አባባሎች በግጥም
አባባሎች በስድ ንባ
ትንሽ ስለአማርኛ
ሰምና ወርቅ
አባባሎች በግጥም
አባባሎች በስድ ንባብ
እንዃን ደህና መጡ ሰምና ወርቅና አባባሎች (ነገር በምሳሌ ጠጂ በብርሌ)
ሰምና ወርቅ |
አባባሎች በግጥም |
አባባሎች በስድ ንባብ |
ነይልኝ በፈረስ በሚገስግሰዉ!
መቸ በቅሎ ያዉቃል እንዳንቺ ያለ ሰዉ
ሞጣ ቀራኒዮ ምነዉ አይታረስ
በሬ ሳላይ መጣሁ ክዚያ እስከዚህ ድረሰ
አዳራሹ ሰፊ ቤቱ አልጠበባችሁ
በተራ በተራ ምነዉ መግባታችሁ?
≈ ≈ ≈ ≈ ≈
ከዚህ በታች ያለዉ ግጥም ከአቶ
ሰዉ ማለት ይኸነዉ የተገኘ ነዉ።
ማን አስተማራቸዉ ይህን ሁሉ ሚስጥር
ማን ነግሮአቸው ነበር ነገር እንደሚያደክም
በነጠላ ሲሆን እንደማያስደምም
እነዲህ እንዲያወሩ
በምሳሌ አድርገው ነገር እንዲያበራሩ
ከመሰልቸት ይልቅ አእምሮ እንዲፈተን
እያሳሳቀን እያጨዋወተን
ነገር እንዲበተን ደግሞ እንዲተነተን
አንድ ቃል ብዙን ወክሎ እንዲናገር
ማን አስተማራቸዉ ዪህን ሁሉ ሚስጥር?
|
ድር ቢያብር
አንበሳ ያስር
ያላወቁ
አለቁ
እባብ ለባብ
ይተያያሉ ካብ ለካብ
አንቺዉ ታመጪዉ
አንችዉ ታሮጪዉ
ምከረዉ ምከረዉ
እምቢ ካለ መከራ ይምከረዉ
ሳይከካ
ተቦካ
ቀና ሲታጣ
ይመለመላል ጎባጣ
ያለ አንድ የላት ጥርስ
በዘነዘና ትነቀስ
የምታቦካው የላት
የምትጋግረው አማራት
የጅብ ፍቅር
እስኪቸግር
በቅሎ ግዙ ግዙ
አንድ አሞሌ ጨው ላያግዙ
ዘመድ ከዘመዱ
አህያ ከአመዱ
ከድጡ
ወደ ማጡ
ላም አለኝ በሰማይ
ወተቷንም አላይ
ሰው ሲያማ
ለኔ ብለህ ስማ
ወደሽ ከተደፋሽ
ቢረግጡሽ አይከፋሽ
ባጎረስኩ
እጄን ተነከስኩ
ሳል ይዞ ስርቆት
ቂም ይዞ ፀሎት
ላያዘልቅ ፀሎት
ለቅስፈት
ከኑግ የተገኘህ ሰሊጥ
አብረህ ተወቀጥ
ያልጠረጠረ
ተመነጠረ
ስራ ለሰሪው
እሾህ ለአጣሪው
አባቱ ዳኛ
ልጁ ቀማኛ
ተልባ ቢንጫጫ
በአንድ ሙቀጫ
አትሩጥ
አንጋጥ
መቀመጥ
መቆመጥ
ካለ ፈጣሪ
አሟጠሽ ጋግሪ
የትም ፍጪው
ዱቄቱን አምጪው
ፍየል ከመድረሷ
ቅጠል መበጠሷ
አለባብሰው ቢያርሱ
በአረም ይመለሱ
ንገረው ንገረው
እምቢ ካለ መከራ ይምከረው
ከስስታም አንድ ——
ዶሮን ሲያታልሏት
በመጫኛ ጣሏት
የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ
አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ
ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ
ይበጣጠስ
አተርፍ ባይ
አጉዳይ
ድር ቢያብር
አንበሳ ያስር
አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል
የሰዉ ፈላጊ የራሱን ያጣል
ሰው ሲያማ
ለኔ ብለህ ስማ
እርስዎ የሚያዉቁቅ ምሳሌአዊ አነጋገር ካለ ከታች ባለዉ ቦታ ዉስጥ ቢጽፉልን ይደርስናል::
|
ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም
የጋን ዉሰጥ መብራት
ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ
ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
ሰዶ ማሳደድ ቢያምርህ
ዶሮህን በቆቅ ለዉጥ
ሲበሉ የላኩት
አላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል
አላርፍ ያለች ጣት አር ጠንቁላ ትወጣለች
በሬ ከአራጁ
አባይ ማደሪያ የለው ግንድ ይዞ ይዞራል
የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ
አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል
በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት
አልሸሹም ዞር አሉ
ታጥቦ ጭቃ
አይጥ ሞቷን ስትሻ ሄዳ ታሸታለች የድመትአፍንጫ
የቆጡን አወርዳለሁ ብላ የብብቷን ጣለች
የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል
ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ
እጸድቅ ብዬ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች
ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሀል
ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም
የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል
ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ
አዛኝ ቅቤ አንጓች
አልሸሹም ዞር አሉ
ታጥቦ ጭቃ
የቆጡን አወርዳለሁ ብላ የብብቷ ጣለች
በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት
አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል
የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ
ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል
አህያውን ፈርቶ ዳውላውን
ሴት የላከው ሞት አይፈራም
ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል
አመድ በዱቄት ይስቃል
ላለፈ ክረምት ቤት አይሰራለትም
የፈሰሰ ውሀ አይታፈስም
ስጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አንድ አለ
አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት መጽሀፍ አጥባ ቆየች
የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ
እሱ የከፈተውን ጉሮሮ
ሳይዘጋው አያድርም
አታግባና የሰው አጥር ዝለል
ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል
አልጠግብ ባይ ሲተፋ ያድራል
ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል
ሀምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሀምሳ ሰው ጌጡ
እውነቱን ተናግሮ ካመሹበት ማደር
ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል
ከእጅ አይሻል ዶማ
በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ
የአህያ ባል ከጅብ አያስጥል
ያዲያቆነ ሰይጣን
ሳያቀስ አይለቅም
ተፈጥሮን ተመክሮ አይለዉጠዉም
ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
የነቶሎ ቶሎ ቤት ግርግዳዉ ሰንበሌጥ
የቆጡን አውርድ ብላ የብብቱዋን ጣለች
በሬ ካራጁ
አይነጋ መስሉዋት በቋት ተጸዳዳች
ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል
አመድ በዱቄት ይስቃል
እየ … ታንቀላፋለች
|
ወደ እራስጌ ለመመለስ ይህን ይጠቁሙ
Leave a Reply
You must be logged in to post a comment.