ገዢው ወያኔ ነው ፤ ወያኔም ትግሬ ነው !

ገዢው ወያኔ ነው ፤ ወያኔም ትግሬ ነው !
ምናልባት በቅርቡ ሕግና ስርአት ተለውጧል መሰለኝ ፤ ቀድሞ የማውቀውንም ሰው እንኳን በሥሙ ለመጥራት እያስፈራኝ መጥቷል ። እድሜ ዘልዛላው በስተመጨረሻው ላይ ምኑን ያሰማኝ ጀመር ? አዬ ጊዜ ! የፈሪዎችና ያድር ባዮች ዘመን ላይ ይጣለኝ ? ያሳዝናል ፤ ቢከፋም ቢለማም ሀሰትን ተገን አድርጎ ከመጠለል ይልቅ ፤ እውነትን ተገን አድርጎ መጠለሉ ማንን ገደለ ? ልብ የሚያምነውን አፍ ሲክደው መመልከቱ ! ግሩም ነው ፤ አንድ ሰው በገዛ አይምሮው ውስጥ ሁለት የማይጣጣሙ ተፃራሪ ነገሮችን ይዞ ሲጓዝና ሲያስተናግዳቸው መመልከቱ እጹብ ድንቅ የሚያሰኝ ነው ።
በቅርቡ አንድ የውይይት መድረክ ውስጥ ገብቼ ሳደምጥ ሥምን በተመለከተ ጉዳይ ትልቅ ውዝግብ ውስጥ ገብተው በማስተዋሌ ነገሩን እስኪቋጩ ላድምጥ ብዬ ረዘም ላለ ሰዓት ተቀምጬ ሳደምጥ ቆየሁ ፤ ሆኖም ግን ያወዛገባቸው ርዕስ ሳይቋጭ ላለመስማማት የተስማሙ ይመስል ሁሉም እንደየ እምነታቸው እንደሚቀጥሉበት በማስረገጥ የጋራ የሆነ አቋም ላይ ሳይደረስ መድረኩ ተዘጋ እኔም ወደጉዳዬ ሄድኩ ።
የርዕሱ አነጋጋሪ ዋና ምክንያት የነበረው አሁን ኢትዮጵያን እያመሰ ያለው የወያኔ አገዛዝ “የትግሬ” መንግሥት” ነው ብሎ መጥራቱንና አለመጥራቱን በተመለከተ ነበር ።
እኔም በመድረኩ ላይ ባድማጭነት እንጂ በተሳታፊነት አልታደምኩም ነበርና ፤ ይሄው እኔም እምነቴና አቋሜ ይታወቅልኝ ዘንድ ይህንን ጽሑፍ ለማቅረብ ተገድጃለሁ ።
በመሰረቱ ይህ የውይይት መድረክ ለምን ይህን ርዕስ እንደመረጠና እንዴትስ ሊያወዛግባቸው እንደቻለ ባይገባኝም በኔ እምነት ግን ዛሬ ኢትዮጵያን እየገዛና አፈር ድሜ እያስጋጠ ያለው “የትግሬ መንግሥት” ነው ። ስለሆነም ትላንትም ፤ ዛሬም ሆነ ነገ ፤ ይህ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ጫንቃ ላይ እስካልተወገደ ድረስ ሁሌም የምጠራው “የትግሬ መንግሥት” ብዬ ነው ።
በቀላል አማርኛ ወያኔ ትግሬ ነው ፤ ትግሬም ኢትዮጵያን እየመዘበረና እየገዛ ነው ፤ ትግሬ ግን ወያኔ አይደለም ፤ (ሕዝቡ ወያኔ ሳይሆን ከሕዝቡ የተወለዱትና የወጡት ዛሬ አገራችንን እያመሷት ያሉት ግን ወያኔውች ናቸው )እውነታው ይህ ነው ። ይህ አገላለጽ ያልገባው ካለ አዝናለሁ ፤ ከዚህ በተሻለ ቋንቋ መግለጽ አልችልምና መቼስ ማልጎደኒ ፤ ያቅሜን ሞክሪያለሁ ።
