የሰማእታቱ መነኩሴ የአቡነ ጴጥሮስ የእምነትና የጽናት ገድል

 

ከዚህ ቀደም በፈረንጅ አፍ ብዙ ጊዜ ደጋግሜ ታሪካቸውን ባቀርበውም እኝህ ጀግና መንፈሳዊ አባት አቡነ ጴጥሮስ ለአገራቸው ለእምነታቸው እና ለማንነታቸው ክብር ሲሉ የከፈሉትን መስዋዕትነት ደጋግሞ ማውሳቱ ትላንት የት ነበርን ዛሬስ ምን ላይ ደረስን ብለን በአስተዋይነት እንድናስብ ይረዳናል፤

ከፍቼ ምድር በምዕራባውያን አቆጣጣር በ1892 ዓም የተቀዱት ጀግናው መነኩሴ አብነ ጴጥሮስ ከረጅም መራራ አስቸጋሪ የጾም የጸሎት ጉዞ እና መንፈሳዊ አገልግሎት በኋላ በምዕራባውያን አቆጣጣር በ1936 ዓም አገር የወረረውን የፋሽስት ጦር በእጅግ በመቃወም, በየቦታው እየተዘዋወሩ አገሬን ብሎ በከፍተኛ አመጽ የተነሳውን አርበኛ ሲያበረታቱ እና ሲያጽናኑ ቆይተው በጥቁማ በፍሽስት ወታደሮች ተያዙ።

ከዛም ወደ ከፍተኛ የጥሊያን ሹማምንት ፊት በግዳጅ ተወስደው የፋሽስትን ጦር እንዲባርኩ በተጠየቁ ጊዜ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው….አንተ አገሬን ልታጠፋ… ሀይማኖቴን ልትቀየር… ወገኔን ልትዘርፍ እና ልትገድል…. የመጣህ ግፈኛ ጠላት እንዴት ሕሊናዬ ፈቅዶልኝ እባርከሀለሁ? የአንተን ግፍ እና በደል ደግፌስ እንዴት አድርጌ በፈጣሪዬ ፊት እቆማለሁ? ብለው የፍሽስትን ወራራ በገሀድ በማውገዛቸው በምዕራባውያን አቆጣጠር 29 July 1936 በሞት ተቀጥተዋል።

በዚህ ሩቅ ዘመን በኢትዮጲያ ምድር የኖረ አንድ እንቁላል በጅምላ ነጋዴ የአረመን ተወላጅ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ አቡኑ እንዴት እንደተገደሉ እና አስክሬናቸውም ቀኑን ሙሉ ከጎዳናው ዳር ተጥሎ ማርፈዱን አስተውሎ ለታሪክ መስክሮአል።

እኛም እነዚህን ከመሰሉ ቆራጥ አባቶች ተፈጥረን… ቅስመ ሰባራ ግዴለሽ እና ፈሪ ብሄረተኛ አንሁን።

source: Edwardo’s history page (Facebook)

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

Archives

Copyright and Disclaimer

Copyright © 2010 - 2015 Kefale Alemu

Copyright © [2010]. KAlemu, All Rights Reserved.