ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይለምልም ብሄረተኝነት ስሩ ተነቅሎ ይዉደም
ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይለምልም ብሄረተኝነት ስሩ ተነቅሎ ይዉደም
በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት መፈክር ለማሰማት መነሳት ፈገግ ያደርጋል:: ምክንያቱም ሰሜኑ : ደቡቡ: ምዕራቡ: ምስራቁ እንዲሁም መሀሉ የኢትዮጵያያ ክፍል በብሄረተኝነት ተወጥሯል:: ብሄረተኝነት እንደ ጀግንነት: ብልጠትና ጀብደኝነት በብዙሃኑ ምሁራን እና ፖለቲከኛ ህሊና ዉስጥ ይንቆረቆራል:: ጀግናውም ፈሪዉም ብሄረተኝነት እንደ ፋሽን መለበስ ያለበት ልብስ መስሎታል:: ይሄ ሁሉ ቢሆንም ብሄረተኝነት ከኢትዮጵያ ምድር መነቀል አለበተ:: ሰንኮፉ እንኳን እንዳይቀር በደንብ ተምሶ መነቀል አለበት::ግን ለምን የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም:: ዋና ዋና ምክንያቱ አራት ነዉ::
1. አንድም ሁሉም ብሄረተኛ ፖለቲከኞች አንድ የጋራ ስነልቦና አላቸዉ:: ይሄም ጸረ -ኢትዮጵያዊነት: ጸረ ሀገርነት እና ጸረ ዉህደት ናቸዉ:: ብሄረተኛ ፖለቲከኞች ሀገርን የሚያህል ነገር ለጎሳቸዉ ጥቅም ይሰዉታል:: ሀገርን የሚያህል ነገር ለጎሳቸዉ የበላይነት ሲሉ አንቀዉ ያርዱታል:: ብሄረተኝነት ከዚህ ብሄር ወይም ከበዚያ ብሄር በወጣ ፖለቲከኛ ቢደረግ ያዉ ብሄረተኝነት ነዉ:: ለሀገር እና ለብዙሃን ጥቅም ነቀርሳ ነዉ::
2. አንድም ብሄረተኝነት በአንድ ሀገር ሲንሰራፋ እና የበላይነት ሲያገኝ ይዋል ይደር እንጅ በአንዲት አገር ብሄሮች /ማህበረሰቦች መሃከል የጎሳ ጦርነት: የእርስ በእርስ ጦርነት መነሳቱ አይቀርም:: ምክንያቱም ብሄረተኞች ሁሉንም ህዝብ በእኩልነት ማስተዳደር ስለማይችሉ ጥላቻና ምሬትን በተለያዩ ማበረሰቦች መሃከል ይፈጥራሉ:: ብሎም ሀገሩን ወደ ግጭት ይወስዱታል:: ህዝቡንም እርስ በእርስ እንዲጠፋፋ ያደርጉታል:: ማህበረሰቡ ተፈራርቶ እንዲኖር ጥላቻና አሉባልታ በህዝቦች መሃከል እየዘሩ ልዩነትን ያሰፋሉ::
3. አንድም ብሄረተኞች የበላይነት ሲያገኙ አገረ በሂደት ይፈርሳል:: ምክንያቱም ሁሉም ብሄረተኞች አንድ ሀገር: አንድ ባንዲራ አንድ መንግስት የሚለዉ ሀሳብ ተቃዋሚ ስለሆኑ ሁሉም የሚያደቡት ልዩነትን አራምደዉ ስለመለያዬት ስለሆነ ነዉ:: ይሄ ሚስጥር የገባቸዉ ሃያላኖቹ አሜሪካኖች አንድ ሀገር አንድ ባንዲራ ብለዉ ጠዋት ማታ ይዘምራሉ::
አንድ ሀገር እና አንድ ባንዲራ የሚለዉ ያሜሪካኖች መዝሙር በሁሉም ዉጤታማ ሀገራት ዉስጥ ይገኛል:: ታላላቅ ሀገራት ቻይና : ሩሲያ : እንግሊዝ: ጀርመን: ፈረንሳይ : ኢራን: ቱርክ: አርጀንቲና : ብራዚል ወይም ማንም ሀገር ብሄረተኝነትን በሀገራዊነት ተክተዉ አያዉቁም:: ሀገራዊነት መመሪያቸዉ ነዉ:: በተቃራኒዉ ግን በርካታ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተከናወነባቸዉ ሀገራት የሚገኙት ብሀረተኝነት ሀገራዊነትን ሲዉጠዉ ነዉ:: ስለሆነም አንድ ህዝብ እንደ ህዝብ በጋራ መኖር ካለበት እንዲሁም አንድ ሀገር እንደ ሀገር መኖር ካለበት የመጀመሪያዉ ስራዉ ጎሰንነትና ብሄረተኝነትን መንቀል ነዉ:: ከስሩ ነቅሎ ማቃጠል::