እዚህ ላይ ግን አንድ ነገር ላስገነዝብ እወዳለሁ “የትግሬ መንግሥት” ብዬ ስጠራው ጥሪዬና ስያሜዬ ገዢውን እንጂ ሕዝቡን እንዳልሆነ ላሰምርበት እወዳለሁ ። የትግሬ ሕዝብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወገኖቹ ከአብራኩ በወጡ ልጆቹ እየተገዛ ሳለ በሥሙ ይነገዳል ። አራትና አምስት ሚሊዮን የሚሆነው የትግሬ ሕዝብ መንግሥት ሊሆን አይችልምም ፤ አይደልምምና ።
ሌላው የሚያምታታው ነገር ቢኖር “የትግሬ መንግሥት” ብዬ የምጠራውንና “የትግሬ ሕዝብ የሥርአቱ ተጠቃሚ ነው” የሚለው ጉዳይ ስለሆነ ፤ እዚህ ላይ የማቀርበው ስለ ትግሬ መንግስት እንጂ ፤ የትግሬ ሕዝብ ከስርአቱ ስላገኘው ጥቅም አይደለምና በቅድሚያ የተነሳሁበትን ርዕሴን አጢኑልኝ ። የትግሬ ሕዝብ በስርአቱ ተጠቃሚ ነው ፤ አይደለም ፤ የሚለው ጉዳይ እራሱን የቻለና በራሱ ሰፊ ትንታኔ ሊሰጠው የሚገባ ስለሆነ ከተነሳሁበት አርእስት ጋር እንዳታምታቱብኝ በቅድሚያ አሳስባለሁ ።
በመሰረቱ ያለፉትን ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ መንግሥታዊ ስርአቶችን ብንቃኝ ፤ ብዙ ጊዜ የሚነሱትና የሚጠቀሱት ከአፄ ምኒሊክ እስከ ደርግ ዘመነ መንግሥት ያሉት አስተዳደሮች ናቸው ። ዛሬ እንደምሰማው ባንዳንድ ደካሞች የተዛባ አጠራር “የአማራው መንግሥት” እየተባሉ የሚጠሩት
ማለት ነው ፤ ይህ ስያሜ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ እይታ ተቀባይነት ባይኖረውም ፤ ነገር ግን ለኢትዮጵያ አገራችን መልካም ምኞት በሌላቸው እንደ ኦነግ ፤ ኦብነግና ወያኔ ፤ ወይም ዛሬ በስልጣን ላይ ያለው “የትግሬው መንግሥትን” የመሳሰሉት የሚያራግቡት የተንሸዋረረ አመለካከትና ተራ ፍሬ ፈርስኪ ፕሮፓጋንዳ ነው ።
መጀመሪያ እኔ “የትግሬ መንግሥት” እያልኩ ወደምጠራው ትንተና ከመሄዴ በፊት በዚህ “የትግሬ መንግሥትና” በቀደሙ ኢትዮጵያን ባስተዳደሩ ነገር ግን በጸረ ኢትዮጵያ ቡድኖች የአማራው መንግሥት እየተባሉ ስለሚጠሩት በሁለቱ በኩል ያለውን ትልቅ ልዩነት በተቻለ ለማስረዳት እሞክራለሁ ።
እስቲ ግን ወደዚያ ከመሄዴ በፊት ይህንን ጽሁፍ በመጫን የወያኔ ቁንጮ የሆነው ስብሃት ነጋ በመባል የሚታወቀው ግለሰብ ከዝጉብኝ እንደወጣ ባልተሟሸ አፉ የሚለውን ያድምጡ
