሉ የምላቸዉ አዎን ነኝ ፡፡ ከዚህም በላይ ሊገልጸዉ የሚችል ቃላት ካለም በመጨመር መሆኔን እገልጽላቸዋለሁ ፡፡ ኮራሁ፣ተመካሁ፣ ነፍጠኝነት ኢትዮጵያዊነት ድንበር አሰከባሪነት ፣ባንዲራ አክባሪነት ፣ህዝብን አክባሪነት ነዉ እላቸዋለሁ፡፡
አመሰግናለሁ
ከተሪክ መዝገቡ ነኝ
Leave a Reply
You must be logged in to post a comment.