ዳግም እንዳያለመልም አድርጎ ማጥፋት:: በሁለት ልብ ማንከስ አይቻልም:: ወይ ኢትዮጵያን ትመርጣለህ አለዚያም ጎሳህን ትመርጣለህ::
4. በመጨረሻም ሀገር በብሄረተኝነት እግር ስር ሲወድቅ ሀገሩ መፍረሱ አይቀርም::
በኢትዮጵያዊነት ሀገራዊ እሴት ላይ አትደራደር:: ብሄረተኝነት ይዉደም በል:: ኢትዮጵያዊነት ይለምልም ስትል ድምጽህን ከፍ አድርገህ ዘምር:: ብሄረተኛ ቡድኖች: ሀይሎች: ፓርቲዎች እና ምሁራን በዝተዉ ብታያቸዉ ዉስጣቸዉ ባዶና ፈሪዎች መሆናቸዉን አትርሳ:: በእኩልነት: በሁሉም የሰዉ ልጆች ዲሞክራሲ: በሁሉም የሰዉልጆች ሰበአዊ መብትና በሁሉም ዜጎች የጋራ ብልጽግና አያምኑም::
ይህ ወቅት እንዲሁም ምናልባትም የሚመጡት ጥቂት አመታት ጭምር ኢትዮጵያዊነት በመጨርሻዉ የፈተና አጣብቂኝ ዉስጥ መዉደቁ አይቀርም:: በርካታ ምሁራን እና ልሂቃን በኢትዮጵያዊነት ላይ ፊታቸዉን ያዞሩበታል:: ቢሆንም በጥቂት ጀግኖች ኢትዮጵያዊነትን ያድኑታል:: ብሄረተኝነትም ስሩ ይነቀላል:: ጸንተህ ቁም:: አትወለጋገድ:: ኢትዮጵያዊነት የሚያራምዱ ሀይሎችን ካሉበት ፈልፍለህ አዉጣቸዉ:: ከጎሰኞችና ከብሄረተኞች ጋር ግን አትደራደር: ጎሰኞችና ብሄረተኞች የሰዉን አስተሳሰብ በብሄረኡ ደም ስለሚለኩ ከእነሱ ጋር ሀሳብ ማዉራት አይቻልም::
መሃል ላይ መስፈር አይቻልም:: ወይ ወደ ብሄረተኝነት ጎራ ወይ ወደ ኢትዮጵያዊነት ጎራ መጠቃለል ግድ ነዉ:: ለዛሬ ጽንሰ ሀሳብ ከተነጋገርን ለነገ ደግሞ የጽንሰ ሀሳብ ትግበራዉን በጋራ እንጀምራለን:: ወይም በልዩነት መስመር ላይ እንቆማለን:: ጽንሰ ሀሳብ ከተግባር ይቀድማል እንዲሉ አቢዮተኞች የትግል መጀመሪያዉ ጽንሰ ሀሳብ ላይ ግልጽ መሆን ነዉ: ስለሆነም እኛ እንዲህ እንላለን :- ኢትዮጵያዊነት ለዘላለም ይለምልም:: ብሄረተኝነት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስሩ ተነቅሎ ይወደም::
ጎሰኛ እና ብሄረተኛ ፖለቲከኞች ምሁራን እና ልሂቃን “በሐሰት የሚናገሩ ሐሰተኛ ምስክሮ በወንድማማቾች መካከልም ጠብን የሚዘሩ” ሰዎች ናቸዉ:: በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራን ደግሞ የእግዚአብሄር ነብስ ከምንም በላይ ትጸየፈዋለች:: በመጽሀፈ ምሳሌ 6:16 እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ:: “እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች :: ትዕቢተኛ ዓይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ:: ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥ ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር:: በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።”
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ:: የኢትዮጵያን ህዝብ ልብ ወደ አንድ ያምጣ ! ጎሰኞችና ብሄረተኞች ከደገሱለት የእርስ በእርስ ጦርነት የኢትዮጵያን ህዝብ እግዚአብሄር ይጠብቅ !