ይህ የአማራው መንግሥት እየተባለ በብተና ካህኖች የሚጠራው የአፄ ምኒሊክ ፤ የአፄ ኃይለሥላሴም ሆነ የደርግ ስርዓተ መንግሥት ዛሬ አለሃፍረትና ይሉኝታ በትግሬ ተወላጆች ብቻ ከላይ እስከ እታች እንደተወረረው የስልጣን ተዋረድ በአማራው የተያዘ አልነበረም ። በቀድሞው መንግሥታዊ ስርአት በቁኝጮነትም የተቀመጡ መሪዎች ቢሆኑም የዘር ሀረጋቸው ቢጎተት ከአማራነት ይልቅ ወደ ሌላ ጎሳ የሚያደሉ እንደሆነ ይታወቃል ። ሆኖም ግን ወደነሱ የዘር ሀረግ ጉተታ አልገባም ፤ ስለነሱ የዘር ሀረግ ብዙ የተባለና የተፃፈ ስለሆነ ፤ ፍላጎቱ ያለው አስፈላጊውን ምርምር አድርጎ ሊደርስበት ይችላልና የተነሳሁበትን ቁም ነገሬን እንዳያስተኝ ምርምሩን ላንባቢያን እተወዋለሁ ።
ከላይ በዘረዘርኳቸው ሶሥት መንግሥታዊ ስርአት መዋቅር ውስጥ በአስተዳደርና በመሪነት ተቀምጠው የነበሩ ግለሰቦች ዛሬ በታኞች እንደሚዘባርቁት ከአማራው ብሄር የተውጣጡ ሳይሆኑ ፤ እውነቱ ፤ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያቀፈና እንዲያውም ዛሬ ካለው አገዛዝ ጋር ሲነፃፀር እንደምሳሌነትና እንደ አብነት ሊጠቀሱ የሚገባቸው ሁሉን አቀፍ መንግሥታዊ አስተዳደሮች እንደነበሩ ነው ።
መነገር ካስፈለገ ባለፉት ሶሥት ስርአቶች ባብዛኛው መንግሥታዊ መዋቅር በበላይነት የስልጣን ኮሪቻውን ይዘው የነበሩት በአንደኛ ደረጃ ኦሮሞ ፤ በሁለተኛ ደረጃ ትግሬ ፤ በሶሥተኛ ደረጃ አማራ እንደሆነና እንዲያም እያለ በሐገራችን ያሉትን ጎሳዎች ሁሉ ያካተተ እንጂ ዛሬ እንደሚደሰኮረው ተረት ፤ ተረት ፤ እንዳልነበረ ከማንም የተሰወረ አይደለም ።
ለተጨማሪ መረጃ “ኢትዮጵያን ማን ገዛ” የሚለውን ከአፄ ምኒሊክ እስከ ደርግ ዘመነ መንግሥት የነበሩትን ከፍተኛ የባለስልጣናት ሥም ዝርዝር ለመመልከት እዚህ ላይ በመጫንም ሆነ አንዳንድ ድረ ገፆችን በመጎብኘት መመልከት ይቻላል
ለዚህ ሁሉ መሰረተ ቢስ ውዥንብር መንስኤው የአማርኛ ቋንቋ የአገራችን ብሄራዊ ቋንቋ መሆኑ እንደሆነ ከማንም የተሰወረ አይደለም ። ከዚያም በመነጨ የብተና አቀንቃኞች ስውር አላማቸውን ለማሳካት ሲሉ የአማርኛ ቋንቋን ማደግ እነሱ እንዲታመንላቸው ከሚጥሩትና ከሚደክሙበት የአማራው አገዛዝ ብለው ከለጠፉት መሰረተ ቢስ ውንጀላ ጋር ሊያጎዳኙትና የተወላገደ ታሪክ ለመመዝገብ ፤ ህልማቸውንና ምኞታቸውን ዕውን ለማድረግ ፤ እንደ ዋና መሳሪያ አድርገው ለመጠቀም ላይ ታች የሚዋትቱበት አላማ እንጂ ፤ ምንም እውነታን ያልተላበሰ የደካሞች አሉባልታ እንደሆነ ይታወቃል ።
