ሰአሊ መዝገቡ ተሰማ

 

የሰአሊ መዝገቡ ተሰማ ስራወች  

 

የመዝገቡ ተሰማን እጅግ ምርጥ ስራዎች ይመልከቱ:: መሳጭ ነዉ:: አመራማሪ ነዉ:: የስነ – ጥበብ ሀይልንም ገላጭ ነዉ::

በሸንቁጥ ዓየለ

መዝገቡ ተሰማ በቅርቡ “ንግስ” የሚል የስዕል ኤግዚቢሽን በብሄራዊ ሙዚዬም አዘጋጅቶ ነበር:: የመዝገቡ ተሰማን ስዕል የተመለከትኩት አንድ ወዳጄ ቀድሞ ገብቶ በመዝገቡ ስራዎች በእጅጉ ስለተመሰጠ ደዉሎልኝ ነበር:: እናም ገብቼ ማዬት እንዳለብኝ ስሜቱን አጋራኝ::

ሆኖም ከአንድ ሳምንት ብሁዋላ የስዕል ኤግዚብሽኑን ግብቼ ተመልክቼ እንደሆነ ሲጠይቀኝ አለመግባቴን ስነግረዉ እንደገና አበክሮ ግብቼ ማዬት እንዳለብኝ አሳሰበኝ:: መቼም ይህ ወዳጄ በቀላሉ አድናቆቱን ለማይረባ ነገር የሚሰጥ እንዳልሆነ አዉቃለሁ:: ደግሞም ነገሮችን በአስተዉሎትና በጥልቀት እንደሚመራምራቸዉም አዉቃለሁ:: እናም የስዕል ኤግዚቢሽኑን ገብቼ ላይ ወሰንሁ::

የስዕል ኤግዚቢሽኑን ገብቼ ስመለከተዉ ስሜትን ጭምድደዉ የሚይዙ: ሀሳብን የሚሰርቁ የሚያመራምሩ እና እጅግ መሳጭ የሆኑ ስዕሎችን ተመለከትሁ:: መቼም የዚህ አርቲስት ችሎታ ነብሴን ሰርቆብኛልና ለሁለተኛ ጊዜ በርካታ ጉዋደኞቼን ሰብስቤ ተመለከትኩት:: በዬስዕሉም ላይ የሀሳብ ልዉዉጥ አደረግንበት:: መቼም ግሩም ድንቅ ነዉ ከማለት የዘለለ ቃላት ብፈልግም አጣሁ::

አንዱ ስዕል ለተለያዩ ሰዎች የሚያስተላልፈዉ ትርጉም እግጅ አስገራሚና አስደማሚ ነበር:: በስልዕል ኤግዚብሽኑ ላያ የተሳተፉ ሰዎችን አስተያዬት አደምጥም ነበር:: ተመልካቹ ሁሉ እጅግ ተመስጦ ነበር:: ደግሞም እንደገባዉ ሁሉም በተደሞና ባግራሞት ይመራመር ነበር:: አንዳንዱም ይከራከር ነበር:: ሁሉም ሰዉ ግን በጣም ተመስጦና አድናቆት ዉጦት ነበር::

እራሴን አንድ ጥያቄ ጠይቄ ወዲያዉ ከአዕምሮዬ ሰረዝኩት:: መቼም የመንግስት ሚዲያዎች ባህሪና አሰራር የታወቀ ነዉ:: ቢያንስ ግን የግል ሚዲያዎች ይህን ታምረኛ አርቲስት ለምን በስፋት ለማህበረሰቡ ሳያስተዋዉቁት ቀሩ የሚል ጥያቄ ያነሳዉን ህሊናዬን “አታቅም እንዴ የግሎቹም እኮ የንግድ ስራ ጉዳይ ያባክናቸዋል::ትኩረታቸዉ የሚከፍሉዋቸዉ ላይ ነዉ እንጅ ባለ ችሎታዎች ላይ አይደለም::” የሚል መልስ ሰጥቼዉ ሁለተኛ ይሄን ሀሳብ እንዳያነሳብኝ አዕምሮዬን አሳሰብኩት:: ቢሆንም አዕምሮዬ እንደልማዱ አሁንም አሁንም ይጠይቃል:: ያገር እሴት በግለሰብ ጥያቄ የሚመለሰብት ጊዜ አለ:: የማይመለስበት ጊዜም አለ::

ምናለበት የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ወርቁን ወርቅ : እንቁዉን እንቁ እያሉ ችሎታ ያላቸዉን ኢትዮጵያዉያን ከዬስርቻዉ እየፈለፈሉ ለብዙሃኑ ህዝብ ማቅረብ ቢለምዱ? አይ የእኔ ነገር አሁንም ደግሞ እጠይቃለሁ እኮ::

እናም የስዕል ኤግዚቢ ሽኑን እያስተዋልኩ እርካታ ነገሮች አንሰላስል ነበር:: የሰዉ አዕምሮ ባንድ ጊዜ ስንቱን ነገር እንደሚያስብ ይገርማል:: በመጨርሻም አስተያዬት ልሰጥ ወደ አስተያዬት መስጫዉ አመራሁ::

ለዚህ አይነቱ ምጡቅ ችሎታ ላለዉ አርቲስት ለምንድን ነዉ “የአለም ሎሬት” የሚል ስያሜ ያልተሰጥዉ ስል ጠዬቅሁ:: ቀድሞዉንስ ማን የሚዲያ እድል ሰጥቶት? ማንስ ወደ ህዝብና ወደ አለም ማህበርሰብ አቅርቦት? ኢትዮጵያዉያንም ሆኑ የአለም ማህበረስብ ሊያዉቀዉና ስራዎችን በአንክሮ ሊያስተዉልለት የሚችለዉ የሚዲያ ሽፋን ሲያገኝ ነዉ::

ደግሞም ይሄ ጥያቄ አሁንም ይፈትነኛል:: ስራዎቹን በደን ለምትመረምሩ ሰዎች ይህ ጥያቄ የእናንተም ጥያቄ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም:: ሚዲያ ወደ ማህበርሰቡ የዚህን ሰዉ ስራ አውጥቶት ቢሆን ኖሮ ይህ ሰዉ ሎሬት ይባል ነበር:: እኔ በግሌ ግን በአስተያዬት መስጫዉ ላይ ያለኝን አስተያዬት ሳሰፍር “ይህ ሰዉ የአለም ሎሬት ነዉ” የሚለዉ ሀሳቤን በርጝጠኝነት ሳኖር ደስ አለኝ:: እናም መዝገቡ እኔ በግሌ የአለም ሎሬት ብየሃለሁ ስል በአስተያዬት መስጫው ላይ የግል እይታዬን አስፍሬ ወጣሁ::

የዚህን ምርጥ አርቲስት ስራዎች ከሚከተለዉ ዌብ ሳይት ዉስጥ ገብታችሁ ተመልከቱት:: ደጋግማችዉ ካስተዋላችሁ ብሁዋላ እናንተም ይህ ሰዉ ያለም ሎሬት መባል አለበት እንደምትሉ አልጠራጠርም:: ደግሞም አንድ ቀን ይባል ይሆናል:: ያኔም ኢትዮጵያም አብራ ትባላለች:: ከእያንዳንዱ ዜጋ ታላቅነት ጋር አገር አብራ ትልቅ ትሆናለች::

የሰአሊ መዝገቡ Work of mezgebuተሰማ ስራወች 

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.