የአማርኛ ቋንቋም የብሄራዊ ቋንቋ ሊሆን የበቃበትና ቋንቋውም እያደገ መምጣት ፤ ብሎም በአብዛኛው ኢትዮጽያዊ ተቀባይነት ማግኘት ፤ እራሱን የቻለ አንድ ሰፊ ትንታኔ የሚፈልግ ስለሆነ ወደሱ ሳልገባ የቋንቋው ማደግ ግን አፍራሾች እንደሚሉት የአማራ መንግሥት ስልጣኑን በመያዙና
ያ… የአማራ መንግሥት ብለው የሚጠሩት በሌሎች ቋንቋዎች ላይ ባደረገው ተጽዕኖ ወይም ጭቆና የወጣና እራሱን ያዳበረ እንዳልሆነ ግን ሳላስገነዝብ አላልፍም ።
ወደተነሳሁበት ርዕስ ስመለስ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ወይንም ሆን ብለን ነገሮችን ለማንሻፈፍ ካለን ጽኑ ፍላጎት ካልሆነ በቀር ዛሬ ኢትዮጵያን አፈር ድሜ እያስጋጠና እየገዛ ያለው “የትግሬ መንግሥት፤ ነው ። እደግመዋለሁ “የትግሬ መንግሥት” ነው ።
ለምን የትግሬ መንግሥት እንዳልኩት በተቻለ ለመዘርዘር እሞክራለሁ ። በመጀመሪያ ከላይ በቁኝጮነት የተቀመጠው ጠ /ሚኒስትሩና ጠቅላላ የፖሊት ቢሮ አባላት በሙሉ የትግሬ ተወላጆች ናቸው ። የህወሃት (ወያኔ ) አባሎች ናቸው ። ባብዛኛው መንግሥታዊ መዋቅር ውስጥ በበላይ አዛዥነት ከፍተኛውን መንግሥታዊ ስልጣን የያዙት በሙሉ የትግሬ ተወላጆች ናቸው ። ከብዙ በጥቂቱ ፤ በጸጥታ ፣ በፍርድ ሚንስትር ፤ በአምባሳደርነት ፤ በፖሊስና በመከላከያ ሰራዊቱ ከፍተኛ ቦታዎች በሙሉ ወይንም ባብዛኛው የትግሬ ተወላጆች ናቸው ።
አንድን መንግሥት ከአንድ ጎሳ የተውጣጣ ነው ብሎ ለመናገር በመጀመሪያ መመልከት የሚኖርብን ያንን መንግሥት ሳይንገዳገድ ጸንቶ እንዲቆም የሚያደርጉትን መንግሥታዊ መዋቅሮች ውስጥ በከፈተኛ ባለስልጣንነት ያስቀመጣቸውን ግለሰቦች መመልከቱ ለጥያቄው አጥጋቢ መልስ ይሰጣል ብዬ አምናለሁ።
እንግዲህ እግዜር ያሳያችሁ የትግሬ ሕዝብ ከጠቅላላው ኢትዮጵያ የሕዝብ ብዛት ሲነፃጸር ከአራት ወይም ከአምስት በመቶ አይበልጥም ፤ ነገር ግን አገሪቱ ካላት ከፍተኛ መንግሥታዊ መዋቅር ውስጥ ሰማንያ በመቶ ወይም ከዚያ በላይ የሚሆነውን ይዘው ይገኛሉ ።
በተለይ የጸጥታ ፤ የፖሊስና የመከላከያ ሰራዊቱ ከሃምሳ አለቃ እስከ ጄኔራል ያለው የማዕረግ እርከን ንፋስ በማያስገባ ሁኔታ ጥቅጥቅ ተደርጎ የታጠረው በትግሬ መኮንኖች ነው ፤ ይህ እንደሌላው የሲቪል ባለስልጣናት ሰማንያ በመቶ የተያዘ ሳይሆን ፤ መቶ በመቶ የተያዘ እንደሆነ ይታወቃል ። ይህ ሁሉ አድሎዋዊና ጎጠኛነት በነገሰበት በወያኔ ስርአት ፤ አንድን መንግሥት እንደ መንግሥትነት ሊቀጥል የሚያስችሉትን ከፍተኛ የሆኑ የስልጣን እርከኖች በሙሉ በአንድ ጎሳ ተወጥሮና ታጥሮ እያየሁ ታዲያ ምን ብዬ ልጥራው ?“የትግሬ መንግሥት” ማለት አግባብነት ከሌለው ፤ ታዲያ ! የሴራሊዮን መንግሥት ልበለው ? ተዉ እንጂ ! እየተስተዋለ ።
ለመሆኑ ባለፉት ሶሥት ስርአቶች ውስጥ በየትኛው ስርአት ውስጥ ነው ከአማራ ብቻ የተውጣጣ የጦር ሰራዊት የተቋቋመው ? ዛሬ ግን በትግሬው አገዛዝ ውስጥ አጋዚ የሚባል ከትግሬ ጎሳ ብቻ የተውጣጣ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሰራዊትን የገነባን ወያኔን ፤ ጎጠኛ መንግሥት አይደለም ብሎ መደስኮር እራስን ከማታለል ወይም ያለውን የጎጠኛ ስርአት ከመለማመጥና ከመፍራት ፤ አሊያም በራስ ካለመተማመን የመጣ በሽታ ካልሆነ በቀር ሌላ ምክንያት ሊኖረው አይችልም።
ይህ አይነት አይን ያወጣና ጥርስ ያገጠጠ የጎጣኛ ስርአት በአፄ ምኒሊክ ዘመነ መንግሥትም ሆነ ከዚያ ስርአት በኋላ በመጡት መንግሥታዊ ስርአቶች አልታየም ። እንዲህ አይነት ጨፍኑና እናሞኛችሁ አይነት ወንጀል ተደርጎም አያውቅ ፤ ዛሬ ግን የምዬን ላብዬ የሆኑ ዘመነኞች ወተት ጥቁር ነው ፤ ውሃ በመጥረቢያ ይፈለጣል ፤ የአለት ንቃት በወስፌ ይጠገናል፤ ሲሉን አዎ ልክ ነው እያሉ ማራገብ ፤ ያስተዛዝባል ፤ በዚህ ሁኔታ አድር ባዩ ፤ ፈሪው ፤ ካድሬው ባንድ ላይ ተሰልፎ እንደ አሚና በየ ሰዉ ደጃፍ እየዞሩ ሲለፈልፉ ቁጭ ብሎ መመልከትና እውነቱን አለማስተማር ኢትዮጵያዊነት አይደለም ።
የሚገርመው ግን ማንም ጎጠኛ እየተነሳ ያለፉትን መንግሥታት ሁሉ የአማራው መንግሥታት ፤ ነፍጠኞች ፤ እያለ ሲያላዝን ፤ በሌላው ወገን ደግሞ ዛሬ አይናችን እያየ እጃችን እየዳሰሰ ያለውን
“የትግሬን መንግሥት” ለምን የትግሬ መንግሥት አላችሁ ብሎ ቡራ ከረዩውን ስሰማ የዚህ ሁሉ ማደናቆር መንስኤው ምን ይሆን ብሎ መጠየቁ አግባብነት አለው ብዬ አምናለሁ ።
በመሰረቱ ባለፉት ሶሥት መንግሥታዊ ስርአቶች አንድን ጎሳ በመንግሥት ደረጃ የሰደበ ፤ ያንቋሸሸ ፤ ያሳደደ የለም ። ዛሬ ግን “የትግሬው መንግሥት” በአማራው ላይ ሕዝብ እንዲነሳሳ ያደረገ ፤ የአማራውን ሕዝብ ያስጨፈጨፈ ፤ በአደባባአይ ወጥቶ የአማራ ነፍጠኞች በማለት ሊያናንቅ የሞከረ ፤ መሆኑ እየታወቀ ዛሬ እኛ የትግሬ መንግሥት አትበሉ የምንባልበት ምክንያቱ ሊገባኝ አልቻለም ።
የትግሬ መንግሥት አይደለም ብሎም ያሳመነኝም የለም ፤ ሊያሳምነኝም አይችልም ፤ እንደ ማስተዛዘኛ የሚጠቀሙት ከአማራውም ሆነ ከኦሮሞ ወይንም ከሌላ ጎሳ የመጣ ወያኔ እንዳለ ነው ። እነኚህ በገብስ ቆሎ ላይ እንደ ኑግ የተበተኑ ወያኔዎች አንደኛ ትግሬዎች አይደሉም ፤ ወያኔ ለመሆን ትግሬ መሆንን ይጠይቃል ፤ ከስሙም እንደምንረዳውና እንደነሱም አላማ “ሕወሀት” “የትግሬ ነፃ አውጪ” እንጂ የአማራ ወይም የኦሮሞ ነፃ አውጪ ማለት አይደለም ። ስለሆነም እንዲያው ለለጋሽ አገሮች ሕብረ ብሄር ለማስመሰል የተቀላቀሉ መለመኛ ጉዶች እንጂ ፤ ወያኔ በደደቢቱ የወያኔ ሂሳብ የሚመለከታቸው ሳይሆኑ (Naturalized ) ወያኔዎች አድርጎ ነው የሚመለከታቸው ፤ ስለሆነም ልክ እኛ በያለንበት አገር የወሰድነውን ዜግነት ጥፋት አጠፋችሁ ተብለን ዜግነታችንን እንደምንገፈፍ ሁሉ እነዚህም ከሌላ ጎሳ የተውጣጡ ወያኔዎች አሸዋ ክምር ላይ የቆሙ ወያኔዎች በመሆናቸው ወያኔነታቸውን ባማናቸውም ጊዜ ሊገፈፉ የሚችሉ ሁለተኛ ደረጃ ወያኔዎች ናቸው ። ስለሆነም የነዚህ ወዶ ገባ ወያኔዎች በመሃከላቸው መጎለት የትግሬ መንግሥት አይደለም ላለማለት አጥጋቢ መከራከሪያ አይሆንም ።
ሌላው አስገራሚ ነገር ቢኖር ባብዛኛው ሰዉ አማራ ፤ ኦሮሞ ወዘተ…ብሎ ለመጥራት ምንም ችግር የለበትም ፤ ነገር ግን “ትግሬ” ብሎ ለመጥራት ግን እንደ ሃጢያት ይሁን ፤ እንደ ወንጀል ፤ የሚታየው አልገባኝም ፤ ምናልባት ቃሉ ላይ እኔ ያልተገነዘብኩት አስፈሪ የሆነ ነገር እንዳለ ለመረዳት ብዬ “ትግሬ” የሚለውን ሆሄያት ማጤን ጀመርኩ ። ያደረኩትን ባደርግ ያው እንደሌላው የአማርኛ ሆሄያት ከመሆን በቀር ፤ ምንም እንከን አላገኘሁባቸውምና የሕብረተሰቡ ፍራቻ ከምን የመነጨ እንደሆነ እንቆቅልሽ እንደሆነብኝ አለሁ ።
እንግዲህ አንድ ሰው ወላጆቹ ባወጡለት ሥም ይጠራል ፤ ወላጆቹ ካወጡለት ሥም ውጪ በጎረቤት ወይም ባካባቢው ህብረተሰብ በሌላ ሥም የሚጠራ ከሆነ ያ ትክክለኛ ሥሙ ሳይሆን “ቅጽል” ሥም በመባል ይታወቃል ፤ ታዲያ አማራውን ፤ አማራ ብለን ስነጠራ ፤ ኦሮሞውን ፤ ኦሮሞ ብለን ስንጠራ ፤ ጉራጌውን ፤ ጉራጌ ፤ ብለን ስንጠራ ፤ ለምን ትግሬ ጋ ስንደርስ ፤ ትግሬ አትበሉ እንባላለን ? ታዲያ ማን ብለን እንጥራቸው ? ሥማቸው ተቀይሮስ ከሆነ ለምን ይፋ አይሆንምና ባዲሱ ስማቸው አንጠራቸውም ? ይህ ሳይሟላ እንዲያው በደፈናው ትግሬ አትበሉ የሚባልበት ጉዳይ ሚስጥሩ ስላልገባኝ ፤ የገባው ካለ ቢያስረዳኝ እወዳለሁ ።
ይህ ብቻም አይደለም ፤ ወያኔም አትበሉም ይባላል ፤ እንዴት ለራሳቸው ያወጡትን ሥም ሌላው ሲጠራው ጸያፍ አባባል እንደሆነ ሊያስረዱ ሲሞክሩ ይገርመኛል ። እነሱ በስማችን አፈርን ሳይሉ እስከ ዛሬ ድረስ የወያኔ 30ኛ ፤ 30 ምናምነኛ ዓመት አከበርን እያሉ ሲቦተልኩ ነውር ነው ወያኔዎች ነን አትበሉ አይባልም ፤ በነሱ አፍ ሲጠራ ይቀበሉታል በሌላው ሲሆን ወንጀል ይሆናል ፤ ዘመነ ግርምቢጥ ማለት እንግዲህ ይሄ ነው ።
ወደ ግራም ወደ ቀኝም ብናገላብጠው ፤ ወያኔ ትግሬ ነው ፤ ትግሬም ኢትዮጵያን እየገዛ ነው ፤ ስለሆነም ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው የትግሬ መንግሥት ነው ! ሃቁ ይሄው ነውና እንቀበለው ።
ማሳሰቢያ :-
እዚህ ላይ አንድ ማሳሰብ የምፈልገው ነገር ቢኖር የትግሬ ምሁራን (Elite) የኢትዮጵያን ሕዝብም ሆነ ኢትዮጵያን ከድተዋል ፤ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ አሁን ካለው አገዛዝ ጋር በመሰለፍ ኢትዮጵያን ለማዳን በሚደረገው ማናቸውም ጥሪ ተባባሪም ፤ ተሳታፊም ለመሆን ፤ ፈቃደኝነት ባለማሳየታቸው ፤ በነዚህ ምሁራን ላይ የሚሰነዘረውን ማንኛውንም አይነት ወቀሳም ይሁን ውግዘት ፤ በትግሬ ሕዝብ ላይ እንደተሰነዘረ አድርገው ለማቅረብ የሚፈልጉ አንዳንድ የዚሁ አገዛዝ አጫፋሪዎች ስላሉ የትግሉ አላማና እየተደረገ ያለው ትግል ከአገዛዙና አገዛዙን ከሚደግፉ ምሁራን ጋር እንጂ ከሕዝብ ጋር እንዳልሆነ ማስተማሩ ተገቢ ነው ። በመሰረቱ ምሁር ምንም እንኳን ከሕዝብ መሃከል የወጣ ቢሆንም ነገር ግን ምሁር ማለት ሕዝብ ማለት እንዳልሆነ መታወቅ አለበት ፤ ይህንን ለምሁሩ የተሰነዘረውን አባባል ለሕዝብ እንደተሰነዘረ አድርጎ ሕዝብን ከሕዝብ ለማለያየትና ለማቃቃር የሚደረገው ተራ ማደናገር ካገዛዙ አገልጋዮች እንደመጣ ተገንዝቦ ተቀባይነት እንዳይኖራቸው ሕግረተሰቡን በትጋት ማስተማር ተገቢ ነው ።
ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ !
ከአይምሮ ዳኛቸው

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.